Skip to main content

ሌላ ማድረግ ባልችል ጻፍሁ (ስለ አርሲ ኦርቶዶክሳውያን)

 ሌላ ማድረግ ባልችል ጻፍሁ (ስለ አርሲ ኦርቶዶክሳውያን)

በአጠቃላይ በኦሮሚያ ክልል፣ በተለይ በአርሲ ዞን የኦርቶዶክስ ክርስትያኖች በተደጋጋሚ  ተጨፍጭፈዋል፣ ቤቶቻቸው ወድመዋል ፣ ተፈናቅለዋል። የተቃጠሉ አብያተ ክርስቲያናትም አሉ። ይህ በታማኝ ምንጮች  የተዘገበ ነው።ይህ የአመጽ ሥራ ከተለያዩ የዓለም አብያተ ክርስቲያናትና ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ተቃውሞ  ተሰምቶበታል ። አመጹ ለተደረገባቸውም የአጋርነት መግለጫ ተሰጥቶበታል። 1 ሙሰሊም ጎረቤቶችም ክርስቲያኖቹን በመከለል ከልብ አጋርነታቸውን ያሳዩበት አጋጣሚ አለ።


ዛሬ እንደገና በአርሲ ኦርቶዶክሳውያን ታርደዋል። በዛው ዞን በበርካታ አካባቢዎች ቤቶቻቸው ተቃጥለዋል። ባለቤቶቹም ክነቤተሰባቸው ሜዳ ላይ በችግር ፈሰዋል፣ ሽብር ሰፍኗል።


ይህ የተለመደ ነው ብለን የምናልፈው ጉዳይ አይደለም። ይህ  በዑደት እየመጣ እንደ ዘበት የሚታለፍ ሁነት ብቻ  ተደርጎ መታየት የሚገባው አይደለም። በሞቱ ቅጽበት የተሰማቸውን አቅመቢስነትና ረዳት የማጣት ሰቀቀን መገመት አይቻልም።

 የሰው ልብ የሚያደክም፣ በዐይን ለማየት የሚዘገንን፣ ለመስማት ጆሮን ጭው የሚያደርግ ሰውን ኅሊና የሚያቆስል ጫካኔ ነው። ሰው ሆኖ መፈጠርን የሚያስጠላ ትዕይንት ነው።


 በእንባና በደም የተጻፈ የታሪክ ምእራፍ - ጩኸታቸው ባልተሰማ ወገኖች ኅሊና ተቀርጾ የሚኖር ነው።ይኸን ያህል ሞቱ በማለት ብቻ  ሰቆቃውን መግለጥ  አይቻልም። በሰው ልጅ ላይ ያረፈውን ጭካኔ፣ የተቃጠሉ ቤቶች ፣ የተበተኑ ቤተሰቦች ፣ ማንም ሊሸከም የማይወደውን ሸክም እንዲሸከም የተፈረደበትን ማኅበረሰብ በዐይነ ኅሊና ማየት ያስፈልጋል። አሳዛኝ ክስተት ነው። 


የቀድሞውም የዛሪውም  ግፍ ሲፈጸም  መንግሥት ኃላፊነቱን በመወጣት የሚያስወቅሰውን እንጂ የሚያመሰግነውን ሥራ አልሠራም። ከዚህ የአመጽ ሥራ ጋር በተገናኘ ከመወቀስ የሚያድነው እርምጃ  አልወሰደም።አስቀድሞ ከጥቃት በመከላከል፣ ደርሶ ከአደጋው በማስጣል፣ ወደ ተፈናቀሉበት ቀዬም መልሶ በማቋቋም፣ ለተጠቁት እርዳታ በማድረስ፣ ገዳዮቹን ይዞ ለፍርድ በማቅረብ ያሳየው ዳተኛነት የሚያስደነግጥ ነው። ከዚህ የተነሳ አንዳንዶች እንዳውም በጉዳዩ የመንግሥት  እጅ እንዳለበት ይጠረጥራሉ።


የወንጌል አማኝ አብያተክርሰቲያናትን በተመለከተ እስካሁን ለኦርቶዶክሳውያኑ ያሳዩት ይፋዊ አጋርነት ተዘግቦ አይገኝም።  ምናልባት የግፉን ጥልቀት፣ ስፋትና ለራሳቸውም ቢሆን አሳሳቢነቱን በሚገባ አልተረዱት ይሆናል።በግርጌ  የተሰጠው ማስታወሻ ቢያነቡት ይህን ያስገነዝባቸዋል የሚል እምነት አለኝ (ለማጣቃሻነት በAI ያጠናቀርኩት ታማኒነት ያለው መረጃ ነው)።

አሁን ግን ጉዳዩን መዝነው በካውንስሉ ደረጃም እንዲሁም አባላቱ በተናጠል የአጋርነት አቋም ያስደምጣሉ የሚል ተስፋ አለኝ።


በየመዋቅሩ  ላሉት የመንግሥት ሹማምንት  ቀረቤታ ያላቸውም ወቀሳ ቢያሰሙአቸው ተገቢ ነው እላለሁ። ይህን በማድረጋቸው ከሥልጣን ይውረዱ ማለታቸው አይደለም። ስለ ዜጎቹ ያለባቸውን መሠረታዊ ኃላፊነታቸውን በወቅቱና በወጉ እንዲወጡ ማስታወሳቸውና መጎትጎታቸው እንጂ። ሙስሊም ጎረቤቶችም በአንድ ወቅት ላይ እንዳደረጉት ሳይሰለቹ  ከለላ በመስጠት  አለኝታነታቸውን  ቢያሳዩ ለበረከት ይሆናል።


 በእርግጥ ግንባር ቀደም  ኃላፊነቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መሆኑ ግልጽ ነው። መፍትሔውን መምራት ይጠበቅባታል።


 ሁላችንም ኢትዮዽያኖች ግን ኃላፊነት አለብን። ታሪኩን እንድንታዘብ  ብቻ ሳይሆን በርኅራሄ ልናያቸው ፣ ስለ እነርሱ ልንጮህ እና በጭንቀታቸው አብረን ልንቆም፣ ፍትሕ እንዲያገኙ ልንናገር ይገባል። በኦርቶዶክሳውያን ላይ በኦሮሚያ ስለሚፈጸመው  የአመጽ ሥራ አንዳች ዘላቂ መፍትሔ ሳይገኝ በዝምታ ማሳለፍ ታሪክ የማይረሳው ምናልባትም ይቅር የማይለው ስህተት ይሆናል። መፍትሔ መፈለጊያ ጊዜው ዛሬና አሁን ነው። በሸንገላም እንዳንዘናጋ።


በፍርሃት ለራዱት፣ በሃዘን ለተዋጡት፣ በሥጋት ለተናወጡት ሁሉ የእግዚአብሔር ሰላም ይክበባቸው። 

የታረዱት ሁሉ በእግዚአብሔር የተፈጠሩ፣ በእግዚአብሔር የተወደዱ እና በእግዚአብሔር በስማቸው የሚታወቁ ናቸው።  በመታረዳቸው ልባቸው የተሰበረባቸውን ቤተሰቦች  እግዚአብሔር በዚህና በነፍስ ወከፍ በሚረዱት በሌላም ቃል ያጽናናቸው።


ከሃዘንተኞቹ የሚሰማው የስቃይ ድምጽ፣ ከተቃጠሉት ቤቶች የተነሳው ጪስ ፥ ከደነገጡ ወገኖች የሚሰማው ኡኡታ፣ ከተበታተነው ቤተሰብ የሚሰማው ዋይታ በእግዚአብሔር ዘንድ ይደርሳሉ።


ስላነበባችሁልኝና የአቅማችሁን ለማድረግ ውሳኔ ስለምታሳልፉ  እግዚአብሔር ይስጥልኝ።


ደህና ቀን ያምጣልን!


ባንቱ ገብረማራያም 

ከአዎን ድምጽ



  1. Footnotes:

    Footnote 1 — News & Human‑Rights Reporting
    1. International news outlets including BBC, Reuters, Associated Press, and The East African reported mass killings, displacement, and destruction of homes in Arsi and wider Oromia. The Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) confirmed dozens of deaths and stated that authorities failed to prevent the attacks or protect civilians.

    Footnote 2 — Catholic & Islamic Solidarity
    1. The Catholic Bishops’ Conference of Ethiopia condemned the “massacres of civilians” in Arsi and expressed solidarity with the Ethiopian Orthodox Church. The Islamic Affairs Supreme Council also issued a statement denouncing the killings and warning that such violence threatens inter‑religious harmony.

    Footnote 3 — Oriental & Eastern Orthodox Churches
    1. Oriental and Eastern Orthodox Churches—including the Coptic, Syriac, Armenian, Russian, Greek, Serbian, and Romanian Churches—issued statements condemning attacks on clergy and churches in Ethiopia and expressing solidarity with the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church.

    Footnote 4 — Evangelical Silence
    1. No major Ethiopian Evangelical denomination issued a public statement regarding the Arsi killings, according to available public records and media reports.

    Footnote 5 — Government Responsibility
    1. Across all sources—EHRC, news outlets, Catholic bishops, and the Ethiopian Orthodox Holy Synod—the government response was described as insufficient both during the attacks and afterward, with displaced families receiving little support and many unable to return home.

    Bibliography

    News Outlets
    BBC News — “Ethiopia: Violence in Oromia Leaves Dozens Dead.”
    https://www.bbc.com/news/topics/cx1m7zg0g1xt/ethiopia

    Reuters — “Killings and Unrest Reported in Ethiopia’s Oromiya Region.”
    https://www.reuters.com/world/africa

    Associated Press (AP) — “Attacks on Clergy and Churches Reported in Ethiopia.”
    https://apnews.com/hub/africa

    The East African — “Mass Killings Reported in Ethiopia’s Arsi Zone.”
    https://www.theeastafrican.co.ke/tea/news

    Human‑Rights Organizations
    Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) — Investigation Reports on Killings and Displacement in Oromia.
    https://ehrc.org

    Global Alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) — “Reports on Mass Killings in Arsi and West Arsi.”
    https://gareadvocacy.org

    Catholic & Islamic Institutions
    Catholic Bishops’ Conference of Ethiopia — “Statement on the Massacres in Arsi.”
    https://cbce-et.org

    Catholic Eparchy of Emdibir — Pastoral letters and statements on violence in Oromia.
    https://emdibirdiocese.org

    Islamic Affairs Supreme Council of Ethiopia — “Statement Condemning the Killings in Arsi.”
    https://eiasc.org

    Ethiopian Orthodox Church
    Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Holy Synod — Public statements on persecution and displacement.
    https://ethiopianorthodox.org

    Oriental Orthodox Churches
    Coptic Orthodox Church — Statements of solidarity with the Ethiopian Orthodox Church.
    https://www.copticorthodox.church

    Syriac Orthodox Church (Patriarchate of Antioch) — Statements on persecution of Christians in Ethiopia.
    https://syriacpatriarchate.org

    Armenian Apostolic Church (Mother See of Holy Etchmiadzin) — Messages of solidarity.
    https://www.etchmiadzin.am

    Eastern Orthodox Churches
    Russian Orthodox Church (Moscow Patriarchate) — Statements condemning the killing of Ethiopian clergy.
    https://mospat.ru/en

    Ecumenical Patriarchate of Constantinople — Messages expressing concern for violence in Ethiopia.
    https://www.patriarchate.org

    Serbian Orthodox Church — Statements condemning religiously motivated violence.
    https://spc.rs/eng

    Romanian Orthodox Church — Appeals for protection of Christians in Ethiopia.
    https://basilica.ro/en

    ↩ Back to text

Comments

Popular posts from this blog

የድንግል ማርያም ክብሯና ዘላለማዊ ድንግልናዋ

የድንግል ማርያም ክብሯና ዘላለማዊ ድንግልናዋ (1)  ድንግል ማርያምን ስለማክበር (2) ለጥያቄዎች መልስ (ሀ) ድንግሊትን ‘የወይን ግንድ (ተክል)’ና የ ‘ሕይወት በር’ የሚል ማዕረግ  ለምን እንሰጣታለን? (ለ) ወደ ድንግል ማርያም መጸለይ ትክክል ነው ወይ? (3) የድንግል ማርያም ድንግልና ዘላለማዊነት (4) ለተቃራኒ አስተያየቶች መልስ (ሀ) “የመጀመሪያ ልጇን” የሚለው ሐረግ (ለ) “ሚስትህ” የሚለው ሐረግ (ሐ) “አብረው ከመሆናቸው በፊት ጸንሳ ተገኘች” (መ) “የመጀመሪያ ልጇን እስክትወልድ አላወቃትም” (ሠ)  “ወንድሞቹ” የሚለው ሐረግ   የቅድስት ድንግል ማርያም  ክብሯ (1) ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ድንግል እመቤታችንን አያከብሩም፤ ደግሞም እንድታማልድላቸውም (እንድትማልድላቸውም)  አይጠይቋትም።ከእነርሱ ወገኖች አንዳንዶቹ እንዲያውም ጫጩቱ ከተፈለፈለ በኋላ ዋጋ ከሌለው የዶሮ እንቁላል ቅርፊት ጋር እስከሚያመሳስሏት ይደርሳሉ።ይህ የተጋነነ ማቃለል የመጣው ምናልባት ሮሜዋውያን ካቶሊኮች የተጋነነ ማክበር ስለሚያከብሯት ለዛ ተቃርኖ ከማሳየት አዝማሚያ ሊሆን ይችላል። ስለዚህም ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን አንዱንም የእርሷን በዓል አያከብሩም።  (2) አንዳንዶቹ የፕሮቴስታንት ወገኖች ድንግል ማርያምን “እህታችን” ይሏታል። (3) በተጨማሪ አንዳንዶቹ ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ጌታ ኢየሱስን በድንግልና ከወለደች በኋላ ከዮሴፍ ጋር ጋብቻዋን ፈጽማለች፤ የ‘ኢየሱስ ወንድሞች’  ወይም የ’ጌታ ወንድሞች’ ተብለው የተጠሩ ልጆችን ወልዳለች ይላሉ።  (4) ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ቤተክርስቲያናችን ለድንግል እመቤታችን የሰጠቻቸውን አንዳንድ የማዕረግ ስሞችም ይቃወማሉ።  (5) ድንግልን ያለማክበራቸው አንዱ...

ጥምቀት

  ጥምቀት       (1) የጥምቀት ፍቱንነቱ (2) ማጥመቅ የካህን ተግባር ነው (3) የጥምቀት አስፈላጊነቱ (4) ጥምቀት በመንከር (በመጥለቅ) (5) የልጆች (የሕጻናት) ጥምቀትሳቦች (6) ተቃውሞዎች   ጥምቀት   በእኛ በኦርቶዶክስና በፕሮቴስታንቶች መኻል ጥምቀትን በተመለከተ ያሉት ልዩነቶች የጥምቀትን ትምህርት በአምስት ጉልህ   ፍሬ ነገሮች ሥር አጠቃሎ መነጋገር ይቻላል። (1)     የጥምቀት   አስፈላጊነቱ   ምንድነው? ፍቱንነቶቹስ (ጠቀሜታዎቹስ) ምንድናቸው? ኦርቶዶክስ ጥምቀት ‘ድኅነት’ን፣ ‘መንጻት’ን፣ ‘መጽደቅ’ን፣ የ‘ሕይወት መታደስ’ን እና በ’ክርስቶስ አካል አባል’ መሆን’ን መቀበያ መንገድ ነው ብላ ታምናለች። የፕሮቴስታንት ቤተ እምነቶች እንደሚሉት እነዚህን   መቀበያው “እምነት” ብቻ ነው። በ እምነት ብቻ መሆኑ ትክክል ከሆነ ታዲያ የጥምቀት አስፈላጊነቱ ምኑ ላይ ነው? የክርስትና ምልክት ብቻ መሆኑ ነውን? ወይስ “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው” (ማቴ 28:19-20) የሚለውን የጌታን ትዕዛዝ መታዘዝ ብቻ መሆኑ ነው? (2 ) ማነው ማጥመቅ ያለበት? በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጥምቀት የሚከናወነው በካህን ብቻ ነው። ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ግን የሰውን ክህነት ጨርሶ አይቀበሉም። ስለሆነም በእነርሱ ቤተ ክርስቲያን የሚያጠምቀው ካህን ወይም ቄስ ያልሆነ አገልጋይ ነው።   ይህ አገልጋይ የቤተክርስቲያኒቷ ሽማግሌ ወይም ሴት ሽማግሌ (የሴቶችን ሽምግልና ...

Comparative Theology የነገረ መለኮት ንጽጽር (በኦርቶዶክስና በፕሮቴስታንት)/ በብፁዕ ወቅዱስ ፖፕ ሲኖዳ ሳልሳዊ

 የነገረ መለኮት ንጽጽር  (በኦርቶዶክስና በፕሮቴስታንት): የወደደ  ሁሉ በነጻ እንዲጠቀምበት ተፖስቷል። ይሁን እንጂ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ስለሆነ በየትኛውም መልኩ ለንግድ እንዲውል አልተፈቀድም። ልዩ ልዩ መግቢያ የሚለውን መጀመሪያ ካነበቡ በኋላ የተቀረውን በተመረጠው ቅደም ተከተል ማንበብ ይቻላል። ልዩ ልዩ መግቢያ   ጥምቀት   ትውፊት (ወግና ልማድ)   መካከለኝነት   ጾም የድንግል ማርያም ክብሯና ዘላለማዊ ድንግልናዋ መንፈሳዊ ስጦታዎችና በልሳኖች የመናገር ስጦታ   ሥርዐት ንስሐ