የተለወጠ ክርስቲያን ንግግር ነው?
“የተለወጠ ክርስቲያን እንዲህ ይናገራል?” ብለው በዶ/ር ደረጀ አነጋገር የተበሳጩም አሉ። እኔም በመጀመሪያ እንደዚያ የተሰማኝ ጊዜ ነበር፤ ንግግሩ በጸጋ እንዳልተቀመመ ሊቆጠር የሚችል ነው። ግን አሁን ሳስበው አንዳንዴ በቁጣ መናገር ሳይገባ አይቀርም እላለሁ። ቁጣ የሚገልጠው ግብና ፍላጎት አለው፤ የደረጀም ቁጣ ከዚህ የተለየ አይደለም።
የአማራ ሕዝብ በእቅድ እየተጠቃ እንደሆነ ሰማ—- በማኀበራዊ መገናኛ ተከታተለ—-ከልዩ ልዩ ዐለም አቀፍ ድርጅቶች ሪፖርት አገኘ። ከዚያ በዚህ ሕዝብ ሰለሚደርሰው ግፍ በቁጣ ተናገረ። ግቡ አማራው እንዳይጠፋ፣ ፍትሕ እንዳይጓደልበት፣ ድሃ አማራው እንዳይጉላላ ነው። እንደ ‘ነቢያዊ ጥሪ’ ሊሰማ የሚገባው ድምጽ ነው።
ፍላጎቱ ግልጽ ነው።በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረው የአማራ ሕዝብ ህልውናው ፈተና ላይ ሲወድቅ ፣ግፍ ሲፈጸምበት ክብሩ ሲዋረድ አለመመልከት ነው። ይህ ሁኔታ ተቀልብሶ አማራን እንደገና በክብሩ ማየት ነው።
ወደ ክብር ቦታው ተመልሶ ማየት ነው።
ስለዚህ ንግግሩ ቁጣ ቢመስልም የሚያመለክተው ይኽንኑ ነው። ኃላፊነት ላይ ያሉ ይኸንን ልብ ብለው እልቂቱን የሚያስቀር እርምጃ ይወስዳሉ ካልሆነ ግን ተጠቂው ማህበረሰብ ተባብሮ መፍትሔ ይፈልጋል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።
ስለዚህ በደረጀ የቁጣ አነጋገር መታወክ አያስፈልግም። በእርግጥ ሁልጊዜ ከሆነ ግን ልማድ ብቻ ሆኖ ይቀራል ብዬ እሰጋለሁ። አድማጭ ተመልካቾቼ ከይቅርታ ጋር አንድ ጥያቄ ልጠይቅ፦ይኸንን ሰበብ አድርጎ እየተደቆሰ ላለው የአማራ ሕዝብ ድምጽ ላለመሆን መሸሽ ግን አይደብርም ?
- ግፉ በአማራ ላይ (መግቢያ)“ግፉ ሲበዛ ፣ አፍ ሁሉ ሲዘጋ ፣ ያኔ ነቢያዊ ድምጽ ይገኝ ፡ ክፍል 1
- በሕይወቱ ሊበረታ ነው ምኞቱበሕይወቱ ሊበረታ ነው ምኞቱ
- የተለወጠ ክርስቲያን ንግግር ነው?የተለወጠ ክርስቲያን ንግግር ነው?
- ከተደራጁ ሃይማኖቶች እንውጣን?ከተደራጁ ሃይማኖቶች እንውጣን?
- በእውኑ ካውንስሉ ፖለቲካ ይሠራልን?በእውኑ ካውንስሉ ፖለቲካ ይሠራልን?
- ፌክ ኢትዮጵያኒስቶች ከፊቱ ዞር በሉፌክ ኢትዮዽያኒሰቶች ከፊቱ ዞር በሉ!
- ቴዲ አፍሮ መጥምቁ ዮሐንስ ነው?ቴዲ አፍሮ መጥምቁ ዮሐንስ ነው?
- ዘፈኑን ወንጌል አለው! አልሳተም?ዘፈኑን እኮ ወንጌል አለው? አልሳተም ትላላችሁ?
- ነቢያዊ ድምጽ (መደምደሚያም) ነቢያዊ ድምጽ /መደምደሚያ
Comments
Post a Comment