Skip to main content

ዘፈኑን እኮ ወንጌል አለው? አልሳተም ትላላችሁ?

 

ዘፈኑን እኮ ወንጌል አለው? አልሳተም ትላላችሁ?


ዘፈኑን “ወንጌል ነው” ማለቱ መሳት አይደለም። የተቃወሙት ሰዎች ዶክተሩ ዘፈኑን ወንጌል አደረገ ብለው ነው የተረዱት። እኔ ግን እንዲህ እላለሁ፦
“ማኀበራዊ ወንጌል”
1 የሚለውን አጠራር ዛሬ እጅግም አንጠቀምበትም። ምክንያቱም ከስሙ ጋር የሚነሱ ያልተፈለጉ ክርከሮችን ለማስቀረት ነው። ይሁን እንጂ እንደ በርካታ የፕሮቴስታንት አሰተማሪዎች ወንጌልን ከማህበራዊ ፍትሕ መነጠል አይቻልም።

የተራራው ስብከትም ይሁን የመጥምቁ ዮሐንስ የ“ንስሐ ግቡ” መልዕክትም በግልጽ ሁኔታ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ግንኙነታዊ ፍትሕን የሚያስተምር መሆኑን የፕሮቴስታንት አስተማሪዎች ያስረዳሉ
2

ይህንን አመለካከት በመቀበል የኢየሱስ ትምህርት በግል ሕይወት ብቻ የሚወሰን ሳይሆን በማህበራዊ ፍትሕ ላይም ግልጽ ጥሪ እንደሚያቀርብ መመልከት ይቻላል።

በእርግጥ ይህን የማይቀበሉ ሌሎች የተከበሩ አስተማሪዎችም አሉ፣ ግን ሁለቱም ወንጌልን ከፍትሕ አያፋቱትም
3

ስለዚህ እውነት፣ ወይም ፍትሕ ወይም ትክክለኛው ሞራል በወንጌል መሰል ዘፈን ቢገለጥ የአግዚአብሔር መልዕክትነቱ አይለወጥም። የወንጌል የሆነው መልዕክት ከቤተክርስቲያን ውጭ ባሉ ሰዎች ሲነገር ያ የአግዚአብሔርን እውነት የሚያስታውሰን ነው
4

የቴዎድሮስ ካሣሁንን ዘፈን ወንጌል ነው ብሎ ደረጀ ሲናገር በዘፈኑ የተላለፈው የፍትሕ፣ የፍቅርና የመሳሰሉት መልዕክት የወንጌል አካል ናቸው ማለቱ ሆኖ ይታየኛል። እንግዳ ነገር እንደተናገረ ያህል የሚያስፈራ አይደለም። የግል ድኅነትን ጉዳይ እንዳይውጠው መጠንቀቁ ግን ክፋት የለውም።

ግን ግን ይኸንን ሰበብ አድርጎ “የአማራ ሕዝብ ሰቆቃ ይቁም” የሚለውን ድምጽ ማፈን ጨካኝነት አይሆንም?


ባንቱ ገብረማርያም 

ከአዎን ድምጽ                  


  1. የማህበራዊ ወንጌል ክርስቲያኖች የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-ምግባርን ሥራ ላይ በማዋል ድህነት፣ እኩልነት መታጣትን፣ የሠራተኛ ብዝበዛን የመሳሰሉትን ማኅበራዊ ችግሮች ስለመፍታት የሚያስተምር ነው። ዐላማውም በምድር ላይ “የእግዚአብሔር መንግሥት” መገንባት ነው። ትኩረታቸውን ማህበራዊ ፍትህ ላይ ባደረጉ ልዩ ልዩ አገልግሎቶች (ሚኒስትሪዎች) ውስጥ እሴቶቹ ዛሬም ድረስ ተፅዕኖ አላቸው። •Christopher H. Evans, The Social Gospel in American Religion: A History (New York: NYU Press, 2017), 45. 
  2. [FGreen, Wright, Keener, France — የኢየሱስና የመጥምቁ ዮሐንስ መልዕክት ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፍትሕን እንደሚያስተምሩ ያሳየሉ 
  3. Social gospe” የሚለውን ቃል ቢቃወሙም በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ፍትሕን እንደ ክርስቲያን ግዴታ የሚቀበሉ ወግ አጥባቂ አስተማሪዎች አሉ። ለምሳሌ ጆን ማካርተር የድኅነት መልዕክት ከማህበራዊ አቀንቃኝነት ጋር እንዳይምታታ በግልጽ “ማኅበራዊ ወንጌልን” ይቃወማል። ያም ሆኖ የፍትሕን አስፈላጊነት ያሰምርበታል። Sources: • John MacArthur, The Gospel According to Jesus (Zondervan, 1994), xiii–xiv. • John MacArthur, “The Social Gospel,” Grace to You (sermon, 2007). 
  4. የእውነት ቃል ከቤተክርስቲያን ውጭ ቢመጣም የእግዚአብሔር ነው ብለው የሚያስተምሩት እነዚህ ናቸው፦ Augustine, On Christian Doctrine (De Doctrina Christiana), II.18.28 (“Wherever truth may be found, it belongs to the Lord.”); John Calvin, Institutes of the Christian Religion, II.2.15–16 (on “common grace,” affirming that God grants truth and moral insight even to unbelievers); John Wesley, Preface to Hymns and Sacred Poems (1739) (“The gospel of Christ knows no religion but social; no holiness but social holiness.”); Dietrich Bonhoeffer, Life Together, ch. 4, and Ethics, “Christ, Reality, and Good” (teaching that God’s truth may confront the church even through voices outside it). 

Comments

Popular posts from this blog

የድንግል ማርያም ክብሯና ዘላለማዊ ድንግልናዋ

የድንግል ማርያም ክብሯና ዘላለማዊ ድንግልናዋ (1)  ድንግል ማርያምን ስለማክበር (2) ለጥያቄዎች መልስ (ሀ) ድንግሊትን ‘የወይን ግንድ (ተክል)’ና የ ‘ሕይወት በር’ የሚል ማዕረግ  ለምን እንሰጣታለን? (ለ) ወደ ድንግል ማርያም መጸለይ ትክክል ነው ወይ? (3) የድንግል ማርያም ድንግልና ዘላለማዊነት (4) ለተቃራኒ አስተያየቶች መልስ (ሀ) “የመጀመሪያ ልጇን” የሚለው ሐረግ (ለ) “ሚስትህ” የሚለው ሐረግ (ሐ) “አብረው ከመሆናቸው በፊት ጸንሳ ተገኘች” (መ) “የመጀመሪያ ልጇን እስክትወልድ አላወቃትም” (ሠ)  “ወንድሞቹ” የሚለው ሐረግ   የቅድስት ድንግል ማርያም  ክብሯ (1) ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ድንግል እመቤታችንን አያከብሩም፤ ደግሞም እንድታማልድላቸውም (እንድትማልድላቸውም)  አይጠይቋትም።ከእነርሱ ወገኖች አንዳንዶቹ እንዲያውም ጫጩቱ ከተፈለፈለ በኋላ ዋጋ ከሌለው የዶሮ እንቁላል ቅርፊት ጋር እስከሚያመሳስሏት ይደርሳሉ።ይህ የተጋነነ ማቃለል የመጣው ምናልባት ሮሜዋውያን ካቶሊኮች የተጋነነ ማክበር ስለሚያከብሯት ለዛ ተቃርኖ ከማሳየት አዝማሚያ ሊሆን ይችላል። ስለዚህም ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን አንዱንም የእርሷን በዓል አያከብሩም።  (2) አንዳንዶቹ የፕሮቴስታንት ወገኖች ድንግል ማርያምን “እህታችን” ይሏታል። (3) በተጨማሪ አንዳንዶቹ ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ጌታ ኢየሱስን በድንግልና ከወለደች በኋላ ከዮሴፍ ጋር ጋብቻዋን ፈጽማለች፤ የ‘ኢየሱስ ወንድሞች’  ወይም የ’ጌታ ወንድሞች’ ተብለው የተጠሩ ልጆችን ወልዳለች ይላሉ።  (4) ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ቤተክርስቲያናችን ለድንግል እመቤታችን የሰጠቻቸውን አንዳንድ የማዕረግ ስሞችም ይቃወማሉ።  (5) ድንግልን ያለማክበራቸው አንዱ...

ጥምቀት

  ጥምቀት       (1) የጥምቀት ፍቱንነቱ (2) ማጥመቅ የካህን ተግባር ነው (3) የጥምቀት አስፈላጊነቱ (4) ጥምቀት በመንከር (በመጥለቅ) (5) የልጆች (የሕጻናት) ጥምቀትሳቦች (6) ተቃውሞዎች   ጥምቀት   በእኛ በኦርቶዶክስና በፕሮቴስታንቶች መኻል ጥምቀትን በተመለከተ ያሉት ልዩነቶች የጥምቀትን ትምህርት በአምስት ጉልህ   ፍሬ ነገሮች ሥር አጠቃሎ መነጋገር ይቻላል። (1)     የጥምቀት   አስፈላጊነቱ   ምንድነው? ፍቱንነቶቹስ (ጠቀሜታዎቹስ) ምንድናቸው? ኦርቶዶክስ ጥምቀት ‘ድኅነት’ን፣ ‘መንጻት’ን፣ ‘መጽደቅ’ን፣ የ‘ሕይወት መታደስ’ን እና በ’ክርስቶስ አካል አባል’ መሆን’ን መቀበያ መንገድ ነው ብላ ታምናለች። የፕሮቴስታንት ቤተ እምነቶች እንደሚሉት እነዚህን   መቀበያው “እምነት” ብቻ ነው። በ እምነት ብቻ መሆኑ ትክክል ከሆነ ታዲያ የጥምቀት አስፈላጊነቱ ምኑ ላይ ነው? የክርስትና ምልክት ብቻ መሆኑ ነውን? ወይስ “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው” (ማቴ 28:19-20) የሚለውን የጌታን ትዕዛዝ መታዘዝ ብቻ መሆኑ ነው? (2 ) ማነው ማጥመቅ ያለበት? በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጥምቀት የሚከናወነው በካህን ብቻ ነው። ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ግን የሰውን ክህነት ጨርሶ አይቀበሉም። ስለሆነም በእነርሱ ቤተ ክርስቲያን የሚያጠምቀው ካህን ወይም ቄስ ያልሆነ አገልጋይ ነው።   ይህ አገልጋይ የቤተክርስቲያኒቷ ሽማግሌ ወይም ሴት ሽማግሌ (የሴቶችን ሽምግልና ...

Comparative Theology የነገረ መለኮት ንጽጽር (በኦርቶዶክስና በፕሮቴስታንት)/ በብፁዕ ወቅዱስ ፖፕ ሲኖዳ ሳልሳዊ

 የነገረ መለኮት ንጽጽር  (በኦርቶዶክስና በፕሮቴስታንት): የወደደ  ሁሉ በነጻ እንዲጠቀምበት ተፖስቷል። ይሁን እንጂ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ስለሆነ በየትኛውም መልኩ ለንግድ እንዲውል አልተፈቀድም። ልዩ ልዩ መግቢያ የሚለውን መጀመሪያ ካነበቡ በኋላ የተቀረውን በተመረጠው ቅደም ተከተል ማንበብ ይቻላል። ልዩ ልዩ መግቢያ   ጥምቀት   ትውፊት (ወግና ልማድ)   መካከለኝነት   ጾም የድንግል ማርያም ክብሯና ዘላለማዊ ድንግልናዋ መንፈሳዊ ስጦታዎችና በልሳኖች የመናገር ስጦታ   ሥርዐት ንስሐ