በእውኑ ካውንስሉ ፖለቲካ ይሠራልን?
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች ካውንስልን በአስተምህሮ ጤናማ የሚባሉትን ከማይባሉት ጋር ቀይጦ በአባልነት መያዙ የሚታወቅ ነው።
ሰለዚህ ድርጅት ነው ለክቡር ጠ/ሚ ፖለቲካ መሣሪያ መሆኑን ዶ/ር ደረጀ በግልጽ የተናገረው። አዎ በወንጌላውያኑ በራሳቸው ተቋቋመ ቢባልም በተግባር ጠ/ሚ የወንጌል አማኞችን ለራሳቸው ለማሰለፍ ተጠቅመውበታል ቢባል ስህተት አይመስለኝም። ለአእርሳቸው የሚሆን ፖለቲካ እየሠራ ነው።
እኔ እንደ ተከታተልኩት ከሆነ በተቃራኒው ተቃዋሚዎቹ ከወንጌል አማኞች ድጋፍን ለማግኘት ሲሠሩ አይታዩም። ብዙዎቹ ብልጽግና ወንጌልንና ሐሰተኛ ነቢያቶችን ተገን አድርገው ፕሮቴስታንቶችን ለመውቀስ ብቻ ይበረታሉ እንጂ “ጸልዩልን” እንኳ ብለው አልቀረቡም። ይህ ጉድለታቸው የአሁኑን መንግሥት ለመተካት ተዘጋጅተናል፥ ብቁ ነን በሚሉበት ጊዜ ምናልባት ይታያቸው ይሆናል። የመንግሥት ወገን ሆኖ ነው እንጂ አዎ ካውንስሉ ፖለቲካ ይሠራል።
ወደ ዶ/ር ደረጀ ከበደ ሐሳብ ልመለስና ካውንስሉ የዶ/ር አብይ አገልጋይ ነው ማለቱ እስካሁን በአንዳንዶች ሲነገር የቆየን የሚደግም ነው። ሲባል መቆየቱን ያልሰማ ወንጌላዊ አማኝ ካለ አሁን ይሰማል ማለት ነው። ከዚህ በኋላ ካውንስሉን እንደ ክርስቲያን ማኅበር ብቻ አድርጎ ማየት ያስቸግርም ይሆናል። የሚደግፈውም ሆነ የሚቃወመው የፖለቲካ ሚናውን እያሰበ የሚሆን ይመስለኛል።
ወንጌል አማኞች በዚህ ድርጅት ውስጥ ወይም ጋር መሥራት ሲያስቡ ይህን አውድ አስቀድመው ይመዝኑም ይሆናል።
ያም ሆነ ይህ ካውንስሉ ጎብዞና ደፍሮ በአማራ ሕዝብና በሌሎችም ላይ እየደረሰ ያለው ‘ጭካኔያዊ ሥራ’ ይቁም ብሎ በአደባባይ ይናገራል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። እንደ እኔ ከሆነ ፖለቲካ ከሠሩ አይቀር ለተገፉት አጋር ቢኮን ያስመሰግናል።
- ግፉ በአማራ ላይ (መግቢያ)“ግፉ ሲበዛ ፣ አፍ ሁሉ ሲዘጋ ፣ ያኔ ነቢያዊ ድምጽ ይገኝ ፡ ክፍል 1
- በሕይወቱ ሊበረታ ነው ምኞቱበሕይወቱ ሊበረታ ነው ምኞቱ
- የተለወጠ ክርስቲያን ንግግር ነው?የተለወጠ ክርስቲያን ንግግር ነው?
- ከተደራጁ ሃይማኖቶች እንውጣን?ከተደራጁ ሃይማኖቶች እንውጣን?
- በእውኑ ካውንስሉ ፖለቲካ ይሠራልን?በእውኑ ካውንስሉ ፖለቲካ ይሠራልን?
- ፌክ ኢትዮጵያኒስቶች ከፊቱ ዞር በሉፌክ ኢትዮዽያኒሰቶች ከፊቱ ዞር በሉ!
- ቴዲ አፍሮ መጥምቁ ዮሐንስ ነው?ቴዲ አፍሮ መጥምቁ ዮሐንስ ነው?
- ዘፈኑን ወንጌል አለው! አልሳተም?ዘፈኑን እኮ ወንጌል አለው? አልሳተም ትላላችሁ?
- ነቢያዊ ድምጽ (መደምደሚያም) ነቢያዊ ድምጽ /መደምደሚያ
Comments
Post a Comment