የነገረ መለኮት ንጽጽር (በኦርቶዶክስና በፕሮቴስታንት): የወደደ ሁሉ በነጻ እንዲጠቀምበት ተፖስቷል። ይሁን እንጂ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ስለሆነ በየትኛውም መልኩ ለንግድ እንዲውል አልተፈቀድም። ልዩ ልዩ መግቢያ የሚለውን መጀመሪያ ካነበቡ በኋላ የተቀረውን በተመረጠው ቅደም ተከተል ማንበብ ይቻላል። ልዩ ልዩ መግቢያ ጥምቀት ትውፊት (ወግና ልማድ) መካከለኝነት ጾም የድንግል ማርያም ክብሯና ዘላለማዊ ድንግልናዋ መንፈሳዊ ስጦታዎችና በልሳኖች የመናገር ስጦታ ሥርዐት ንስሐ
የምታገኙት ለወንድሜ ፓስተር ግርማ ቤካ አድርሱልኝ! ለፓስተር ግርማ ቤካ በአድራሻህ ከባንቱ ገብረማርያም ጉዳዩ፡ - ወንጌላውያንን ለኦርቶዶክሳውያን አታሽቃብጡ ስላልከው፡ የተወደድክ ወንድሜ ፓስተር ግርማ ቤካ፡ - ለጤናህ እንደምን አለህ ? እኔ ቸርነቱ የማያልቅበት መድኅኒዓለም ይክበር ይመስገን ደህና ነኝ። ለኦርቶዶክሶች ከሚጮኹት ጋር አትተባበሩ / አታሽቃብጡ ያልከው መልዕክት ደርሶኛል።አባል የሆንኩባትን ቤተክርስቲያንም ሆነ ወንጌላውያንን ወክዬ ለመናገር መብት እንደሌለኝ ታውቃለህ። ነገር ግን ከወንጌላውያን መኻል እንደመቆጠሬ መጠን የግሌን አቋም ለመግለጥና ለማብራራት ነው ይህንን ደብዳቤ የምልክልህ። ይፋዊ ማድረጌም መልዕክትህ ይፋዊ ስለሆነ ነው። ከሁሉ አስቀድሜ ግልጽነትህንና ስሜትህን ለመግለጥ መድፈርህን ማድነቄን ልገልጽልህ እወዳለሁ። በመቀጠል ወደ ጉዳዩ ልግባና መጀመሪያ በዝርዝር የተናገርከውን በአጭሩ ሳስቀምጠው፡፡ በቀጥታ ምክንያት አድርገህ ባታቀርባቸውም ከቋንቋ አገባቡ እንደተረዳሁት ከኦርቶዶክሶቹ ጋር እንዳንተባበር ( ማለትም እንዳናሽቃብጥላቸው ) የሚከተሉትን በምክንያትነት ተናግረሃል። 1. እንደ እኛ መከራን በፀጥታ ይቀበሉ 2. አሳዳጆቻችን ነበሩ 3. ለእኛ ድምጽ ሆነው አያው...