Skip to main content

Posts

Comparative Theology የነገረ መለኮት ንጽጽር (በኦርቶዶክስና በፕሮቴስታንት)/ በብፁዕ ወቅዱስ ፖፕ ሲኖዳ ሳልሳዊ

 የነገረ መለኮት ንጽጽር  (በኦርቶዶክስና በፕሮቴስታንት): የወደደ  ሁሉ በነጻ እንዲጠቀምበት ተፖስቷል። ይሁን እንጂ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ስለሆነ በየትኛውም መልኩ ለንግድ እንዲውል አልተፈቀድም። ልዩ ልዩ መግቢያ የሚለውን መጀመሪያ ካነበቡ በኋላ የተቀረውን በተመረጠው ቅደም ተከተል ማንበብ ይቻላል። ልዩ ልዩ መግቢያ   ጥምቀት   ትውፊት (ወግና ልማድ)   መካከለኝነት   ጾም የድንግል ማርያም ክብሯና ዘላለማዊ ድንግልናዋ መንፈሳዊ ስጦታዎችና በልሳኖች የመናገር ስጦታ   ሥርዐት ንስሐ
Recent posts

“ከኦርቶዶክስ ወቀሳዬን አነሳሁ-በወንጌላዊ አማኞች ካውንስል ሰጋሁ”

“ከኦርቶዶክስ ወቀሳዬን አነሳሁ-በወንጌላዊ አማኞች ካውንስል ሰጋሁ” አድማጭ ተመልካቾቼ እንደምን ከረማችሁ? ቸሩ መደኅኒዓለም ይመስገነውና  እኔ ደህና ነኝ።            ዛሬ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን መውቀሴን ስለማቆሜ እንዲሁም  በካውንስሉ ስለገባኝ ሥጋቴ አካፍላችኋለሁ። ሐሳቡ የግሌ ነው። ወንጌል አማኞችን በአጠቃላይ ሆነም ፣ አባል የሆንኩባትን ቤተክርስቲያን አይወክልም። ወቀሳዬን በመተዌ ለኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሚጨምርላት ነገር የለም። ባልተወውም የሚያጎድልባት ነገር የለም። ምናልባትም ነገሩን በማንሳቴ ሊቆጡብኝ የሚችሉ ይኖራሉ። ስለወቀሳው የማወጋው በጓዳዬ የማወጣውንና የማወርደውን ወደ ብርሃን ለማውጣት ያህል ነው። ስለ"ወንጌላዊ አማኞች ካውንስሉ" ለመጻፍ የተነሳሁት  ደግሞ  የካውንስሉ ቦርድ በ13ኛ መደበኛ ስብሰባው ያሳለፈው ውሳኔ አሳስቦኝ ነው። ሁለቱን አንድ ላይ ማቅረቤ ግን ተገጣጥሞብኝ ነው። እንደተለመደው በትዕግሥት ተከታተሉኝ! ኦርቶዶክስን መውቀስ ከመተዉ ልጀምር            ከቀደሙትና ዛሬ በሕይወት ከሚገኙት‍ የወንጌል አማኞች መኻል የምቆጠር ነኝ።ታዲያ በዚያ በወጣትነት ዘመኔ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ስደት አድርሳብን እንደነበር አስታውሳለሁ።በግሌ እንኳ ወላጆቼ እንዲቆጣጠሩኝ ክቤተክርስቲያኒቷ ተመክረው ነበር። በተለይም አባቴ ደብተራ በመሆኑ “የቤተክርስቲያን አገልጋይ ልጅ ሆኖ እንዴት የመጤ ሃይማኖት ተከታይ ይሆናል” የሚል ጫና ነበረበት።በጊዜው  አብሬው (ማለትም ከወላጆቼ ጋር) የማልኖር ስለነበር ሊያደርግ የቻለው ነገር አልነበረም።...

ለፓስተር ግርማ ቤካ

ለፓስተር ግርማ ቤካ አድማጭ ተመልካቾቼ እንደምን አላችሁ ? እኔ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁንና ደህና ነኝ። ይህ   የአርሲ ኦርቶዶሳውያንን መገደል በተመለከተ   ለፓስተር ግርማ ቤካ የሚተላለፍ መልእክቴ ነው።   ከታች ልናገርባቸው ያሉትን ጉዳዮች በዩትዩብ ሲናገር የሰማሁት እርሱን ነውና። ይሁን እንጂ ከግርማ ቤካ ሐሳቦች ብዙውን የሚጋሩ ፓስተሮች እንዳሉ እገምታለሁ።ስለዚህ መልዕክቴ ለአንድ ሰው የተላለፈ ቢሆንም፣ ተመሳሳይ ሐሳብ ላላቸውም የሚዛመት ነው። በሌላ በኩል ግን ሐሳቡን ጨርሶ የማይጋሩት   የወንጌል አማኝ ፓስተሮች   እንዳሉም ከግርማ ቤካ ንግግር መረዳት ይቻላል።   የአርሲ ኦርቶዶክሳውያን ጭፍጨፋ አሳሳቢ ነው። ጉዳዩን የሰብዐዊ መብት ተሟጋቾች እንዲይዙትና ክትትል እንዲያደርጉበት ተስፋ አደርጋለሁ። በዚህ አጋጣሚ   ቤተሰብ   የተገደለባቸውን እግዚአብሔር አምላክ ያጽናናችሁ፣ የአርሲ  ሕዝብንም አይዟችሁ ፥ የአብርሃም አምላክ ያያችኋል  ለማለት እወዳለሁ።    ይህን ካልኩ በኋላ የፓስተር ግርማ ቤካን  ሐሳብ ነጥብ በነጥብ   እያነሳሁ    ፣ በየነጥቡ ሥር   የራሴን አጭር መልስ እሰጣለሁ፤ ማብራሪያዬንም አስከትላለሁ። አቀራረቡ እስከመጨረሻው እንደዚህ ይቀጥላል። በስፋት ከተደመጠ ቀና  ውይይት ይከፍታል ብዬም አምናለሁ። የተወደድክ ወንድሜ ፓስተር ግርማ ቤካ፡ - ለጤናህ እንደምን አለህ ? እኔ ቸርነቱ የማያልቅበት እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን ደህ...