Skip to main content

Posts

Showing posts from July, 2023

ዐማራ ብልጽግና ዐላፊዎች

  ለዐማራ ብልጽግና ዐላፊዎች፦ እንደ ባሕላችንና እንደ ወጋችን አስድሜ የእግዚአብሔር ሰላምታዬን አቀረባለሁ። ይኸንን ጽሑፍ አግኝታችሁ ለማንበብ ዕድል ላይኖራችሁ ይችላል። አግኝታችሁም  መልስ የመስጠት ግዴታ አይሰማችሁ ይሆናል። እንደሰለጠነ አመራር ግን መረጃን ስታነፈንፉ ድንገት ታገኙታላችሁ ፤ መልስ ለመስጠትም አትቦዝኑም ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።  ጽሑፌን ከመቀጠሌ በፊት  አቅሜን ልግለጥ።  ምንም የፖለቲካ ሥራ ሠርቼ አላውቅም፣ ዕውቀቱም የለኝም። ስለዚህ የምሰጠው አስተያየት ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው ቢባል ሊያስኬድ እንደሚችል እገነዘባለሁ።አእምሮ እንዳለው  ሰው ግን ማሰቤ አልቀረም።  በመጀመሪያ  ሕዝብን ለማስተዳደር በመፍቀዳችሁ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ። በተለይም  በኢትዮጵያ ሁኔታ ይኸንን ለማድረግ በመምረጣችሁ መደነቅ የሚገባችሁ ይመስለኛል።  የልባችሁን የምታውቁት እናንተ ብትሆኑም ፣ ለማገልገል ገፊ ምክንያታችሁ የሚያስገኘው ክብር ወይም  ጥቅም እንዳልሆነ ባምን ደስ ይለኛል።ኢሕዴን ሆናችሁ ብቅ ባላችሁበት ጊዜ ያ እንዳልነበረ ተመልክቼአለሁና።  ወንበሩ ላይ ከተቀመጣችሁ በኋላ ግን  እንደሚወራው ወሬ ከሆነ ያ ጠባያችሁ አልተቀየረም ብዬ ልሟገትላችሁ አልችልም።ኢሕዴን ሆናችሁ  የሠራችሁትን ትክክል ነበር ወይም አልነበረም በማለትም ጉንጩን ለማልፋት አልሻም። አልፏልም፤ አይጠቅምም። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ብልጽግና እስከሆናችሁበት ጊዜም ለድርጅታዊ ነጻነታችሁ የውስጥ ትግል ስታደርጉ የቆያችሁ ይመስላል። አሁን የምጽፈው የዐማራ ብልጽግና ከሆናችሁ ወዲህ ስላለው ነው። እሳቱ ላይ የተዳጣችሁት እናንተ ስለሆናችሁ አጣብቂኛችሁን የምታውቁትም እናንተ ናችሁ። እስካልተነፈ...