Skip to main content

Posts

Showing posts from November, 2025

ለፓስተር ግርማ ቤካ

ለፓስተር ግርማ ቤካ ይህ የመጀመሪያው ጽሑፌ በዩ ትዩብ ለማቅረብ እንዲስማማ የተደረገ ነው። አድማጭ ተመልካቾቼ እንደምን ሰነበታችሁ? እኔ ቸርነቱ የበዛ አምላክ ይመስገንና ደህና ነኝ። የዛሬ ዝግጅቴ አንድ ፓስተር ወንድሜ ለተናገረው ምላሸ የሚሰጥ ነው።      የአርሲ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች የደረሰባቸውን ግፍ ከኦርቶዶክሳውያኑ ጎን በመሆን ያወገዙ የወንጌል አማኞች ነበሩ። ይኸንን የወንጌል አማኞች ድርጊት “አታሽቃብጡ” በማለት ይኸው ወንድማችን ተቃውሞታል።የተቃወባቸውን ስምንት ምክንያቶች ነጥብ በነጥብ እያነሳሁ የራሴን አጭር ምላሽ የምሰጥባቸው ይሆናል። ከአጭር ምላሹ በኋላም ማብራሪያን አስከትላለሁ። በመጨረሻም ሐሳቤን አጠቃልላለሁ።በስፋት ከተደመጠ ቀና ውይይት ይከፍታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።      በዚህ አጋጣሚ ቤተሰብ የተገደለባቸውን እግዚአብሔር አምላክ ያጽናናችሁ ለማለት እወዳለሁ። ያፈሩትን ሐብትና ንብረት በትነው፣ ለዘመናት ከኖሩበት ቀዬ እንዲሰደዱ ለተገደዱት ወገኖችም ስቃያችሁን እግዚአብሔር “ሕይወትን ለማዳን” ያድርግላችሁ እላቸዋለሁ። አሁን ወደ ምላሹ፡      የተወደድክ ፓስተር ወንድሜ: ለጤናህ እንደምን አለህ? እኔ ቸርነቱ የማያልቅበት እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን ደህና ነኝ።      በአርሲ ግፍ ለተቀበሉት ኦርቶዶክሳውያን ድምጽ ላሰሙቱ የወንጌል አማኞች “አታሽቃብጡ" በሚል ሐሳብ ዙሪያ የተናገርከውን በአንክሮ አዳምጬ ከጨረስኩ በኋላ ግልጽነትህንና ስሜትህን ለመግለጥ መድፈርህን አድንቄአለሁ።ይኸው ድፍረትህ እኔንም እንድናገር አነቃቅቶኛል። ወንጌላዊ አማኝ ብሆንም በአርሲ ኦርቶዶክሳውያን የደረሰውን ግፍ ካወገዙት ጋር ...

እግዚአብሔር የጠላቶቼ ጠላት አይደለም!

 እግዚአብሔር የጠላቶቼ ጠላት አይደለም! በባንቱ ገብረማርያም አድማጭ ተመልካቾቼ ፡ እንደምን ሰነበታችሁ? እኔ እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ። እንደገና ብቅ ብያለሁ። ዛሬ የምናገረው መምህር  በጋሻው ሰሞኑን የተናገሩት መነሻ ሆኖኝ ነው። ርዕሱም "እግዚአብሔር የጠላቶቼ ጠካት አይደለም" የሚል ይሆናል። እንደ ተለመደው በጽሞና እንድትከታተሉኝ ላስቸግራችሁ እወዳለሁ። አሁን ወደ አስተያየቴ፦ ከዚህ ቀደም በኦርቶዶክሳውያን ስለሚደርሰው መከራ የደረስኩበትን ግንዛቤ “መከራው እስካለ” በሚል ርዕስ ጽፌ ነበር። ማንበብ ለሚፈልግ ሊንኩ ይኸው።  You searched for መከራው እስካለ - Hintset  ። መምህር  በጋሻው ሰሞኑን በተናገሩት መነሻ የጻፍሁት ይኸኛው  ጽሑፍ ከዚያ የተከተለ አድርጎ መውሰድ ይቻላል። “እግዚአብሔር የጠላቶቼ ጠላት አይደለም” የሚለው ሐረግ የተነገረው በማርቲን ኒሞለር (Martin Niemöller") የሉተራዊ ነገረ መለኮት አዋቂ በነበረው ጀርመናዊ ነበር። ማርቲን መጀመሪያ የሂትለር ደጋፊ ቢሆንም በኋላ ላይ  አጥብቀው ከሚቃወሙት አንዱ ሆኗል። “የእግዚአብሔር ፍቅርና ምህረት በወገን/ በቡድን የሚታጠር አይደለም። ጠላት ለሚባሉትም እንኳ የተዘረጋ ነው ። የእዚአብሔር ፍቅር የግል ቂም በቀልን ትክክለኛነት ለማጽደቅ ወይም የበቀል መሣሪያ ሆኖ  ሊያገለግል አይገባውም” ብሎ የሚሞግት ሰው ነበር። ናይጄራዊቷ  ጸሐፊና ተናጋሪ ቺማማንዳ ንጎዚ አዲሼ (Chimamanda Ngozi Adichie) ይኸንን አተያየት በሕይወት ጉዞዋ ደርሳበታለች። ነገር ግን ጊዜ እንደወሰደባት በተለያዩ አጋጣሚዎች ስትናገር ተደምጣለች። የካቶሊክ አማኝ የሆነችዋ ይኽች ሰው አንድ ጊዜ ራሷንና የእርሷ የሆኑትን የ...