ከተደራጁ ሃይማኖቶች እንውጣን?
ዘማሪው ዶ/ር ደረጀ ታሪካዊ ምሳሌዎች እያቀረበ የተደራጁ ሃይማኖቶች ሕዝብን በማሰቃየት ከአምባገነን መንግሥታት ተባባሪ እንደሚሆኑ አስረድቷል።የተደራጀ ሃይማኖት ለራሱም እንደማይመቸው ሲናገር ተደምጧል። ያንን ስሜት ይገልጥ ይሆን በማለት ነው ጥያቄውን ርዕስ ያደረግሁት። ለማንኛውም ስለተደራጁ ሃይማኖቶች የጻፈው መጽሐፍ ለንባብ (ጨርሼዋለሁ ብሏል) ሲበቃ ዝርዝሩን የምናይ ይሆናል።
እስከዚያው ግን ይህን እላለሁ። እኔ እንደሚገባኝ አስጨናቂ የአገር መሪዎች በአነሳሳቸው የቤተ ክርስቲያንን ድጋፍ የሚያስገኝላቸው ነገር ይዘው ነው የሚነሱት።
በዚያን ጊዜ ላላመደገፍ አብያተ ክርስቲያናት አጣብቂኝ ውስጥ ይገባሉ።የሚደግፉት ከባዶ ተነስተው አይደለም ለማለት ነው።
አስጨናቂው ሥልጣን ላይ መደላደሉን ሲያውቅ እውነተኛ ባሕርዩ ይገለጣል፤ያኔ አብያተ ክርስቲያናቱ ከገቡበት ወጥመድ መውጣት ይከብዳቸዋል። መሪዎቹ ለራሳቸውም ለቤተክርስቲያንም “ሕልውና” ብለው አስጨናቂውን መሪ እየደገፉ ይቀጥላሉ።የሚታየው ነገር እንዲህ ነው።
ስለዚህ እኔ መሪዎቹን እንደሰው ስለማያቸው ፍርዴ ቀለል ያለ ነው። ግና ምን ያደርጋል ያለ ኤጲስ ቆጶስ ቤተክርስቲያን አትኖርም። ደህነኞቹን ኤዺስ ቆዾሳት እግዚአብሔር ለአብያተክርስቲያናት ይስጣቸው ከማለት ሌላ ምን ይባላል?
የተደራጁ ሃይማኖቶች ጉዳይ ከተነሳ አይቀር የኦርቶዶክስን ላንሳ። እንደሚታወሰው የዛሬውን አያድርገውና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳውያን አባቶች በየአጥቢያቸው (ፓትረያርኩም በአገር ደረጃ) ፣ ይሸመግሉ፣ ያሰታርቁ፥ ለሰላም ይሠሩ ነበር። እንደ እውቀታቸው መጠን ጎሏል ወይም ጠፍቷል በሚሉት ነገርም ይመክሩ፣ ይገስጹም፣ ሲየስፈልግ ይገዝቱም ነበር። ቤተክርስቲያኒቷ በደርግ ከተደቆሰች ወዲህ ግን እንዲህ ዐይነቱን ነገር “ነጻ ሆና” ለማከናወን እሰካሁን አላንስራራችም።ልጆቿንም አልታደገችም።
ለማንኛውም ከታሪክ በተማረው መሠረት ደረጀ የተደራጁ ሃይማኖቶችን ክፉኛ አብጠልጥሏል።
አነጋገሩ በታሪክ ባገኛቸው መሪዎች ዐይንና አሁን ላይ ያሉትንም ዝምታችውን አይቶ በተደራጁ ሃይማኖቶች ተስፋ መቁረጡን መግለጹ ይመስላል።
በበኩሌ ንግግሩ ለተደራጁ ሃይማኖቶች ለተግሳጽና ምክር የሚሆናቸው ነው ብዬ አስባለሁ። ይህ ማስጠንቀቂያ ለአሁኖቹ ብቻ ሳይሆን ለወደፊት ለሚመጡትም ነው።
በተለይ ፕሮቴስታንቶችን በተመለከተ ስለ ተገፉት ዝምታቸው ለምን እንደሆነ አባሎች መሪዎቻቸውን በግልጽ እንዲጠይቁ የዘማሪው ዘለፋ አጋጣሚ ፈጥሮላቸዋል።- ግፉ በአማራ ላይ (መግቢያ)“ግፉ ሲበዛ ፣ አፍ ሁሉ ሲዘጋ ፣ ያኔ ነቢያዊ ድምጽ ይገኝ ፡ ክፍል 1
- በሕይወቱ ሊበረታ ነው ምኞቱበሕይወቱ ሊበረታ ነው ምኞቱ
- የተለወጠ ክርስቲያን ንግግር ነው?የተለወጠ ክርስቲያን ንግግር ነው?
- ከተደራጁ ሃይማኖቶች እንውጣን?ከተደራጁ ሃይማኖቶች እንውጣን?
- በእውኑ ካውንስሉ ፖለቲካ ይሠራልን?በእውኑ ካውንስሉ ፖለቲካ ይሠራልን?
- ፌክ ኢትዮጵያኒስቶች ከፊቱ ዞር በሉፌክ ኢትዮዽያኒሰቶች ከፊቱ ዞር በሉ!
- ቴዲ አፍሮ መጥምቁ ዮሐንስ ነው?ቴዲ አፍሮ መጥምቁ ዮሐንስ ነው?
- ዘፈኑን ወንጌል አለው! አልሳተም?ዘፈኑን እኮ ወንጌል አለው? አልሳተም ትላላችሁ?
- ነቢያዊ ድምጽ (መደምደሚያም) ነቢያዊ ድምጽ /መደምደሚያ
Comments
Post a Comment