Skip to main content

"ጾሙና በዐሉ አስተዋሽ ምልክት ይሁንልህ"

 

 

ለአማራ  ሕዝብና ዎገኖቹ፡-

ከአዎን ድምጽ (Awon Dimts) ባንቱ ገብረማርያም ነኝ። ማንነቴን በሌሎች ጽሑፎች አስተዋውቄአለሁ።እንዳስፈላጊነቱ  ሌላ ጊዜ የምመለስበት ይሆናል።ዛሬ ግን ጊዜ ለመቆጠብ በቀጥታ ወደ ተነሳሁበት ጉዳይ እገባለሁ።

ለዐማራ ሕዝብና ዎገኖቹ፡-

"ጾሙና በዐሉአስተዋሽ ምልክት ይሁንልህ

     የተከበረከውና የተወደድከው  የዐማራ  ሕዝብና  ዎገኖቹ ሆይ፡-እንደምን ከርመሃል? በአለሁበት ሥፍራ ሆኜ እንደምሰማው ከሆነ ከምንጊዜውም በላይ በሕልውናህና በነጻነትህ ላይ የተነሳብህን በንግግርም፥ በተግባርም  ለመቋቋም እጅግ በተሻለ ቁመናና ቁርጠኝነት ላይ ተገኝተሃል። የበርካታ ዐመታት ውስብስብ ተግዳሮቶችን አልፈህ እዚህ እንደደረስህ እረዳለሁ።ለዚህ በመብቃትህ ለአንተ ያለኝን አድናቆት መሸሸግ አይቻለኝም። መጎዳትህንና መጨነቅህን አይቶ እዚህ ላይ ለመድረስህ የአብርሃም አምላክና አምላካችን የረዳህ እንደሆነም አምኛለሁ። እርሱ ይመስገን። ለዘለቄታውም ሥጋትን የምታስተዳድርበት ዘዴ ወይም መድረክ ታዘጋጃለህ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።

     ዛሬ በዚህ  ሚዲያ ብቅ ያልኩት በጎ ፈቃድህ ይሆናል በማለት በእኔ ዘንድ ያለውን ዐሳብ ላካፍልህ ነው። አዲስ "አስተሳሰብና አሠራር" ሲሆን መሪ ነጥቦቹን በአምስት አምዶች አሳጥሬ እንደሚከተለው አቀርባለሁ። ይህንን ሳቀርብ  እንደ ድፍረት እንዳይቆጠርብኝ በታላቅ ትህትና መሆኑን ልገልጽ እወዳለሁ።

1“ "አዎናዊ" አኗኗር

ሕልውናህንና-ነጻነትህን ለማረጋገጥና ለማስቀጠል

አንድነትህን ለመጠበቅና ለማጠንከር

በተወራረሱ እሴቶችህ ለመደሰት፤ እነርሱን ለመንከባከብና ለማስተዋወቅ

በረከቶችህን ለማብዛትና ለማካፈል

ያለብህን ኅላፊነት በማህበር፣ በማስተዋልና በትጋት እንድትወጣ "ጾምና በዐሉ የማይዳሰስ አስተዋሽ ምልክት" ይሁንልህ እላለሁ። ከማስታወስ በዘለለ እንደ አንድ ማኀበረሰብ በየዐመቱ  ሃላፊነቱን ስለመወጣት ለመምከርና ለመመካከር ዐይነተኛ መሰባሰቢያ መድረክ ሆኖ ያገለግልሃል። ከወቅቱ ጋር የተገናዘበ  የድርጊት መርሀ-ግብር ለማውጣትም ዕድል ያስገኝልሃል። ስለዚህ  "ጾሙና በዐሉ" እንድትሳተፍም አደራዬን አኖራለሁ። "ጾሙና በዐሉ" እያስታወሰህ ኅላፊነቶቹን  እንደተጠቀሰው እየተወጣህ ብትኖር የአማራ ህዝብና ዎገኖቹን ንቁ አኗኗር (በአጭሩ "አዎን"አዊ" = አዎናዊ አኗኗር) እየኖርክ ነው ማለት እችላለሁ። "" የሚለው "አማራ ሕዝብን" "" ዎገኖቹን" "" ደግሞ "ንቁ" የሚለውን ቃል እንደወከሉ ልብ ይሏል። ይኸንኑ አዎናዊ አኗኗር እንደ አንድ ማህበረሰብ ስትኖር ለራስህ፣ ለየምትኖርበት ማህበረሰብና ለኢትዮጵያ እንዲሁም ለጎረቤቶቿ በረከት ትሆናለህ ብዬ አምናለሁ።ይህ አዎናዊ አኗኗር አዎንታዊ አኗኗር  እንደሆነም ለመገንዘብ አዳጋች አይሆንም። 

2."ጾሙና በዐሉ" ተቀላቅሎ (በወል) ስለማክበር

"ጾሙና በዐሉ" የተተለመው እንደ የአቅሙና፥ እንደ የዝንባሌው ወይም ኅሊናው እንደሚፈቅደው እነዚህን አራት ግዙፍ  ኃላፊነቶችን መወጣት የሚገባው (ነፍስ ያወቀ ማለት ነው) የዐማራ ሕዝብና ዎገኖቹ ሁሉ ኦርቶዶክሱ፣ ሙስሊሙ፣ ወንጌላዊ አማኙ፣ ካቶሊኩ፣ ይሁዲ እምነት ተከታዩ፣ ሃይማኖት የሌለው፥ ወዘተርፈ  በወል ተቀላቅሎ (በእሳቦቱ እንደሚብራራው አስተዋሽያዊ እንጅ ሃይማኖታዊ አይደለምና) እንዲሳተፍበት ው።ስያሜውም  የዐማራ  ሕዝብና  ዎገኖቹን "ኅላፊነቱን አስታዋሽ ጾሙና  በዐሉ" ወይም  የአማራ ሕዝብና ዎገኖቹን ኅላፊነቱን አስታዋሽ ባሕላዊ ምልክቱይባላል። ከላይ ከተገለጠው አኗኗር ጋር ለማያያዝና እንዲሁም በአጭሩ ለመግለጥ እንዲያመች  "አዎን ጾምና በዐሉ" ወይም "አዎን ምልክቱ" ቢባልም ይቻላል። የዐማራን ሕዝብ ከዎገኖቹ ያለውን ትሥሥር የዘነጉቱ ወይም ዎገንነቱን ያልተቀበሉቱ  ወይም አጠራሩን ያቀላጠፉት የሚመስላቸው አንዳንዶች "ዐማራው ምልክት" ማለት ይቀናቸው ይሆናል።  

የሚውልበት ቀን ከአድዋ ድል በዐል በፊት ባለው የመጀመሪያ ቅዳሜ በየዐመቱ ነው።እንደሚታወሰው የአድዋ ድል የዐማራ ሕዝብ እርስ በእርሱ እንዲሁም  ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ዎገኖቹ ጋር አብሮና ተባብሮ ድንቅ ታሪክ የሠራበት የቅርቡ አጋጣሚ ነው። ያንን ሁኔታ የመናፈቄ ልክ ነው ይኸንን ጊዜ ያስመረጠኝ።

3. ዎገኖች የሚለውን ቃል  ስለማብራራት፦

 ዎገኖች የሚለውን ቃል ጥቅም ላይ ያዋልኩት የዐማራ ሕዝብ አስተሳሰብ ነው ብዬ ባመንኩት ስሜት ነው።የዐማራ ሕዝብ በጋብቻ፣ በመዋለድ፣ በጉርብትና፣ በባሕልና በታሪክ ከእርሱ ጋር ሲያያዝና ሲተሳሰር የኖረውን ሕዝብ ሁሉ ጎሳ፣ ነገድ፣ ውህድ፣ ቋንቋ፣ ሃይማኖት ሳይል ወይም ብሎ ሳይጠይቅ በዘልማድ የኢትዮጵያና የኤርትራ ዲያስፖራ በመባል የሚታወቁትን የልጅ ልጆቻቸውን ጨምሮ ዎገኖቼ ናቸው፣ እኔም ዎገናቸው ነኝ እንደሚል ይታወቃል። የእነርሱም አጸፋ ተመሳሳይ ወይም ተመጣጣኝ  ሲሆን ለዎገንነታቸው ግር የሚል ጉዳይ አይኖርም። 

4. "አዎን ድምጽ" "Awon Dimts" ማኅበራዊ ሚዲያ

ስለ "ጾምና በዐሉ" ዝርዝር ጉዳዮች ማለትም

ከኃላፊነቶቹ (የዐማራ ሕዝብና ዎገኖቹ ተልዕኮች ማለት ይቻላል) ጋር ስለመገናኘቱ 

ሃይማኖትንና እምነትን ማስታረቅ ሳያስፈልግ ተደባልቆ መጾምና በዐሉን ለማድረግ ስለመቻሉ 

›  "ጾሙና በዐሉ" ሰሞን ሊከናወኑ ስለሚችሉ ሥራዎች

"ጾሙና በዐሉ" ስለሚሰመርባቸው (ስለሚደምቁ) "የተወራረሱ እሴቶችና ታላሚ በረከቶች "

ተገማች ስለሆኑ ጥያቄዎች መልሳቸው 

በአጠቃላይ "አዎናዊ" አኗኗሩ ልዩ ልዩ ጉዳዮች  "አዎን ድምጽ" "Awon Dimts" ማኅበራዊ ሚዲያ የሚነሱ ይሆናሉ። አስተያየት እንዲሰጥባቸው፥ ውይይት እንዲደረግባቸውም ይበረታታል።

5ኛ፣ መልካም ፈቃድን ስለ መጠየቅ፦ 

 በዐማራ ሕዝብና ዎገኖቹ መኻል ወይም የዐማራ ሕዝብንና ዎገኖቹን የሚያገለግሉ

ብጹአን ጳጳሳት መነኮሳት፥ ካህናት፥ ዲያቆናት፥ መምህራን እንዲሁም ሌሎች (የካቶሊክንም ይጨምራል)

የተከበሩ ሼኾች፣ ኢማሞች፣ ኡስታዞች ሌሎችም

የተከበሩ ቄሶች- ፓስተሮችና-የወንጌላውያን ዘማሪዎች፥ ሌሎችም አገልጋዮች 

የተከበሩ ራቢዎች 

የተከበሩ የአገር ሽማግሌዎችና እናቶች

መልካም ፈቃዳቸውን ላግኝና ይህን አዲስ አስተሳሰብንና አሠራርን የሚመሠርተውን "ጾሙና በዐሉ" ይፋዊ እንዲሆን እንዲሁም በየሚደመጡበት ማኅበረሰብ እንዲታወቅና የዐማራ ሕዝብና ዎገኖቹ እንዲሳተፍበት በማትጋቱ እንዲተባበሩኝ በታላቅ አክብሮትና ትህትና፣ ከልቤ እጠይቃለሁ። ከተጠሩለት መንፈሳዊ አገልግሎት በተጓዳኝ ለዚህ ጾምና በዐል የሚኖራቸው ድጋፍ ለዐማራ ሕዝብና ዎገኖቹ ንቁ አኗኗር የሚደረግ ድጋፍ ይሆናል።

ማኅበራዊ አንቂዎች፥ ተሟጋቾችና፥ መገናኛ አውታሮች ጉዳዩን በማስተዋወቅ እንዲደግፋኝም በተመሳሳይ ሁኔታ ላስቸግራቸው እወዳለሁ።

በአማራ ሕዝብና ዎገኖቹ መኻል ወይም ለዐማራ ሕዝብና ዎገኖቹ የሚሠሩ የፖለቲካ ሠራተኞችም ይኸንኑ ቢያበረታቱ ለዐማራ ሕዝብና ዎገኖቹ ዘላቂ ሥራ እንደሠሩለት ስለሚቆጠር በአድናቆት እንደሚነሡ ያለኝን እምነት እገልጻለሁ።

ለመደምደም፦ "በጾሙና በዐሉ" አስታዋሽነት በህበረት፣ በማስተዋልና በትጋት ኅላፊነቶቹን እንወጣ በሌላ አገላለጽ አዎናዊ አኗኗርን እንኑር  በማለት ለዐማራ ሕዝብና ዎገኖቹ አደራዬን አሰምርበታለሁ። 

የአብርሃም አምላክና አምላካችን በቸርነቱ ያሳካልን። አሜን!

በትዕግሥት ስለተከታተልከኝ አመሰግናለሁ

ቸር እንሁን

ባንቱ ገብረማርያም  

"አዎን ድምጽ"

bantge@yahoo.com

ማስታወሻ፡

 ስለአስተዋሽ ጾምና በዐሉ ጥያቄና መልስ የሚለውን ቢያነቡ ምናልባት የእርስዎም ጥያቄ ይኖርበትና መልስን ሊያገኙበት ይችላሉ።ስለዚህ  ሊንኩን ከፍተው 

https://www.blogger.com/blog/post/edit/





Comments

Popular posts from this blog

የድንግል ማርያም ክብሯና ዘላለማዊ ድንግልናዋ

የድንግል ማርያም ክብሯና ዘላለማዊ ድንግልናዋ (1)  ድንግል ማርያምን ስለማክበር (2) ለጥያቄዎች መልስ (ሀ) ድንግሊትን ‘የወይን ግንድ (ተክል)’ና የ ‘ሕይወት በር’ የሚል ማዕረግ  ለምን እንሰጣታለን? (ለ) ወደ ድንግል ማርያም መጸለይ ትክክል ነው ወይ? (3) የድንግል ማርያም ድንግልና ዘላለማዊነት (4) ለተቃራኒ አስተያየቶች መልስ (ሀ) “የመጀመሪያ ልጇን” የሚለው ሐረግ (ለ) “ሚስትህ” የሚለው ሐረግ (ሐ) “አብረው ከመሆናቸው በፊት ጸንሳ ተገኘች” (መ) “የመጀመሪያ ልጇን እስክትወልድ አላወቃትም” (ሠ)  “ወንድሞቹ” የሚለው ሐረግ   የቅድስት ድንግል ማርያም  ክብሯ (1) ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ድንግል እመቤታችንን አያከብሩም፤ ደግሞም እንድታማልድላቸውም (እንድትማልድላቸውም)  አይጠይቋትም።ከእነርሱ ወገኖች አንዳንዶቹ እንዲያውም ጫጩቱ ከተፈለፈለ በኋላ ዋጋ ከሌለው የዶሮ እንቁላል ቅርፊት ጋር እስከሚያመሳስሏት ይደርሳሉ።ይህ የተጋነነ ማቃለል የመጣው ምናልባት ሮሜዋውያን ካቶሊኮች የተጋነነ ማክበር ስለሚያከብሯት ለዛ ተቃርኖ ከማሳየት አዝማሚያ ሊሆን ይችላል። ስለዚህም ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን አንዱንም የእርሷን በዓል አያከብሩም።  (2) አንዳንዶቹ የፕሮቴስታንት ወገኖች ድንግል ማርያምን “እህታችን” ይሏታል። (3) በተጨማሪ አንዳንዶቹ ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ጌታ ኢየሱስን በድንግልና ከወለደች በኋላ ከዮሴፍ ጋር ጋብቻዋን ፈጽማለች፤ የ‘ኢየሱስ ወንድሞች’  ወይም የ’ጌታ ወንድሞች’ ተብለው የተጠሩ ልጆችን ወልዳለች ይላሉ።  (4) ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ቤተክርስቲያናችን ለድንግል እመቤታችን የሰጠቻቸውን አንዳንድ የማዕረግ ስሞችም ይቃወማሉ።  (5) ድንግልን ያለማክበራቸው አንዱ...

Comparative Theology የነገረ መለኮት ንጽጽር (በኦርቶዶክስና በፕሮቴስታንት)/ በብፁዕ ወቅዱስ ፖፕ ሲኖዳ ሳልሳዊ

 የነገረ መለኮት ንጽጽር  (በኦርቶዶክስና በፕሮቴስታንት): የወደደ  ሁሉ በነጻ እንዲጠቀምበት ተፖስቷል። ይሁን እንጂ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ስለሆነ በየትኛውም መልኩ ለንግድ እንዲውል አልተፈቀድም። ልዩ ልዩ መግቢያ የሚለውን መጀመሪያ ካነበቡ በኋላ የተቀረውን በተመረጠው ቅደም ተከተል ማንበብ ይቻላል። ልዩ ልዩ መግቢያ   ጥምቀት   ትውፊት (ወግና ልማድ)   መካከለኝነት   ጾም የድንግል ማርያም ክብሯና ዘላለማዊ ድንግልናዋ መንፈሳዊ ስጦታዎችና በልሳኖች የመናገር ስጦታ   ሥርዐት ንስሐ

ጥምቀት

  ጥምቀት       (1) የጥምቀት ፍቱንነቱ (2) ማጥመቅ የካህን ተግባር ነው (3) የጥምቀት አስፈላጊነቱ (4) ጥምቀት በመንከር (በመጥለቅ) (5) የልጆች (የሕጻናት) ጥምቀትሳቦች (6) ተቃውሞዎች   ጥምቀት   በእኛ በኦርቶዶክስና በፕሮቴስታንቶች መኻል ጥምቀትን በተመለከተ ያሉት ልዩነቶች የጥምቀትን ትምህርት በአምስት ጉልህ   ፍሬ ነገሮች ሥር አጠቃሎ መነጋገር ይቻላል። (1)     የጥምቀት   አስፈላጊነቱ   ምንድነው? ፍቱንነቶቹስ (ጠቀሜታዎቹስ) ምንድናቸው? ኦርቶዶክስ ጥምቀት ‘ድኅነት’ን፣ ‘መንጻት’ን፣ ‘መጽደቅ’ን፣ የ‘ሕይወት መታደስ’ን እና በ’ክርስቶስ አካል አባል’ መሆን’ን መቀበያ መንገድ ነው ብላ ታምናለች። የፕሮቴስታንት ቤተ እምነቶች እንደሚሉት እነዚህን   መቀበያው “እምነት” ብቻ ነው። በ እምነት ብቻ መሆኑ ትክክል ከሆነ ታዲያ የጥምቀት አስፈላጊነቱ ምኑ ላይ ነው? የክርስትና ምልክት ብቻ መሆኑ ነውን? ወይስ “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው” (ማቴ 28:19-20) የሚለውን የጌታን ትዕዛዝ መታዘዝ ብቻ መሆኑ ነው? (2 ) ማነው ማጥመቅ ያለበት? በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጥምቀት የሚከናወነው በካህን ብቻ ነው። ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ግን የሰውን ክህነት ጨርሶ አይቀበሉም። ስለሆነም በእነርሱ ቤተ ክርስቲያን የሚያጠምቀው ካህን ወይም ቄስ ያልሆነ አገልጋይ ነው።   ይህ አገልጋይ የቤተክርስቲያኒቷ ሽማግሌ ወይም ሴት ሽማግሌ (የሴቶችን ሽምግልና ...