Skip to main content

ዐማራ ብልጽግና ዐላፊዎች

 ለዐማራ ብልጽግና ዐላፊዎች፦



እንደ ባሕላችንና እንደ ወጋችን አስድሜ የእግዚአብሔር ሰላምታዬን አቀረባለሁ።

ይኸንን ጽሑፍ አግኝታችሁ ለማንበብ ዕድል ላይኖራችሁ ይችላል። አግኝታችሁም  መልስ የመስጠት ግዴታ አይሰማችሁ ይሆናል። እንደሰለጠነ አመራር ግን መረጃን ስታነፈንፉ ድንገት ታገኙታላችሁ ፤ መልስ ለመስጠትም አትቦዝኑም ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። 

ጽሑፌን ከመቀጠሌ በፊት  አቅሜን ልግለጥ።  ምንም የፖለቲካ ሥራ ሠርቼ አላውቅም፣ ዕውቀቱም የለኝም። ስለዚህ የምሰጠው አስተያየት ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው ቢባል ሊያስኬድ እንደሚችል እገነዘባለሁ።አእምሮ እንዳለው  ሰው ግን ማሰቤ አልቀረም።

 በመጀመሪያ  ሕዝብን ለማስተዳደር በመፍቀዳችሁ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ። በተለይም  በኢትዮጵያ ሁኔታ ይኸንን ለማድረግ በመምረጣችሁ መደነቅ የሚገባችሁ ይመስለኛል። 

የልባችሁን የምታውቁት እናንተ ብትሆኑም ፣ ለማገልገል ገፊ ምክንያታችሁ የሚያስገኘው ክብር ወይም  ጥቅም እንዳልሆነ ባምን ደስ ይለኛል።ኢሕዴን ሆናችሁ ብቅ ባላችሁበት ጊዜ ያ እንዳልነበረ ተመልክቼአለሁና።  ወንበሩ ላይ ከተቀመጣችሁ በኋላ ግን  እንደሚወራው ወሬ ከሆነ ያ ጠባያችሁ አልተቀየረም ብዬ ልሟገትላችሁ አልችልም።ኢሕዴን ሆናችሁ  የሠራችሁትን ትክክል ነበር ወይም አልነበረም በማለትም ጉንጩን ለማልፋት አልሻም። አልፏልም፤ አይጠቅምም። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ብልጽግና እስከሆናችሁበት ጊዜም ለድርጅታዊ ነጻነታችሁ የውስጥ ትግል ስታደርጉ የቆያችሁ ይመስላል። አሁን የምጽፈው የዐማራ ብልጽግና ከሆናችሁ ወዲህ ስላለው ነው።

እሳቱ ላይ የተዳጣችሁት እናንተ ስለሆናችሁ አጣብቂኛችሁን የምታውቁትም እናንተ ናችሁ። እስካልተነፈሳችሁት ድረስ የማውቅበት ዘዴ የለኝም። ስለዚህ ጥያቄዬ ወይም አስተያየቴ በውጭ በምሰማው መረጃ ላይ ብቻ የተመሠረተ  ነው።የውስጥ አዋቂ አይደለሁም። የውስጥ አዋቂም አላውቅም።ወሬው አሉባልታ ብቻ ከሆነ ይኸንኑ ትገልጡታላችሁ ብዬ አምናለሁ።

  1. ከሌሎች የብልጽግና አባላት ጋር በመሆን መላዋን ኢትዮጵያ  ስለምታስተዳድሩ  ዘይቤያችሁን ለዚያ በሚስማማ መልክ ቃኝታችሁ  

  2. የዐማራ ሕዝብ ሆደ ሰፊነትና ሁሉን አቃፊነት ባሕል  ጨምድዷችሁ  

  3. የመሪው ብልጽግና ክንፍ ተጽዕኖ በርትቶባችሁ

  4. በሌላ ክልል ያለው ዐማርኛ ተናጋሪ ሕዝብ እንዳይጎዳ  ተጠንቅቃችሁ

ሊሆን ይችላል፦ “ለቤት ቀጋ ለውጭ አልጋ” እንደሆናችሁ ይሰማኛል።በዚህ የአስተዳደር ዘመናችሁ የዐማራ ሕዝብና ዎገኖቹ እንዳልተመቸው አያለሁ። 

  • በጅምላ ከመገደልና ከመቀበር ፣ ያለአግባብ ከመፈናቀል አልታደጋችሁትም። ወይም ራሱን እንዲከላከል ሁኔታን አላመቻችሁም (አልፎ አልፎ አንዳንድ ሙከራ እንዳለ ሰምቼአለሁ)። 

  • በጦርነት ከመጠቃት የሚከለልበትን ዘዴ አላዘጋጃችሁም ነበር። ዛሬም ከዚያ ሥጋት አላወጣችሁትም።

  • በጠለፋ ከመወሰድና ከመሰወር አልታደጋችሁትም። የተጠለፉትንም መጨረሻ አልተከታተላችሁም

  • በመላዋ ኢትዮጵያ ተዘዋወሮ መሥራትና ንብረትን ማፍራት እንዲችል  ዋስትና አላስገኛችሁለትም። ቀድሞ የነበረውንም የንብረት መብት  አላስጠበቃችሁለትም።

እነዚህ የአንድ  መንግሥት ትንሹና መሠረታዊ ኃላፊነቶቹ  አድርጌ አያቸዋለሁ።አልተወጣችኋቸውም።  ከዐማራ ክልል ውጭ የሚኖረው ዐማርኛ ተናጋሪ ፖለቲካዊ ውክልና እንዲያገኝ ማስቻልማ ቅንጦት ነው። “ጽድቁም ቀርቶ በጽድቁ በኮነነኝ” እንዲሉ፤ ይኼ ሁሉ ቀርቶ ጩኸቱን እንኳ ባደመጣችሁት ኖሮ።

ከዚህም የከፋው ለዐማራው ሕዝብ  እንታገልለን ለሚሉት በሩንና መንገዱን መጠርቀማችሁ ነው። አልፎ ተርፎ እጃቸውን ትጠመዝዛላችሁ፣ ታስሯችዋላችሁ፣ ታጠፏቸዋላችሁ። ሲሆን ሲሆን የዐማራ ሕዝብን ሕልውና በማስጠበቁ አብራችሁ ልትተባበሩ በተገባችሁ ነበር።

 ከክልሉ ውጭ ያለው ዐማርኛ ተናጋሪ በሰላም ሊኖር የቻለበት ሥፍራ የመኖሩም ምክንያት የእናንተ ሥራ ሳይሆን አብሮት የሚኖረው የአካብቢው ሕዝብ ክፉ መሥራትን አለመምረጡ ነው። 

ስለዚህ  የመተማመኛ ድምጽ ጠይቃችሁ የሕዝብ ዐመኔታ ካላገኛችሁ፣ በገዛ ፈቃዳችሁ ኃላፊነታችሁን "ለዐማራ ሕዝብ ሕልውና መጠበቅ" እንሠራለን ለሚሉ ለሌሎች ብትለቁና የእኛም ዕድል፣ የእነርሱም ችሎታ ቢሞከር እላለሁ። 

ነው  ወይስ እኛ በውስጥ ሥራዎችን ባንሠራ ኖሮ የባሰ ይሆን ነበር፤ ኃላፊነታችንን  ከለቀቅን የዐማራ ሕዝብና ዎገኖቹ የባሰውን ሰማዩ ይደፋበታልና እንቀጥል ትሉኝ ይሆን?

የደፈርኳችሁ  ዎገኔ ስለሆናችሁ ነው።እንደማትከፉብኝ ተስፋ አደርጋለሁ። 

እግዚአብሔር ይስጥልኝ። ቸር እንሰንብት


Comments

Popular posts from this blog

የድንግል ማርያም ክብሯና ዘላለማዊ ድንግልናዋ

የድንግል ማርያም ክብሯና ዘላለማዊ ድንግልናዋ (1)  ድንግል ማርያምን ስለማክበር (2) ለጥያቄዎች መልስ (ሀ) ድንግሊትን ‘የወይን ግንድ (ተክል)’ና የ ‘ሕይወት በር’ የሚል ማዕረግ  ለምን እንሰጣታለን? (ለ) ወደ ድንግል ማርያም መጸለይ ትክክል ነው ወይ? (3) የድንግል ማርያም ድንግልና ዘላለማዊነት (4) ለተቃራኒ አስተያየቶች መልስ (ሀ) “የመጀመሪያ ልጇን” የሚለው ሐረግ (ለ) “ሚስትህ” የሚለው ሐረግ (ሐ) “አብረው ከመሆናቸው በፊት ጸንሳ ተገኘች” (መ) “የመጀመሪያ ልጇን እስክትወልድ አላወቃትም” (ሠ)  “ወንድሞቹ” የሚለው ሐረግ   የቅድስት ድንግል ማርያም  ክብሯ (1) ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ድንግል እመቤታችንን አያከብሩም፤ ደግሞም እንድታማልድላቸውም (እንድትማልድላቸውም)  አይጠይቋትም።ከእነርሱ ወገኖች አንዳንዶቹ እንዲያውም ጫጩቱ ከተፈለፈለ በኋላ ዋጋ ከሌለው የዶሮ እንቁላል ቅርፊት ጋር እስከሚያመሳስሏት ይደርሳሉ።ይህ የተጋነነ ማቃለል የመጣው ምናልባት ሮሜዋውያን ካቶሊኮች የተጋነነ ማክበር ስለሚያከብሯት ለዛ ተቃርኖ ከማሳየት አዝማሚያ ሊሆን ይችላል። ስለዚህም ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን አንዱንም የእርሷን በዓል አያከብሩም።  (2) አንዳንዶቹ የፕሮቴስታንት ወገኖች ድንግል ማርያምን “እህታችን” ይሏታል። (3) በተጨማሪ አንዳንዶቹ ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ጌታ ኢየሱስን በድንግልና ከወለደች በኋላ ከዮሴፍ ጋር ጋብቻዋን ፈጽማለች፤ የ‘ኢየሱስ ወንድሞች’  ወይም የ’ጌታ ወንድሞች’ ተብለው የተጠሩ ልጆችን ወልዳለች ይላሉ።  (4) ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ቤተክርስቲያናችን ለድንግል እመቤታችን የሰጠቻቸውን አንዳንድ የማዕረግ ስሞችም ይቃወማሉ።  (5) ድንግልን ያለማክበራቸው አንዱ...

Comparative Theology የነገረ መለኮት ንጽጽር (በኦርቶዶክስና በፕሮቴስታንት)/ በብፁዕ ወቅዱስ ፖፕ ሲኖዳ ሳልሳዊ

 የነገረ መለኮት ንጽጽር  (በኦርቶዶክስና በፕሮቴስታንት): የወደደ  ሁሉ በነጻ እንዲጠቀምበት ተፖስቷል። ይሁን እንጂ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ስለሆነ በየትኛውም መልኩ ለንግድ እንዲውል አልተፈቀድም። ልዩ ልዩ መግቢያ የሚለውን መጀመሪያ ካነበቡ በኋላ የተቀረውን በተመረጠው ቅደም ተከተል ማንበብ ይቻላል። ልዩ ልዩ መግቢያ   ጥምቀት   ትውፊት (ወግና ልማድ)   መካከለኝነት   ጾም የድንግል ማርያም ክብሯና ዘላለማዊ ድንግልናዋ መንፈሳዊ ስጦታዎችና በልሳኖች የመናገር ስጦታ   ሥርዐት ንስሐ

ጥምቀት

  ጥምቀት       (1) የጥምቀት ፍቱንነቱ (2) ማጥመቅ የካህን ተግባር ነው (3) የጥምቀት አስፈላጊነቱ (4) ጥምቀት በመንከር (በመጥለቅ) (5) የልጆች (የሕጻናት) ጥምቀትሳቦች (6) ተቃውሞዎች   ጥምቀት   በእኛ በኦርቶዶክስና በፕሮቴስታንቶች መኻል ጥምቀትን በተመለከተ ያሉት ልዩነቶች የጥምቀትን ትምህርት በአምስት ጉልህ   ፍሬ ነገሮች ሥር አጠቃሎ መነጋገር ይቻላል። (1)     የጥምቀት   አስፈላጊነቱ   ምንድነው? ፍቱንነቶቹስ (ጠቀሜታዎቹስ) ምንድናቸው? ኦርቶዶክስ ጥምቀት ‘ድኅነት’ን፣ ‘መንጻት’ን፣ ‘መጽደቅ’ን፣ የ‘ሕይወት መታደስ’ን እና በ’ክርስቶስ አካል አባል’ መሆን’ን መቀበያ መንገድ ነው ብላ ታምናለች። የፕሮቴስታንት ቤተ እምነቶች እንደሚሉት እነዚህን   መቀበያው “እምነት” ብቻ ነው። በ እምነት ብቻ መሆኑ ትክክል ከሆነ ታዲያ የጥምቀት አስፈላጊነቱ ምኑ ላይ ነው? የክርስትና ምልክት ብቻ መሆኑ ነውን? ወይስ “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው” (ማቴ 28:19-20) የሚለውን የጌታን ትዕዛዝ መታዘዝ ብቻ መሆኑ ነው? (2 ) ማነው ማጥመቅ ያለበት? በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጥምቀት የሚከናወነው በካህን ብቻ ነው። ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ግን የሰውን ክህነት ጨርሶ አይቀበሉም። ስለሆነም በእነርሱ ቤተ ክርስቲያን የሚያጠምቀው ካህን ወይም ቄስ ያልሆነ አገልጋይ ነው።   ይህ አገልጋይ የቤተክርስቲያኒቷ ሽማግሌ ወይም ሴት ሽማግሌ (የሴቶችን ሽምግልና ...