Skip to main content

ነቢያዊ ድምጽ /መደምደሚያ

  ነቢያዊ ድምጽ /መደምደሚያ


የኢትዮጵያውያ ወንጌላውያንም ሆኑ ጴንጤቆስጣዊ አብያተ ክርስቲያናት የወንጌል አገልግሎታቸው በግል መዳን፣ ቅድስና፣ በመከራ መታገስ እና በሰማይ ተስፋ ዙሪያ ያተኮረ ነው። ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፍትህን አያነሳም። ይህ አካሄድ ወንጌልን   ከአሜሪካና ከአውሮፓ ካመጡልን ወግ አጥባቂ ሚሲዮናውያን የተወረሰ ነው
1

ደርግ ሥልጣን ላይ በወጣበት አካባቢ በላቲን አሜሪካ የታየው የሊበሬሽን (ነጻ የመውጣት) ቲዎሎጂ
2 ወደ ኢትዮጵያ አልገባም። ገብቶ ቢሆን ኖሮ በሚሲዮናውያኑ መር ወንጌል አገልግሎቱ ላይ ማህበረሰብን መለወጥ ይታከልበት ነበር ማለት ስህተት አይሆንም። ያንን ያመለጠ እድል አድርጎ ማሰብ ይቻላል።

በዚያኑ ወቅት የቄስ ጉዲና ቱምሳም “ሁለንተናውን ሰው” ማገልገል የሚለው ነገረ መለኮት የምዕራቡ ነገረ መለኮት በኢትዮጵያ ሁኔታ የጎደለውን እንዲያሟላ መንገድ ከፋች ነበር
3። ይሁን እንጂ መካነ ኢየሱስ በወቅቱ ይኸን ለመቀበል ያልተዘጋጀች ስለነበርና ታሪካዊ ሁኔታ ባለማመቸቱ ተጨናግፏል። የባከን እድል ነው ማለት ይቻላል።

በደርግ ዘመን ቤተክርስቲያን ብትሰፋም በሚሲዮኑ ከተተለመው መሥመር አልወጣችም። በሕዝባዊ ጉዳይ መግባት ለሞት የሚያደርስ ስለነበርም ዝምታውን ከመሞት የመሰንበት ዘዴ ሆኗት ነበር
4

ከደርግ መውደቅ ወዲህም አካባቢው በዛው በግል ድኅነት ዙሪያ ተወስኖ ለመሥራት ነጻነት ይኑር እንጂ በማኅበራዊ ጉዳይ ለመግባት አመቺ ሁኔታም አልነበረም።

በእርግጥ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የሃይማኖት ነጻነቱን በአደባባይ ሳይቀር ፕሮግራም ማድረግ እስከሚቻል ድረስ አስፍተውታል። ታዲያ ምን ያደርጋል እንደ ተቃውሚዎቻቸው ግምገማ ከሆነ ቤተ እምነቶችን መልሰው ካልተቆጣጠርኳችሁ ይላሉ
5

በካውንስሉ በኩል በማኅበራዊ ጉዳይ ለመሳተፍ ለወንጌል አማኞች በሩን ከፈት ያደረጉትም ይመስላል። ይሁን እንጂ እስካሁን ስለተጨቆኑ ወይም ስለተገፉ ድምጽ የሚያሰሙ ብቅ አላሉም። እኔ እንደ ተከታተልኩት ከሆነ ወንጌላውያኑ ዝምታቸውን አልሰበሩም። ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ የሚባሉትን መገመት ይቻላል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚወራባቸው ልጓም አስገብተው ይሆን? በደርግ ዘመን የነበረው ድንጋጤ አሁንም ድረስ ከሕዝበ ክርስቲያኑን ልብ አልወጣ ይሆን? 
ወንጌል አማኙ በብልጽግና ወንጌል የግል ስኬትና ምቾት ተስፋ ተሞልቶ የራሱን ጉዳይ ብቻ እያየ ይሆን?ብዙዎቹ አገልጋዮች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀረቤታ አላቸው ይባላል። እርሳቸውን ላለማሳዘን ለጥንቃቄ ይሆን? 

እነዚህ ሁሉ መልስ ሊሆኑ ይችላሉ። ግን ያው ሁሉም ግምት ነው። ነገር ግን ስለተበደሉ ወይም ስለተገፉ የሚናገር ድምጽ አልተሰማም። ዛሬም በዛው ሚሲዮን መር አገልግሎት ላይ መወሰን ይታያል።

ግፉ ግን በዝቷል። አንዳንዱን ለመስማት እንኳ ይዘገንናል። ደግነቱ “ግፍ ሲበዛ፣ አፍ ሁሉ ሲዘጋ፣ ያኔ ነቢያዊ ድምጽ (Prophetic Voice)
6 ” ይነሳል። ለአማራው ያ ነቢያዊ ድምጽ ዶ/ር ደረጀ ከበደ ሆኖ ተገኝቷል። እጅግ የበዛ ‘አዋኪ ሞገድን’ ሰንጥቆ ኩልል ያለ ድምጹን ስለ ግፉአኑ አማራዎች አሰምቷል። እኛም እንተባበረው።

ይቅርታ ነገር አበዛሁባችሁ።
ሁሉ ቀን ሠናይ ቀን ይሁንላችሁ።
ያነበበና የወደደ ለሌላ ያሰማ–ያስነብብ።

ቸር ሰንብቱልኝ
ባንቱ ገብረማርያም
ከአዎን ድምጽ
       

Modern AI tools were used to support the preparation of this manuscript.



  1. Øyvind Eide, Revolution and Religion in Ethiopia (Brill, 2000).
  2. Gustavo Gutiérrez, A Theology of Liberation (Orbis Books, 1973); Leonardo Boff, Liberating Theology (Orbis Books, 1979); CELAM Documents: Medellín (1968), Puebla (1979).
  3. Jörg Haustein, Historiography of Ethiopian Pentecostalism (2011); Rode Molla, EECMY and Society (2018).
  4. Jörg Haustein, “Religion and the State in Ethiopia,” Journal of Eastern African Studies (2014).
  5. Jon Abbink, “Religion in Public Life in Ethiopia,” Africa Spectrum (2020).
  6. “Prophetic voice is the moral courage to speak truth on behalf of the oppressed, even when silence is safer.”

    This means:
    • A prophetic voice is not about predicting the future.
    • It is about speaking truth to power.
    • It is about defending the oppressed, the poor, the marginalized.
    • It requires courage, because speaking out can be dangerous.
    • Many people stay silent to protect themselves, but a prophetic voice refuses to be silent.

Comments

Popular posts from this blog

የድንግል ማርያም ክብሯና ዘላለማዊ ድንግልናዋ

የድንግል ማርያም ክብሯና ዘላለማዊ ድንግልናዋ (1)  ድንግል ማርያምን ስለማክበር (2) ለጥያቄዎች መልስ (ሀ) ድንግሊትን ‘የወይን ግንድ (ተክል)’ና የ ‘ሕይወት በር’ የሚል ማዕረግ  ለምን እንሰጣታለን? (ለ) ወደ ድንግል ማርያም መጸለይ ትክክል ነው ወይ? (3) የድንግል ማርያም ድንግልና ዘላለማዊነት (4) ለተቃራኒ አስተያየቶች መልስ (ሀ) “የመጀመሪያ ልጇን” የሚለው ሐረግ (ለ) “ሚስትህ” የሚለው ሐረግ (ሐ) “አብረው ከመሆናቸው በፊት ጸንሳ ተገኘች” (መ) “የመጀመሪያ ልጇን እስክትወልድ አላወቃትም” (ሠ)  “ወንድሞቹ” የሚለው ሐረግ   የቅድስት ድንግል ማርያም  ክብሯ (1) ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ድንግል እመቤታችንን አያከብሩም፤ ደግሞም እንድታማልድላቸውም (እንድትማልድላቸውም)  አይጠይቋትም።ከእነርሱ ወገኖች አንዳንዶቹ እንዲያውም ጫጩቱ ከተፈለፈለ በኋላ ዋጋ ከሌለው የዶሮ እንቁላል ቅርፊት ጋር እስከሚያመሳስሏት ይደርሳሉ።ይህ የተጋነነ ማቃለል የመጣው ምናልባት ሮሜዋውያን ካቶሊኮች የተጋነነ ማክበር ስለሚያከብሯት ለዛ ተቃርኖ ከማሳየት አዝማሚያ ሊሆን ይችላል። ስለዚህም ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን አንዱንም የእርሷን በዓል አያከብሩም።  (2) አንዳንዶቹ የፕሮቴስታንት ወገኖች ድንግል ማርያምን “እህታችን” ይሏታል። (3) በተጨማሪ አንዳንዶቹ ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ጌታ ኢየሱስን በድንግልና ከወለደች በኋላ ከዮሴፍ ጋር ጋብቻዋን ፈጽማለች፤ የ‘ኢየሱስ ወንድሞች’  ወይም የ’ጌታ ወንድሞች’ ተብለው የተጠሩ ልጆችን ወልዳለች ይላሉ።  (4) ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ቤተክርስቲያናችን ለድንግል እመቤታችን የሰጠቻቸውን አንዳንድ የማዕረግ ስሞችም ይቃወማሉ።  (5) ድንግልን ያለማክበራቸው አንዱ...

ጥምቀት

  ጥምቀት       (1) የጥምቀት ፍቱንነቱ (2) ማጥመቅ የካህን ተግባር ነው (3) የጥምቀት አስፈላጊነቱ (4) ጥምቀት በመንከር (በመጥለቅ) (5) የልጆች (የሕጻናት) ጥምቀትሳቦች (6) ተቃውሞዎች   ጥምቀት   በእኛ በኦርቶዶክስና በፕሮቴስታንቶች መኻል ጥምቀትን በተመለከተ ያሉት ልዩነቶች የጥምቀትን ትምህርት በአምስት ጉልህ   ፍሬ ነገሮች ሥር አጠቃሎ መነጋገር ይቻላል። (1)     የጥምቀት   አስፈላጊነቱ   ምንድነው? ፍቱንነቶቹስ (ጠቀሜታዎቹስ) ምንድናቸው? ኦርቶዶክስ ጥምቀት ‘ድኅነት’ን፣ ‘መንጻት’ን፣ ‘መጽደቅ’ን፣ የ‘ሕይወት መታደስ’ን እና በ’ክርስቶስ አካል አባል’ መሆን’ን መቀበያ መንገድ ነው ብላ ታምናለች። የፕሮቴስታንት ቤተ እምነቶች እንደሚሉት እነዚህን   መቀበያው “እምነት” ብቻ ነው። በ እምነት ብቻ መሆኑ ትክክል ከሆነ ታዲያ የጥምቀት አስፈላጊነቱ ምኑ ላይ ነው? የክርስትና ምልክት ብቻ መሆኑ ነውን? ወይስ “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው” (ማቴ 28:19-20) የሚለውን የጌታን ትዕዛዝ መታዘዝ ብቻ መሆኑ ነው? (2 ) ማነው ማጥመቅ ያለበት? በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጥምቀት የሚከናወነው በካህን ብቻ ነው። ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ግን የሰውን ክህነት ጨርሶ አይቀበሉም። ስለሆነም በእነርሱ ቤተ ክርስቲያን የሚያጠምቀው ካህን ወይም ቄስ ያልሆነ አገልጋይ ነው።   ይህ አገልጋይ የቤተክርስቲያኒቷ ሽማግሌ ወይም ሴት ሽማግሌ (የሴቶችን ሽምግልና ...

Comparative Theology የነገረ መለኮት ንጽጽር (በኦርቶዶክስና በፕሮቴስታንት)/ በብፁዕ ወቅዱስ ፖፕ ሲኖዳ ሳልሳዊ

 የነገረ መለኮት ንጽጽር  (በኦርቶዶክስና በፕሮቴስታንት): የወደደ  ሁሉ በነጻ እንዲጠቀምበት ተፖስቷል። ይሁን እንጂ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ስለሆነ በየትኛውም መልኩ ለንግድ እንዲውል አልተፈቀድም። ልዩ ልዩ መግቢያ የሚለውን መጀመሪያ ካነበቡ በኋላ የተቀረውን በተመረጠው ቅደም ተከተል ማንበብ ይቻላል። ልዩ ልዩ መግቢያ   ጥምቀት   ትውፊት (ወግና ልማድ)   መካከለኝነት   ጾም የድንግል ማርያም ክብሯና ዘላለማዊ ድንግልናዋ መንፈሳዊ ስጦታዎችና በልሳኖች የመናገር ስጦታ   ሥርዐት ንስሐ