Skip to main content

Posts

Showing posts from February, 2025

ስለ "አስታዋሽ ጾምና በዐሉ" ጥያቄና መልስ

 ስለ "አስታዋሽ ጾምና በዐሉ" ጥያቄና መልስ  ለዐማራ ሕዝብና ዎገኖቹ፦ ሕልውናችንን-ነጻነትችንን የማረጋገጥና የማስቀጠል አንድነታችንን የመጠበቅና የማጠንከር  በእሴቶቻችን የመደሰት፣ እነርሱን የመንከባከብና የማስተዋወቅ  በረከታችንን የማብዛትና የማካፈል  ኃላፊነቶቻችንን በማኅበር ፣ በማስተዋልና በትጋት እንድንወጣ “ጾሙና በዐሉ" አስታዋሽ ባሕላዊ ምልክታችን ይሁንልን   ጥያቄ 1 ፡ አድማጭ ተመልካቾቻችን እንኳን ደህና መጣችሁ።የከበረ ሰላምታችን ይድረሳችሁ። ዛሬ የምንወያየው ከአቶ ባንቱ ገብረማርያም ጋር ይሆናል። አቶ ባንቱ በሙያው ፋርማሲት ነው። እንደነገረኝ በእምነቱ ደግሞ ባፕቲስት ነው።ለዐማራ ሕዝብና ዎገኖቹ ባሕላዊ ምልክት የሚሆን “ጾምና በዐልን” በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል። የምንወያየውም ስለዚሁ "ጾሙና በዐሉ" ምልክትነት ይሆናል።  አቶ ባንቱ ለመወያየት  ወደ እኛ በመምጣትህ አመሰግንሃለሁ። እንኳን ደህና መጣህ። አንተ እያልኩ ልቀጥል ወይስ አንቱ? መልስ 1፡ ዎገኔ፡   እንኳን ደህና ቆየኸኝ። ለአድማጭ ተመልካቾቻችሁም ሰላምታዬ ይድረስልኝ። አንተ በለኝ። የሚያውቀኝ ሁሉ አንተ ነው የሚለኝ።  ጥያቄ 2 ፡ እሺ  አንተ እያልኩ እቀጥላለሁ። አቶ ባንቱ፣ ምናልባትም ብዙ ሰው ስለማያውቅህ  እስቲ ስለራስህ በአጭሩ ንገረን። ወዲያውም መክፈቻ ይሆነናል መልስ 2 ዎገኔ ፦ አስቀድሜ ይኸን ዕድል ስለሰጠኸኝ ላመሰግንህ እወዳለሁ። አድማጭ ተመልካቾችህንም ጊዜ ወስደው  ውይይቱን  ስለሚከታተሉ ላመሰግናቸው እወዳለሁ።አዎን፣ ባንቱ ገብረማርያም እባላለሁ።እንደነገሩኝ የተወለድኩት ሽርካ በዛሬ አጠራሩ በአርሲ ዞን ነው።ነፍስ ያወቅሁትና ትምህርት ...

"ጾሙና በዐሉ አስተዋሽ ምልክት ይሁንልህ"

    ለአማራ   ሕዝብና ዎገኖቹ፡ - ከአዎን ድምጽ (Awon Dimts) ባንቱ ገብረማርያም ነኝ። ማንነቴን በሌሎች ጽሑፎች አስተዋውቄአለሁ።እንዳስፈላጊነቱ   ሌላ ጊዜ የምመለስበት ይሆናል።ዛሬ ግን ጊዜ ለመቆጠብ በቀጥታ ወደ ተነሳሁበት ጉዳይ እገባለሁ። ለዐማራ ሕዝብና ዎገኖቹ፡ - " ጾሙና በዐሉ "  አስተዋሽ ምልክት ይሁንልህ       የተከበረከውና የተወደድከው   የዐማራ   ሕዝብና   ዎገኖቹ ሆይ፡ - እንደምን ከርመሃል ? በአለሁበት ሥፍራ ሆኜ እንደምሰማው ከሆነ ከምንጊዜውም በላይ በሕልውናህና በነጻነትህ ላይ የተነሳብህን በንግግርም፥ በተግባርም   ለመቋቋም እጅግ በተሻለ ቁመናና ቁርጠኝነት ላይ ተገኝተሃል። የበርካታ ዐመታት ውስብስብ ተግዳሮቶችን አልፈህ እዚህ እንደደረስህ እረዳለሁ።ለዚህ በመብቃትህ ለአንተ ያለኝን አድናቆት መሸሸግ አይቻለኝም። መጎዳትህንና መጨነቅህን አይቶ እዚህ ላይ ለመድረስህ የአብርሃም አምላክና አምላካችን የረዳህ እንደሆነም አምኛለሁ። እርሱ ይመስገን። ለዘለቄታውም ሥጋትን የምታስተዳድርበት ዘዴ ወይም መድረክ ታዘጋጃለህ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።       ዛሬ በዚህ   ሚዲያ ብቅ ያልኩት በጎ ፈቃድህ ይሆናል በማለት በእኔ ዘንድ ያለውን ዐሳብ ላካፍልህ ነው። አዲስ " አስተሳሰብና አሠራር " ሲሆን መሪ ነጥቦቹን በአምስት አምዶች አሳጥሬ እንደሚከተለው አቀርባለሁ። ይህንን ሳቀርብ   እንደ ድፍረት እንዳይቆጠርብኝ በታ...