Skip to main content

Posts

Showing posts from May, 2026

“ቋርፍ“ን ይደግፍ ይሆን?

ዓይነ ምድር መድኃኒት? የሰው ዓይነምድር በአፍ ተጠጥቶ ወይም ተውጦ ለተቅማጥ ፣  በምግብ ለተመረዘ  ሆድ እና በአጠቃላይ ለሆድ  ህመምና ለሌሎችም ሕመሞች  ባሕላዊ መድኃኒት  ሆኖ ያገለግል ነበር።  በዘመናዊ መድኀኒትም አግባብ ተበጅቶለት አገልግሎት  ይሰጣል። ለሙሉ መረጃ እንግሊዝኛውን ያንብቡ።   This is what I got from AI  Ancient Chinese medical texts from the 4th century CE describe using fresh or fermented human stool to treat severe diarrhea, food poisoning, and abdominal disease. This remedy—sometimes called “yellow soup”—was administered orally and intended to restore gut balance. Modern research confirms these records and identifies them as early examples of microbiome-based therapy. ccjm.org +1 📜 What the historical sources say 1. Ge Hong (葛洪) and early documentation • In the Eastern Jin dynasty (approx. 300–400 CE), Ge Hong’s Zhou Hou Bei Ji Fang recorded treating food poisoning and severe diarrhea by having patients ingest human fecal suspensions. ResearchGate 2. “Yellow Soup” / Huanglong Decoction (黄龙汤) • Modern scholarship ...

ነቢያዊ ድምጽ /መደምደሚያ

   ነቢያዊ ድምጽ /መደምደሚያ የኢትዮጵያውያ ወንጌላውያንም ሆኑ ጴንጤቆስጣዊ አብያተ ክርስቲያናት የወንጌል አገልግሎታቸው በግል መዳን፣ ቅድስና፣ በመከራ መታገስ እና በሰማይ ተስፋ ዙሪያ ያተኮረ ነው። ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፍትህን አያነሳም። ይህ አካሄድ ወንጌልን   ከአሜሪካና ከአውሮፓ ካመጡልን ወግ አጥባቂ ሚሲዮናውያን የተወረሰ ነው 1 ። ደርግ ሥልጣን ላይ በወጣበት አካባቢ በላቲን አሜሪካ የታየው የሊበሬሽን (ነጻ የመውጣት) ቲዎሎጂ 2 ወደ ኢትዮጵያ አልገባም። ገብቶ ቢሆን ኖሮ በሚሲዮናውያኑ መር ወንጌል አገልግሎቱ ላይ ማህበረሰብን መለወጥ ይታከልበት ነበር ማለት ስህተት አይሆንም። ያንን ያመለጠ እድል አድርጎ ማሰብ ይቻላል። በዚያኑ ወቅት የቄስ ጉዲና ቱምሳም “ሁለንተናውን ሰው” ማገልገል የሚለው ነገረ መለኮት የምዕራቡ ነገረ መለኮት በኢትዮጵያ ሁኔታ የጎደለውን እንዲያሟላ መንገድ ከፋች ነበር 3 ። ይሁን እንጂ መካነ ኢየሱስ በወቅቱ ይኸን ለመቀበል ያልተዘጋጀች ስለነበርና ታሪካዊ ሁኔታ ባለማመቸቱ ተጨናግፏል። የባከን እድል ነው ማለት ይቻላል። በደርግ ዘመን ቤተክርስቲያን ብትሰፋም በሚሲዮኑ ከተተለመው መሥመር አልወጣችም። በሕዝባዊ ጉዳይ መግባት ለሞት የሚያደርስ ስለነበርም ዝምታውን ከመሞት የመሰንበት ዘዴ ሆኗት ነበር 4 ። ከደርግ መውደቅ ወዲህም አካባቢው በዛው በግል ድኅነት ዙሪያ ተወስኖ ለመሥራት ነጻነት ይኑር እንጂ በማኅበራዊ ጉዳይ ለመግባት አመቺ ሁኔታም አልነበረም። በእርግጥ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የሃይማኖት ነጻነቱን በአደባባይ ሳይቀር ፕሮግራም ማድረግ እስከሚቻል ድረስ አስፍተውታል። ታዲያ ምን ያደርጋል እንደ ተቃውሚዎቻቸው ግምገማ ከሆነ ቤተ እምነቶችን መልሰው ካልተቆጣጠርኳችሁ ይላሉ 5 ። በካውንስሉ...

ዘፈኑን እኮ ወንጌል አለው? አልሳተም ትላላችሁ?

  ዘፈኑን እኮ ወንጌል አለው? አልሳተም ትላላችሁ? ዘፈኑን “ወንጌል ነው” ማለቱ መሳት አይደለም። የተቃወሙት ሰዎች ዶክተሩ ዘፈኑን ወንጌል አደረገ ብለው ነው የተረዱት። እኔ ግን እንዲህ እላለሁ፦ “ማኀበራዊ ወንጌል” 1 የሚለውን አጠራር ዛሬ እጅግም አንጠቀምበትም። ምክንያቱም ከስሙ ጋር የሚነሱ ያልተፈለጉ ክርከሮችን ለማስቀረት ነው። ይሁን እንጂ እንደ በርካታ የፕሮቴስታንት አሰተማሪዎች ወንጌልን ከማህበራዊ ፍትሕ መነጠል አይቻልም። የተራራው ስብከትም ይሁን የመጥምቁ ዮሐንስ የ“ንስሐ ግቡ” መልዕክትም በግልጽ ሁኔታ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ግንኙነታዊ ፍትሕን የሚያስተምር መሆኑን የፕሮቴስታንት አስተማሪዎች ያስረዳሉ 2 ። ይህንን አመለካከት በመቀበል የኢየሱስ ትምህርት በግል ሕይወት ብቻ የሚወሰን ሳይሆን በማህበራዊ ፍትሕ ላይም ግልጽ ጥሪ እንደሚያቀርብ መመልከት ይቻላል። በእርግጥ ይህን የማይቀበሉ ሌሎች የተከበሩ አስተማሪዎችም አሉ፣ ግን ሁለቱም ወንጌልን ከፍትሕ አያፋቱትም 3 ። ስለዚህ እውነት፣ ወይም ፍትሕ ወይም ትክክለኛው ሞራል በወንጌል መሰል ዘፈን ቢገለጥ የአግዚአብሔር መልዕክትነቱ አይለወጥም። የወንጌል የሆነው መልዕክት ከቤተክርስቲያን ውጭ ባሉ ሰዎች ሲነገር ያ የአግዚአብሔርን እውነት የሚያስታውሰን ነው 4 ። የቴዎድሮስ ካሣሁንን ዘፈን ወንጌል ነው ብሎ ደረጀ ሲናገር በዘፈኑ የተላለፈው የፍትሕ፣ የፍቅርና የመሳሰሉት መልዕክት የወንጌል አካል ናቸው ማለቱ ሆኖ ይታየኛል። እንግዳ ነገር እንደተናገረ ያህል የሚያስፈራ አይደለም። የግል ድኅነትን ጉዳይ እንዳይውጠው መጠንቀቁ ግን ክፋት የለውም። ግን ግን ይኸንን ሰበብ አድርጎ “የአማራ ሕዝብ ሰቆቃ ይቁም” የሚለውን ድምጽ ማፈን ጨካኝነት አይሆንም? ባንቱ ገብረማርያም ...

ቴዲ አፍሮ መጥምቁ ዮሐንስ ነው?

ቴዲ አፍሮ መጥምቁ ዮሐንስ ነው? ቴዲ አፍሮ ስለ ማህበራዊ ፍትሕ መዝፈኑን ሲያደንቅ ዶክተር ደረጀ መጥምቁ ዮሐንስን አድርጎ ስሎታል። መቼም መጥምቁ ዮሐንስ የጌታን መንገድ ጠራጊ እንደነበረ ደረጀ አያውቅም አይባልም፣ የወንጌል ማዕከሉ የኃጢአተኛ ድኅነት መሆኑንም ይረሳል ተብሎ አይታሰብም። ነገር ግን ጥቂት የማይባሉ ፕሮቴስታንቶች የዮሐንስ “ንስሐ ግቡ” ስብከት የፍትሕ መልዕክትን ያካትታል ብለው ያምናሉ 1 ። ይህንን አመለካከት በመቀበል የዮሐንስ መልዕክት የፍትሕ ጥሪን እንደሚያካትት መረዳት ቀላል ይሆናል። ስለ ፍትሕን ማንም ተናገረው ማንም ያው የእግዚአብሔርን ሓሳብ መግለጡ ነው። ቴዲ አፍሮም በዘፈን መልክ ቢያቀርበው ያው የእግዚአብሔር እውነት ነው። ስለ እግዚአብሔር ፍትሕ ከቤተክርስቲያን ውጭ ያሉ ሲናገሩት የእግዚአብሔር እውነትነቱን ያጣል ማለት አይደለም። አባቶች ከቤተክርስቲያን ውጭ ያሉ ሰዎች የእግዚአብሔርን እውነት ሊናገሩ የሚችሉበት ጊዜ እንዳለና ያ ዐይነቱ የእግዚአብሔር እውነት እንደሆነ ያምናሉ 2 ። በአጭሩ ዶ/ር ደረጀ ያለው የቴዲ አፍሮ ዘፈን መጥምቁ ዮሐንስ ያለውንና የተናገረበትን መንፈስ ያስታውሳል ነው። መጥምቁ ዮሐንስ ራሱን ነው ብሎ መጥራቱ አይደለም። እኔ የምረዳው እንደዚህ ነው፤ ከተሳሳትኩ እታረማለሁ። ለማንኛውም “የአማራ ሕዝብ ግፍ እየተፈጸመበት ነው! ይቁምለት” ማለቱ ቀርቶ ይኸን ሰበብ አገኘሁ ብሎ ነገር ማስቀየስ በደለኝነት ነው። ባንቱ ገብረማርያም  ከአዎን ድምጽ                              ግፉ በአማራ ላይ (መግቢያ) “ግፉ ሲበዛ ፣ አፍ ሁሉ...

ፌክ ኢትዮዽያኒሰቶች ከፊቱ ዞር በሉ!

   ፌክ ኢትዮዽያኒሰቶች ከፊቱ ዞር በሉ ! ዶ/ር ደረጀ “ ፌክ ኢትዮጵያኒስቶች “ ሲል - አማራ የአገሪቱን ሥልጣን ተረክቦ እንዲያስተዳድር አለመፈለጋችውን በወፍ ቋንቋቸው ( በምስጢራዊ መግባቢያ ቋንቋቸው ማለት ነው ) የሚናገሩትን ፣ በሥራቸውም የሚገልጡትን ይመስላል።እነዚህ ለአማራው ወደ ሥልጣን መምጣት እንቅፋት እየሆኑ ስለሚያስቸግሩ ገለል እንዲሉ ይፈልጋል።አዎ ከአማራ ፊት ዞር ቢሉለት! እውነት ነው የአማራ ፖለቲከኞች ከአእነዚህ ጋር አብረው እየሠሩ ውጤት እንዳላመጡ እንዳውም እንደተጎዱ ሲወሳ የቆየ ነው።   ዞሮ ዞሮ ግን ዘላቂ መፍትሔው ያለው በአማራው በራሱ እጅ እንደሆነ በማመልከቱ ከዶ/ር ደረጀ ጋር እስማማለሁ።   የመፍትሔው ቁልፍ ያለው በራሱ በኣማራ ዘንድ ነው — ራሱን ከጥፋት መከላከል፣ እኩልነቱን ማረጋገጥ፣ በብልሃት ተጽዕኖ መፍጠር ይኖርበታል። ይህን ብልሃት /ቀመር የማግኘት ኅላፊነት የማንም አይደለም፣ የአማራው የራሱ ነው። በእርግጥ የሌሎችን ድጋፍ   ቢያገኝ ይረደዋል፣ እንደሚያገኝም መጠበቅ መነሻ የሌለው አይደለም። ግን መሠረቱ የራሱ የውስጥ ብልሃት ነው።  ለኢትዮዽያ ሲጠቅም የኖረው አሠፋፈሩና ከብዙ ብሔሮች ጋር በፍቅር የመኖር ሥርዐቱ የህልውና ትግሉን ለጊዜው ጠመዝማዛ ያደረገው ይመስላል። ብቻ ይዋል ይደር እንጂ ይህም ቢሆን ለበረከቱ ይሆናል። በሌላ በኩል ግን ዶ / ር ደረጀ   ከአነጋገሩ ለአውነተኛ ኢትዮጵያኒስቶች ስስ ልብ እንዳለው መረዳት ይቻላል።እንደ ቴዲ አፍሮ ላሉት ማለት ነው። ለእነርሱ አድናቆትም ድጋፍም አለው። ስለዚህ ምናልባት ...

በእውኑ ካውንስሉ ፖለቲካ ይሠራልን?

  በእውኑ ካውንስሉ ፖለቲካ ይሠራልን?   የኢትዮጵያ   ወንጌል አማኞች ካውንስልን በአስተምህሮ ጤናማ የሚባሉትን ከማይባሉት ጋር ቀይጦ   በአባልነት መያዙ የሚታወቅ ነው። ሰለዚህ ድርጅት ነው ለክቡር ጠ / ሚ ፖለቲካ መሣሪያ መሆኑን ዶ / ር ደረጀ   በግልጽ የተናገረው ።   አዎ በወንጌላውያኑ በራሳቸው ተቋቋመ ቢባልም በተግባር ጠ / ሚ የወንጌል አማኞችን ለራሳቸው ለማሰለፍ ተጠቅመውበታል ቢባል ስህተት አይመስለኝም።  ለአእርሳቸው የሚሆን ፖለቲካ እየሠራ ነው። እኔ እንደ ተከታተልኩት ከሆነ በተቃራኒው ተቃዋሚዎቹ   ከወንጌል አማኞች ድጋፍን ለማግኘት ሲሠሩ አይታዩም። ብዙዎቹ ብልጽግና ወንጌልንና ሐሰተኛ ነቢያቶችን ተገን አድርገው ፕሮቴስታንቶችን ለመውቀስ ብቻ ይበረታሉ   እንጂ “ ጸልዩልን ”  እንኳ ብለው   አልቀረቡም።   ይህ ጉድለታቸው የአሁኑን   መንግሥት ለመተካት ተዘጋጅተናል፥   ብቁ ነን በሚሉበት ጊዜ ምናልባት ይታያቸው ይሆናል።  የመንግሥት ወገን ሆኖ ነው እንጂ አዎ ካውንስሉ ፖለቲካ ይሠራል። ወደ ዶ / ር ደረጀ ከበደ ሐሳብ ልመለስና ካውንስሉ የዶ / ር አብይ አገልጋይ ነው ማለቱ እስካሁን በአንዳንዶች ሲነገር የቆየን የሚደግም ነው ። ሲባል   መቆየቱን ያልሰማ   ወንጌላዊ አማኝ ካለ አሁን ይሰማል   ማለት ነው። ከዚህ በኋላ ካውንስሉን እንደ ክርስቲያን ማኅበር ብቻ አድርጎ ማየት ያስቸግርም ይሆናል። የሚደግፈውም ሆነ የሚቃወመው የፖለቲካ ሚናው...