Skip to main content

በሕይወቱ ሊበረታ ነው ምኞቱ

 በሕይወቱ ሊበረታ ነው  ምኞቱ

/ ደረጀ ከበደ በመዝሙር አገልግሎቱ የነበረበትን ፈተና ተናገረ። ይሁን እንጂ እርሱ በመዝሙሩ በታወቀበት ዘመን  የአገልጋዮች ሕይወት  ለአደባባይ የተገለጠ ነበር። በጊዜው ከሌሎች ዋንኞቻችን የተለየ ነቀፋ ቢኖርበት ኖሮ የመታወቅ እድል ነበረው።ለማንኛውም የውስጥ ትግሉን ከራሱ በላይ የሚያውቅ የለምና "እንደ ዘመርኩት አልኖርኩም" ያለውን እንዳለው እቀበለዋለሁ። 

 ዘፈንን በተመለከተ በዚያው ወደ ዘማሪነት በመጣበት ዘመን "ዘፋኝነት ኃጢአት ነው፣  ዘፈን የሥጋ ሥራ ነው" ብሎ ማመን ጤናማ ትምሀርት ነበር። ጆሮዬ ሳያጣራ ቀርቶ ካልሆነ  በስተቀር  አብዮታዊ መዝሙር አልዘምርም (ያው ዘፈን መሆኑ አይደል) በማለት  መከራን  ተቀብሏል። አሁንም በዩትዩቡ የዱሮውንመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም እንደሚያነብ አሳይቶናል። ዛሬም  ዘፋኝነት ኃጢአት ነው የሚል ፊት ለፊቱ አለ።ስለዚህ ዘፈንን ስለማዳመጥ በወንጌል አማኞች ዘንድ የሰፈነውን ሐሳብ ያውቃል ብል ያልሆነ ነገር በእርሱ ላይ መለጠፍ አይሆንብኝም። 

ታዲያ የቴዲ አፍሮኢቶሪካዘፈንን ማዳመጡ ከምን የተነሳ ነው?

 እንዳለው እንደዘመረው አለመኖሩ ይሆን? የወንድሜን የዮናስ ጎርፌን ሙግት ገዝቶ ይሆንለነገሩ አዲሱ የመጽሐፍ ትርጉምም  ዘፈንን እንደ ቀድሞው  ትርጉም አይገልጠውም።የተለየ ትንተና (commentary) እየተሰጠበትም ይገኛል። ይህ ተጽእኖ አሳድሮበት ይሆን? ነው ወይስእስቲ ቴዲ አፍሮ ምን ብሎ ዘፍኖ ይሆን?” ብሎ በመጓጓት አደመጠው? ለእነዚህ ጥያቄዎች መልሱ ያለው በወንድሜ ደረጀ እጅ ነው።

 ዘፈኑን ያደመጠው ግን አስቦበት መሆኑ ድብቅ አይደለም።ዘፈን ጽድቅ ነውና  አዳምጡ ብሎ አልሰበከንም (ዘፈኑንወንጌል ነው ስላለውበሌላ ክፍል (ንዑስ  ርዕስ) የማነሳው ይሆናል

መዝሙሩና ሥራው አልገጠመም ብሎ ካሳሰበው የራሱ ፓስተር ቀርቦ ሊማከረው፣ ሊጸልይለትና ሊረዳው ይችላል—-በሕይወቱ እንዲበረታ። ያም ሆኖ ከማኀበራዊ መገናኛ እንደሚታየው ያሰቡለት፣ ያዘኑለት ያዘኑበትም እጅግ ብዙ ነፍሳት አግኝቷል።

እኔ ደግሞ ስለ ሕይወቱ ከመመስከሩና ዘፈን ከማዳመጡ ያገኘነው ትርፍ ወይም በጎ ነገር አለ ባይ ነኝ።

  1. እርሱ እንዳደረገው የክርስትና ሕይወታችንን  እንድንመረመርና የምናድግበትን እንድናይ ምክንያት ሆኖናል።

  2. በአስጨናቂዎቻቸው መዳፍ ሥር በወደቁ ወገኖች በተለይም በአማራው ላይ ስለሚደርሰው ግፍ ትኩረታችን ተጨምድዶ እንዲያዝ አድርጓል (በአማራ ስለደረሰው ግፍ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሪፖርቶች ክፍል 1 የግርጌ ማስታወሻ ይመልከቱ)።

  3.  / ደረጀ የእነርሱ ወገን ባለመሆኑ ያዘኑና  የተቆጡ መኖራቸውን አይተንበታል (እንደ ራሴ በማየት ህመማቸውን እረዳለሁ) 

    ባንቱ ገብረመሸርያም

    ከአዎን ድምጽ

                                    

Comments