ቴዲ አፍሮ መጥምቁ ዮሐንስ ነው?
ቴዲ አፍሮ ስለ ማህበራዊ ፍትሕ መዝፈኑን ሲያደንቅ ዶክተር ደረጀ መጥምቁ ዮሐንስን አድርጎ ስሎታል። መቼም መጥምቁ ዮሐንስ የጌታን መንገድ ጠራጊ እንደነበረ ደረጀ አያውቅም አይባልም፣ የወንጌል ማዕከሉ የኃጢአተኛ ድኅነት መሆኑንም ይረሳል ተብሎ አይታሰብም።
ነገር ግን ጥቂት የማይባሉ ፕሮቴስታንቶች የዮሐንስ “ንስሐ ግቡ” ስብከት የፍትሕ መልዕክትን ያካትታል ብለው ያምናሉ 1።
ይህንን አመለካከት በመቀበል የዮሐንስ መልዕክት የፍትሕ ጥሪን እንደሚያካትት መረዳት ቀላል ይሆናል።
ስለ ፍትሕን ማንም ተናገረው ማንም ያው የእግዚአብሔርን ሓሳብ መግለጡ ነው። ቴዲ አፍሮም በዘፈን መልክ ቢያቀርበው ያው የእግዚአብሔር እውነት ነው። ስለ እግዚአብሔር ፍትሕ ከቤተክርስቲያን ውጭ ያሉ ሲናገሩት የእግዚአብሔር እውነትነቱን ያጣል ማለት አይደለም። አባቶች ከቤተክርስቲያን ውጭ ያሉ ሰዎች የእግዚአብሔርን እውነት ሊናገሩ የሚችሉበት ጊዜ እንዳለና ያ ዐይነቱ የእግዚአብሔር እውነት እንደሆነ ያምናሉ 2።
በአጭሩ ዶ/ር ደረጀ ያለው የቴዲ አፍሮ ዘፈን መጥምቁ ዮሐንስ ያለውንና የተናገረበትን መንፈስ ያስታውሳል ነው። መጥምቁ ዮሐንስ ራሱን ነው ብሎ መጥራቱ አይደለም። እኔ የምረዳው እንደዚህ ነው፤ ከተሳሳትኩ እታረማለሁ።
ለማንኛውም “የአማራ ሕዝብ ግፍ እየተፈጸመበት ነው! ይቁምለት” ማለቱ ቀርቶ ይኸን ሰበብ አገኘሁ ብሎ ነገር ማስቀየስ በደለኝነት ነው።
ባንቱ ገብረማርያም
ከአዎን ድምጽ
- ግፉ በአማራ ላይ (መግቢያ)“ግፉ ሲበዛ ፣ አፍ ሁሉ ሲዘጋ ፣ ያኔ ነቢያዊ ድምጽ ይገኝ ፡ ክፍል 1
- በሕይወቱ ሊበረታ ነው ምኞቱበሕይወቱ ሊበረታ ነው ምኞቱ
- የተለወጠ ክርስቲያን ንግግር ነው?የተለወጠ ክርስቲያን ንግግር ነው?
- ከተደራጁ ሃይማኖቶች እንውጣን?ከተደራጁ ሃይማኖቶች እንውጣን?
- በእውኑ ካውንስሉ ፖለቲካ ይሠራልን?በእውኑ ካውንስሉ ፖለቲካ ይሠራልን?
- ፌክ ኢትዮጵያኒስቶች ከፊቱ ዞር በሉፌክ ኢትዮዽያኒሰቶች ከፊቱ ዞር በሉ!
- ቴዲ አፍሮ መጥምቁ ዮሐንስ ነው?ቴዲ አፍሮ መጥምቁ ዮሐንስ ነው?
- ዘፈኑን ወንጌል አለው! አልሳተም?ዘፈኑን እኮ ወንጌል አለው? አልሳተም ትላላችሁ?
- ነቢያዊ ድምጽ (መደምደሚያም) ነቢያዊ ድምጽ /መደምደሚያ
- የዮሐንስ “ንስሐ ግቡ” የፍትሕ መልዕክት መሆኑን የሚያስረዱ ፕሮቴስታንት አስተማሪዎች መካከል Joel Green (NICNT)N. T. Wright Craig Keener. T. France Wesley ይገኙበታል።
-
እንደሚከተሉት አባቶች ከተሄደ የእውነት ቃል ከቤተክርስቲያን ውጭ ቢመጣም የእግዚአብሔር እውነት ነው።
Augustine, On Christian Doctrine (De Doctrina Christiana), II.18.28 — “Wherever truth may be found, it belongs to the Lord.”
John Calvin, Institutes of the Christian Religion, II.2.15–16 — on “common grace,” affirming that God grants truth and moral insight even to unbelievers.
John Wesley, Preface to Hymns and Sacred Poems (1739) — “The gospel of Christ knows no religion but social; no holiness but social holiness.”
Dietrich Bonhoeffer, Life Together, ch. 4, and Ethics, “Christ, Reality, and Good” — teaching that God’s truth may confront the church even through voices outside it.
Comments
Post a Comment