ፌክ ኢትዮዽያኒሰቶች ከፊቱ ዞር በሉ!
ዶ/ር ደረጀ “ፌክ ኢትዮጵያኒስቶች “ ሲል - አማራ የአገሪቱን ሥልጣን ተረክቦ እንዲያስተዳድር አለመፈለጋችውን በወፍ ቋንቋቸው (በምስጢራዊ መግባቢያ ቋንቋቸው ማለት ነው) የሚናገሩትን ፣ በሥራቸውም የሚገልጡትን ይመስላል።እነዚህ ለአማራው ወደ ሥልጣን መምጣት እንቅፋት እየሆኑ ስለሚያስቸግሩ ገለል እንዲሉ ይፈልጋል።አዎ ከአማራ ፊት ዞር ቢሉለት!
እውነት ነው የአማራ ፖለቲከኞች ከአእነዚህ ጋር አብረው እየሠሩ ውጤት እንዳላመጡ እንዳውም እንደተጎዱ ሲወሳ የቆየ ነው።
ዞሮ ዞሮ ግን ዘላቂ መፍትሔው ያለው በአማራው በራሱ እጅ እንደሆነ በማመልከቱ ከዶ/ር ደረጀ ጋር እስማማለሁ። የመፍትሔው ቁልፍ ያለው በራሱ በኣማራ ዘንድ ነው—ራሱን ከጥፋት መከላከል፣ እኩልነቱን ማረጋገጥ፣ በብልሃት ተጽዕኖ መፍጠር ይኖርበታል። ይህን ብልሃት /ቀመር የማግኘት ኅላፊነት የማንም አይደለም፣ የአማራው የራሱ ነው። በእርግጥ የሌሎችን ድጋፍ ቢያገኝ ይረደዋል፣ እንደሚያገኝም መጠበቅ መነሻ የሌለው አይደለም። ግን መሠረቱ የራሱ የውስጥ ብልሃት ነው።
ለኢትዮዽያ ሲጠቅም የኖረው አሠፋፈሩና ከብዙ ብሔሮች ጋር በፍቅር የመኖር ሥርዐቱ የህልውና ትግሉን ለጊዜው ጠመዝማዛ ያደረገው ይመስላል። ብቻ ይዋል ይደር እንጂ ይህም ቢሆን ለበረከቱ ይሆናል።
በሌላ በኩል ግን ዶ/ር ደረጀ ከአነጋገሩ ለአውነተኛ ኢትዮጵያኒስቶች ስስ ልብ እንዳለው መረዳት ይቻላል።እንደ ቴዲ አፍሮ ላሉት ማለት ነው። ለእነርሱ አድናቆትም ድጋፍም አለው። ስለዚህ ምናልባት ደረጀን ለአማራ ብቻ ተሟጋች አድርጎ ማየት አይገባ ይሆን? እላለሁ።
አሁን አገሪቷን በማስተዳደር ላይ ያሉትን ግን ደረጀ “ለፌክ ኢትዮጵያዊስትነት ” ማዕረግ እንኳ ያበቃቸው አይመስልም።
ምን አደከማችሁ ይህን ሁሉ የነካካው ያው የአማራው ሰቆቃ እንዲቆም ካለው ጥልቅ ፍላጎት የተነሳ ዙሪያ ገባውን ለማስቃኘት ይመስለኛል።ምን ትላላችሁ? ተሳሳትኩኝ?
ባንቱ ገብረማርያም
ከአዎን ድምጽ
- ግፉ በአማራ ላይ (መግቢያ)“ግፉ ሲበዛ ፣ አፍ ሁሉ ሲዘጋ ፣ ያኔ ነቢያዊ ድምጽ ይገኝ ፡ ክፍል 1
- በሕይወቱ ሊበረታ ነው ምኞቱበሕይወቱ ሊበረታ ነው ምኞቱ
- የተለወጠ ክርስቲያን ንግግር ነው?የተለወጠ ክርስቲያን ንግግር ነው?
- ከተደራጁ ሃይማኖቶች እንውጣን?ከተደራጁ ሃይማኖቶች እንውጣን?
- በእውኑ ካውንስሉ ፖለቲካ ይሠራልን?በእውኑ ካውንስሉ ፖለቲካ ይሠራልን?
- ፌክ ኢትዮጵያኒስቶች ከፊቱ ዞር በሉፌክ ኢትዮዽያኒሰቶች ከፊቱ ዞር በሉ!
- ቴዲ አፍሮ መጥምቁ ዮሐንስ ነው?ቴዲ አፍሮ መጥምቁ ዮሐንስ ነው?
- ዘፈኑን ወንጌል አለው! አልሳተም?ዘፈኑን እኮ ወንጌል አለው? አልሳተም ትላላችሁ?
- ነቢያዊ ድምጽ (መደምደሚያም) ነቢያዊ ድምጽ /መደምደሚያ
Comments
Post a Comment