Skip to main content

Posts

Showing posts from February, 2024

ፋኖ ፡ በኢትዮጵያ የሃያ አንደኛው ምዕተ ዐመት ልዩ ክስተት

  ፋኖ ፡ በኢትዮጵያ የሃያ አንደኛው ምዕተ ዐመት ልዩ ክስተት  የኢትዮጵያን ሁኔታ ከዜና አቅራቢዎች  እንደሚከታተል ሰው በዚችው ጥቂት ዕድሜዬ በርካታ ፓለቲከኞች ተነስተው አይቼአለሁ። አስተዋጽኦዋቸውን በጓዳዬ ያደነቅኋቸው ብዙ ናቸው። ከእነዚህ መኻል ባስቀመጥኳቸው ሥፍራ ያላገኘኋቸው  አሉ።ድርጅቶቻቸውም  እንደዚያው የሆኑባቸው። ያዘንኩላቸውም ያዘንኩባቸው ይኖራሉ። ችግራቸውንና  ፈተናቸውን እነርሱ ያውቃሉ። እኔ በሩቅ ሆኜ የምከታተል ስለሆንኩ እሳቱ ምን ያህል እንደፈጃቸው ልረዳላቸው አልታደልኩም።  አሁን ላይ ከእነዚህ መኻል  የዐማራ ሕዝብና ዎገኖቹን ለማዳን ኃላፊነቱን በሚገባ እየተወጣ ያለውን ፋኖ፣ ለመለወጥ ወይም ለማደናቀፍ ወይም ጠልፎ ለመጣል የሚሠሩትን  ግን  ተቀይሜአቸዋለሁ። የዐማራ ስቃይን ለዘለቄታው  ማስወገድ እስከቻለ ድረስ ማንስ ፋኖን ቢመራው ምን ቸግሯቸዋል?  ቀጥታ በተጋድሎው ሥፍራ  ላይ ያሉት የፋኖ መሪዎች ያጎደሉት ምን ኖሮ ነው? እንደ እኔ ዐሳብ ይህን ትተው በመተባበሩ ላይ ቢያተኩሩ ለሁላችንም ድንቅ ይሆናል እላለሁ። ደግሞ ይኸንን ያጡታል ብዬ አላስብም። መተባበሩን ይመርጣሉም ብዬ አምናለሁ። ለማንኛውም በስፋት ሲዘገብ እንዳገኘሁት ፋኖዎች  ሞትን ሳይፈሩ፥ ደፍረው ፥ በነፍሳቸው ቆርጠው ጉልበታቸውን በደሊላዎች ሳያደክሙ  ገንዘብንም ሎሌያቸው እንጂ ገዥያቸው ሳያደርጉ  በቅርብም በሩቅም ባሉ ወንድሞቻቸው የሸፍጥና  የኅይል ሥራ ሳይርዱ የዐማራ ሕዝብና ዎገኖቹ እንዳይጐዳ እየተጠነቀቁለትና እርሱም እየደገፋቸው አብዛኞቹ መሪዎቹ ለዐማራ ሕዝብ በረከት ሲሉ  የግል ኢጎአቸውን በመዋጥ  ወደ መተ...