Skip to main content

Posts

Showing posts from June, 2026

ሌላ ማድረግ ባልችል ጻፍሁ (ስለ አርሲ ኦርቶዶክሳውያን)

  ሌላ ማድረግ ባልችል ጻፍሁ (ስለ አርሲ ኦርቶዶክሳውያን) በአጠቃላይ በኦሮሚያ ክልል፣ በተለይ በአርሲ ዞን የኦርቶዶክስ ክርስትያኖች በተደጋጋሚ  ተጨፍጭፈዋል፣ ቤቶቻቸው ወድመዋል ፣ ተፈናቅለዋል። የተቃጠሉ አብያተ ክርስቲያናትም አሉ። ይህ በታማኝ ምንጮች  የተዘገበ ነው።ይህ የአመጽ ሥራ ከተለያዩ የዓለም አብያተ ክርስቲያናትና ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ተቃውሞ  ተሰምቶበታል ። አመጹ ለተደረገባቸውም የአጋርነት መግለጫ ተሰጥቶበታል። 1 ሙሰሊም ጎረቤቶችም ክርስቲያኖቹን በመከለል ከልብ አጋርነታቸውን ያሳዩበት አጋጣሚ አለ። ዛሬ እንደገና በአርሲ ኦርቶዶክሳውያን ታርደዋል። በዛው ዞን በበርካታ አካባቢዎች ቤቶቻቸው ተቃጥለዋል። ባለቤቶቹም ክነቤተሰባቸው ሜዳ ላይ በችግር ፈሰዋል፣ ሽብር ሰፍኗል። ይህ የተለመደ ነው ብለን የምናልፈው ጉዳይ አይደለም። ይህ  በዑደት እየመጣ እንደ ዘበት የሚታለፍ ሁነት ብቻ  ተደርጎ መታየት የሚገባው አይደለም። በሞቱ ቅጽበት የተሰማቸውን አቅመቢስነትና ረዳት የማጣት ሰቀቀን መገመት አይቻልም።   የሰው ልብ የሚያደክም፣ በዐይን ለማየት የሚዘገንን፣ ለመስማት ጆሮን ጭው የሚያደርግ ፣ የ ሰውን ኅሊና የሚያቆስል   ጫካኔ ነው። ሰው ሆኖ መፈጠርን የሚያስጠላ ትዕይንት ነው።  በእንባና በደም የተጻፈ የታሪክ ምእራፍ - ጩኸታቸው ባልተሰማ ወገኖች ኅሊና ተቀርጾ የሚኖር ነው።ይኸን ያህል ሞቱ በማለት ብቻ  ሰቆቃውን መግለጥ  አይቻልም። በሰው ልጅ ላይ ያረፈውን ጭካኔ፣ የተቃጠሉ ቤቶች ፣ የተበተኑ ቤተሰቦች ፣ ማንም ሊሸከም የማይወደውን ሸክም እንዲሸከም የተፈረደበትን ማኅበረሰብ በዐይነ ኅሊና ማየት ያስፈልጋል። አሳዛኝ ክስተት ነው።...