Skip to main content

ግፉ በአማራ ላይ፡

“ግፉ ሲበዛ ፣ አፍ ሁሉ ሲዘጋ፣ ያኔ ነቢያዊ ድምጽ ይገኝ 

ማስታወሻ 

ከወንጌል አማኝ  ዘማሪዎች መኻል ዘማሪ ዶ/ር ደረጀ ከበደ የቴዲ አፍሮን ’ኢቶሪካ’ የተሰኘውን ዘፈን ከአደመጠ በኋላ በአድናቆት ተናግሮለት ነበር። ማድመጡም የአድናቆት ንግግሩም ምላሽ ጎርፎለታል። እኔም በዚያ ዙሪያ ያለኝን ልወረውር ነው።

ጽሁፌ የማንኛውንም ብሔር ወይም ብሔረሰብ ችግር ለማሳነስ ወይም ዋጋ ላለመስጠት የተጻፈ አይደለም። በተለያዩ ክልሎች የሚታዩ ህመሞች እንዳሉ እና ሁሉም ሰው ህመም እንደሚሰማው እሰማለሁ። የእነዚህ ህመሞች መድኃኒት በአማራ ጥያቄ ባለመመለስ ውስጥ ተቆልፎበታል ብዬ አምናለሁ።

 የአማራን ጥያቄ መመለስ የሁሉንም መድኃኒት ክተቆለፈበት ሥፍራ የማውጣት ያህል ነው። ለዚህም ጭምር ነው የአማራውን ግፍ ትኩረት እንዲያገኝ በማድረጉ የዶክተር (ዘማሪ) ደረጀ ክበደን ንግግር የደገፍሁ።

መግቢያ

 ግፉ በአማራ ላይ፡ 

አዲሱን ሥርዐት በመገንባት ሰበብ፣ አሮጌውን ለማፍረስ ባለው ሂደት አማራ ላይ ግፍ እየተሠራ መሆኑ የሚታወቅ ነው። ይሀን “ግፍ ተው! ይቅር” ብሎ የሚናገር ድምጽ ከታዋቂ ወንጌል አማኞቹ መኻል አልሰማሁም። ሌሎቹ ቢቀሩ በአማራ ባሕል ያደጉ እንኳ ትንፍሽ አላሉም። አንዳንዶቹ እንዳውም “ሽር ጉዳቸው” ክአማራ አስጨናቂዎች ጋር ነው። አንድ ፓስተር ብቻ በደምብ የተደራጀ ልመና ስለ አማራውና ስለተቀሩትም አቅርቦ አድምጬአለሁ። እርሱም ለምን እንደሆነ በማላውቀው ምክንያት ቪዲዮውን ያነሳው ይመስላል (ሳልሰማ ወይም ሳላይ ያመለጠኝ የለም ለማለት ግን ዓይነ አፋር ነኝ)።

 በዚህ ሁኔታ ውስጥ፣ ስለ አማራው የሚጮህ ድምፅ ሆኖ ስላገኘሁት ነው፣ “ዶ/ር ዘማሪ ደረጀ ከበደን “የእኔ ባትሆን ይቆጨኝ ነበር” ያልኩት። እርሱን ስደግፍ ዎገኖቼ እንደመሆናቸው መጠን የሌሎች ብሔር-ብሔረሰቦች ህመም ሳይሰማኝ ቀርቶ አይደለም። ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ የጭንቁን ገፈት እየቀመሰ ያለው አማራው ስለሆነና ¹ (ስለመሆኑ የግርጌ ማስታወሻውን ይመልከቱ) ያ መፍትሔ ሲያገኝ የሌላውም የማግኘት ዕድሉ ከፍ ይላል ብዬ ስለማምን ነው።

 እስቲ አስቡት ዶክተር ደረጀ ከአማራ አስጨናቂዎች ጋር ተሰልፎ ቢሆን ኖሮ--- በአማራው ላይ የሚደርሰው ተጨማሪ ሰቀቀን --- ያም ይቅር፣ እንደ ብዙዎች ፍላጎት፣ እንደ ጥንቱ ድንቅ መዝሙሩን እየዘመረ ከምንም ነገር ጋር ሳይነካካ ቢኖር ኖሮ? ---የአማራ ሕዝብ ትልቅ ተሟጋች አጣ ማለት ነበር---። ይህን ሳስበው ይሰቀጥጠኛል። እንኳን ለአማራ ተሟጋች ሆነ፣ ሊያውም ደፋር ተሟጋች፣ በትክክለኛው ጊዜ የተገኘ። 

ይህንን በመግቢያነት ካልኩ በኋላ በተናገራቸው አንዳንድ ጉዳዮች ላይ የራሴን ሐተታ በክፍል (ንዑስ ርዕስ) እያደራጀሁ እጽፉለሁ። በተፈለገው ቅደም ተከተል ሊነበብ ይችላል። ከታች ተዘርዝረዋል።

ባንቱ ገብረማርያም 
ከአዎን ድምጽ
 

 በአማራ ሕዝብ የደረሰው ጥፋት (2020 → 2026)

  1. Amnesty International (2020 – Mai Kadra)
    “Amnesty verified the killing of scores of Amhara civilians in Mai Kadra in November 2020.”
    Source: Amnesty International

  2. Human Rights Watch (2021 – Tole Massacre)
    “Over 200 Amhara civilians were killed in the Tole area of Oromia in one of the deadliest massacres documented by HRW.”
    Source: Human Rights Watch

  3. Amnesty International (2021)
    “Amhara civilians have been subjected to unlawful killings, mass displacement, and targeted attacks.”
    Source: Amnesty International

  4. Human Rights Watch (2022 – ‘They Slaughtered Us Like Animals’)
    “Survivor testimonies describe systematic ethnic targeting of Amhara civilians across western Oromia, including mass killings and forced displacement.”
    Source: Human Rights Watch

  5. Human Rights Watch (2022 – Contextual)
    “Government‑backed security forces carried out abuses including arbitrary arrests and displacement targeting Amhara civilians in contested areas.”
    Source: Human Rights Watch

  6. Amnesty International (2022 – New Evidence)
    “Satellite imagery and witness accounts confirmed targeted killings of Amhara civilians in western Oromia and Amhara regions.”
    Source: Amnesty International

  7. OHCHR–EHRC Joint Investigation (2022)
    “The joint investigation documented serious violations, including killings and abuses against Amhara civilians, during the northern Ethiopia conflict.”
    Source: OHCHR–EHRC Joint Investigation

  8. Associated Press (2021/2022)
    “AP documented ethnic attacks driving millions from their homes, including targeted violence against Amhara civilians.”
    Source: Associated Press

  9. Amnesty International (2023 – Forced Evictions)
    “Authorities carried out large‑scale demolitions in Addis Ababa and Oromia towns, leading to forced evictions and displacement of residents, including many Amharas.”
    Source: Amnesty International

  10. Human Rights Watch (2023 – Airstrikes in Amhara)
    “HRW documented unlawful airstrikes and military operations targeting civilian areas in the Amhara region.”
    Source: Human Rights Watch

  11. United Nations Human Rights Council (2023)
    “The Commission received credible reports of violations against Amhara civilians, including extrajudicial killings and enforced disappearances.”
    Source: UN International Commission of Human Rights Experts on Ethiopia

  12. UN Special Rapporteur on Adequate Housing (2023)
    “Urban‑expansion and demolition campaigns around Addis Ababa have resulted in forced evictions disproportionately affecting Amhara residents.”
    Source: UN Special Rapporteur on Adequate Housing

  13. UN OCHA (2023)
    “Large numbers of Amhara civilians have been displaced due to insecurity and targeted violence.”
    Source: UN OCHA

  14. Reuters (2023)
    “Reuters reported that communication blackouts were obscuring widespread violence in the Amhara region, hindering documentation of abuses.”
    Source: Reuters

  15. U.S. State Department (2023)
    “There were reports of ethnically motivated attacks against Amhara civilians, including killings and destruction of property.”
    Source: U.S. State Department – Country Report on Human Rights Practices: Ethiopia

  16. International Crisis Group (ICG)
    “Amhara civilians have suffered from cycles of violence and retaliatory attacks, leading to significant humanitarian suffering.”
    Source: International Crisis Group

  17. Amhara Association of America (2023)
    “More than 9,300 homes belonging primarily to Amhara residents were demolished in Sheger City, causing mass displacement, killings, and widespread human‑rights violations.”
    Source: Amhara Association of America

  18. Lemkin Institute for Genocide Prevention (2023 – Update 1)
    “Ongoing killings of Amhara civilians, drone strikes, and a state of emergency used to silence opposition indicate escalating genocidal violence.”
    Source: Lemkin Institute for Genocide Prevention

  19. Lemkin Institute for Genocide Prevention (2023 – Position Statement)
    “The Institute has documented massacres, forced displacement, genocidal rhetoric, and over two million unaccounted Amharas, describing the situation as an ignored genocide.”
    Source: Lemkin Institute for Genocide Prevention

  20. Danish Immigration Service (2024)
    “Amhara communities around the capital have faced displacement justified under development and urban‑corridor projects, contributing to insecurity and loss of housing.”
    Source: Danish Immigration Service

  21. European Centre for Law and Justice (2024)
    “The ECLJ documented forced displacement of Amharas around the capital, drone strikes on civilians, mass arrests, and extrajudicial killings.”
    Source: European Centre for Law and Justice

  22. Lemkin Institute for Genocide Prevention (2026)
    “The Lemkin Institute remains greatly concerned about the ongoing widespread genocide against the Amhara people, including systematic killings, abductions, sexual violence, and arbitrary detention.”
    Source: Lemkin Institute for Genocide Prevention

Comments

Popular posts from this blog

የድንግል ማርያም ክብሯና ዘላለማዊ ድንግልናዋ

የድንግል ማርያም ክብሯና ዘላለማዊ ድንግልናዋ (1)  ድንግል ማርያምን ስለማክበር (2) ለጥያቄዎች መልስ (ሀ) ድንግሊትን ‘የወይን ግንድ (ተክል)’ና የ ‘ሕይወት በር’ የሚል ማዕረግ  ለምን እንሰጣታለን? (ለ) ወደ ድንግል ማርያም መጸለይ ትክክል ነው ወይ? (3) የድንግል ማርያም ድንግልና ዘላለማዊነት (4) ለተቃራኒ አስተያየቶች መልስ (ሀ) “የመጀመሪያ ልጇን” የሚለው ሐረግ (ለ) “ሚስትህ” የሚለው ሐረግ (ሐ) “አብረው ከመሆናቸው በፊት ጸንሳ ተገኘች” (መ) “የመጀመሪያ ልጇን እስክትወልድ አላወቃትም” (ሠ)  “ወንድሞቹ” የሚለው ሐረግ   የቅድስት ድንግል ማርያም  ክብሯ (1) ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ድንግል እመቤታችንን አያከብሩም፤ ደግሞም እንድታማልድላቸውም (እንድትማልድላቸውም)  አይጠይቋትም።ከእነርሱ ወገኖች አንዳንዶቹ እንዲያውም ጫጩቱ ከተፈለፈለ በኋላ ዋጋ ከሌለው የዶሮ እንቁላል ቅርፊት ጋር እስከሚያመሳስሏት ይደርሳሉ።ይህ የተጋነነ ማቃለል የመጣው ምናልባት ሮሜዋውያን ካቶሊኮች የተጋነነ ማክበር ስለሚያከብሯት ለዛ ተቃርኖ ከማሳየት አዝማሚያ ሊሆን ይችላል። ስለዚህም ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን አንዱንም የእርሷን በዓል አያከብሩም።  (2) አንዳንዶቹ የፕሮቴስታንት ወገኖች ድንግል ማርያምን “እህታችን” ይሏታል። (3) በተጨማሪ አንዳንዶቹ ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ጌታ ኢየሱስን በድንግልና ከወለደች በኋላ ከዮሴፍ ጋር ጋብቻዋን ፈጽማለች፤ የ‘ኢየሱስ ወንድሞች’  ወይም የ’ጌታ ወንድሞች’ ተብለው የተጠሩ ልጆችን ወልዳለች ይላሉ።  (4) ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ቤተክርስቲያናችን ለድንግል እመቤታችን የሰጠቻቸውን አንዳንድ የማዕረግ ስሞችም ይቃወማሉ።  (5) ድንግልን ያለማክበራቸው አንዱ...

ጥምቀት

  ጥምቀት       (1) የጥምቀት ፍቱንነቱ (2) ማጥመቅ የካህን ተግባር ነው (3) የጥምቀት አስፈላጊነቱ (4) ጥምቀት በመንከር (በመጥለቅ) (5) የልጆች (የሕጻናት) ጥምቀትሳቦች (6) ተቃውሞዎች   ጥምቀት   በእኛ በኦርቶዶክስና በፕሮቴስታንቶች መኻል ጥምቀትን በተመለከተ ያሉት ልዩነቶች የጥምቀትን ትምህርት በአምስት ጉልህ   ፍሬ ነገሮች ሥር አጠቃሎ መነጋገር ይቻላል። (1)     የጥምቀት   አስፈላጊነቱ   ምንድነው? ፍቱንነቶቹስ (ጠቀሜታዎቹስ) ምንድናቸው? ኦርቶዶክስ ጥምቀት ‘ድኅነት’ን፣ ‘መንጻት’ን፣ ‘መጽደቅ’ን፣ የ‘ሕይወት መታደስ’ን እና በ’ክርስቶስ አካል አባል’ መሆን’ን መቀበያ መንገድ ነው ብላ ታምናለች። የፕሮቴስታንት ቤተ እምነቶች እንደሚሉት እነዚህን   መቀበያው “እምነት” ብቻ ነው። በ እምነት ብቻ መሆኑ ትክክል ከሆነ ታዲያ የጥምቀት አስፈላጊነቱ ምኑ ላይ ነው? የክርስትና ምልክት ብቻ መሆኑ ነውን? ወይስ “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው” (ማቴ 28:19-20) የሚለውን የጌታን ትዕዛዝ መታዘዝ ብቻ መሆኑ ነው? (2 ) ማነው ማጥመቅ ያለበት? በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጥምቀት የሚከናወነው በካህን ብቻ ነው። ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ግን የሰውን ክህነት ጨርሶ አይቀበሉም። ስለሆነም በእነርሱ ቤተ ክርስቲያን የሚያጠምቀው ካህን ወይም ቄስ ያልሆነ አገልጋይ ነው።   ይህ አገልጋይ የቤተክርስቲያኒቷ ሽማግሌ ወይም ሴት ሽማግሌ (የሴቶችን ሽምግልና ...

Comparative Theology የነገረ መለኮት ንጽጽር (በኦርቶዶክስና በፕሮቴስታንት)/ በብፁዕ ወቅዱስ ፖፕ ሲኖዳ ሳልሳዊ

 የነገረ መለኮት ንጽጽር  (በኦርቶዶክስና በፕሮቴስታንት): የወደደ  ሁሉ በነጻ እንዲጠቀምበት ተፖስቷል። ይሁን እንጂ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ስለሆነ በየትኛውም መልኩ ለንግድ እንዲውል አልተፈቀድም። ልዩ ልዩ መግቢያ የሚለውን መጀመሪያ ካነበቡ በኋላ የተቀረውን በተመረጠው ቅደም ተከተል ማንበብ ይቻላል። ልዩ ልዩ መግቢያ   ጥምቀት   ትውፊት (ወግና ልማድ)   መካከለኝነት   ጾም የድንግል ማርያም ክብሯና ዘላለማዊ ድንግልናዋ መንፈሳዊ ስጦታዎችና በልሳኖች የመናገር ስጦታ   ሥርዐት ንስሐ