Skip to main content

Posts

Showing posts from January, 2024

ካውንስሉ ካስገደደው የሚስተካከል የጸሎት ጥያቄ ባይሆንም፦

  ካውንስሉ ካስገደደው የሚስተካከል የጸሎት ጥያቄ ባይሆንም፦ እነዚያ ሁሉ አባቶች ፣ የቤተክርስቲያን መሬዎችና፣ አዋቂዎች መክረው (ግራና ቀኙን አይተው) በካውንስሉ በኩል ካቀረቡት አስገዳጅ የጸሎት ጥያቄ የተሻለ አቅርቤአለሁ አልልም። ይሁን እንጂ የአደባባዩ ቢቀር የተሰማችሁ በየግላችሁ ብትጸልዩበት ይሆናል።በተባለው የሰላም መልዕክትና ጸሎት ጊዜም ልታስቡት ትችላላችሁ። “በአዲስ አበባ ያላችሁ ወንጌላውያን ተረጋጉ” በሚለው ጽሑፌ ያቀረብኩት የጸሎት ጥያቄ ነበር። ፋኖዎች የሃይማኖት እኩልነትን  የማክበር አቋማቸውን በተግባር ማሳየት እንዲችሉ እግዚአብሔር  አምላክ እንዲረዳቸው ለፋኖ  መነሳት ምክንያት የሆነው የዐማራ ሕዝብና ዎገኖቹ መጨፍጨፍና መፈናቀል ስለሆነ እግዚአብሔር ዐማራውንና ዎገኖቹን  እንዲታደግ ፥ ሊከፋፍሉትና ሊያጠፋት ሌት ተቀን የሚያደቡትን ምክራቸውን እንዲያፈርስ ፥ ኅይላቸውንም እንዲበትን ከኦርቶዶክሳውያን ጋር በበጎ ዐይን ለመተያየት እንዲያበቃንና ወንጌልን በመተባበር ወደ መዝራቱ በተለይ ዕዳሪ መሬት ወደ ማውጣቱ  ልቦቻችንን እንዲያዘነብል የብልጽግና የበላይነት ለረዠም ጊዜ ከቀጠለ ኢትዮጵያ ወደ አረማዊ አገርነት የመገስገስ  አደጋ ስለሚገጥማት ከዚያ እንዲታደጋት። እኛም ከኦርቶዶክሳውያኑ ጋር ሆነን ኢትዮጵያን ከዚያ  ለማትረፍ  በመሥራቱ እንዲያተጋን  እንጸልይ

ልቡን ለሕዝብ የሚያዘነብል መሪ ፍለጋ

  ልቡን  ለሕዝብ የሚያዘነብል መሪ ፍለጋ ለዚህ ሐተታዬ መነሻ የሆኑኝ የብጹእ አቡነ ኤርምያስ፣ የብጹእ አቡነ ሉቃስ እና የብጹእ  አቡነ አብርሃም  ንግግሮች ናቸው። እንደ ራሴ ግንዛቤ ከንግግሮቹ  ባገኘኋቸው ሦስት የዐማራ ሕዝብና ዎገኖቹ እይታዎች (እሴቶች) ላይ አትታለሁ።  መጀመሪያ ስለ ብጹኣን ጳጳሳቱ የተሰማኝን ልጻፍ፦ ሦስቱም ብጹአን አባቶች በንግግራቸው የብሔር ማንነታቸውን ሲገልጡ አልሰማሁም። ምናልባት መነኩሴ ማለት ለዚህ ዐለም ነገር የሞተ ማለት ሆኖባቸው ምድራዊውን የነገድ ነገር ስለማያስቡት ሊሆን ይችላል። ወይም ራሳቸውን ለኦርቶዶክሳውያንና እድል ፈንታው ከኦርቶዶክሳውያኑ ጋር ለሚወሰን ሕዝብ ሁሉ አባት አድርገው ስለሚያዩ ሊሆን ይችላል (የዐሳባቸውን መድረሻ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ማድረጋቸው  ለዚህኛው ምክንያት ክብደት ይሰጣል)። ሦስቱም ብጹአን አባቶች ለኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንና  ምዕመናኑ የሚገዳቸው ናቸው። በአቡነ ኤርምያስ በኩል የላሊበላ አብያተክርስቲያናት ጉዳት እንዳይደርስባቸው ብልሃት ያሉትን መምከራቸውና በሰበካቸው ስለሚገኘው ምእመናቸው  ችግር መጨነቃቸው ማሳያ ነው። አቡነ ሉቃስ ደግሞ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት ስለመቃጠላቸው፣ ገደማውያንና መነኮሳቱ ስለመገደላቸውና ፣ በአጠቃላይ ስለ ኦርቶዶክሳውያኑ መጨፍጨፉ ያሰሙት የቁጭት ቃል ይመሰክራል። አቡነ አብርሃም ከሕግ ውጭ የታሠሩ ኦርቶዶክሳውያን እንዲፈቱ ፣በሕግ አግባብ የታሠሩ ካሉም ፍትሕን  እንዲያገኙ መጠየቃቸው (ይፋ ባልሆነ መንገድ) ይኽንኑ ያሳያል።  በቀኖናዋ መሠረት እንጂ በሌላ ወገን ተጽዕኖ  ቤተክርስቲያን እንደማትሠራ ማረጋገጫ መስጠታቸውም ለቤተክርስቲያን የመቆማቸው የመጨረሻው መገለጪያ ነው።...