Skip to main content

Posts

Showing posts from October, 2025

ፓስተር ታምራት ኃይሌ፡ አመሰግናለሁ!

  እድማጭ ተመልካቾቼ እንደምን አላችሁ ? ቸርነቱ የማያልቅበት አምላክ ይመስገንና እኔ ደህና ነኝ።ዛሬ ፓስተር ታምራት ኃይሌ በቅርቡ ባሰማው “ ልመና ” ላይ ያለኝን አስተያየት አጋራለሁ። እንድትከታተሉልኝ በታላቅ ትህትና እጋብዛችኋለሁ። ባንቱ ገብረማርያም ነኝ ርእሱ ፡ ፓስተር ታምራት ኃይሌ ፡  አመሰግናለሁ ! (ከታምራት ላይኔ ጋር አይምታታ)   መነሻዬ ሰሞኑን ፓስተር በዩትዩብ ያቀረበው መልዕክት ነው። ማዳመጥ ለሚፈልግ ሊንኩን እያይዤዋለሁ። ፓስተር ታምራት ለመንግሥት፣ መንግሥትን ለሚዋጉና   እንዲሁም በዲያስፖራ ላለነው በወግ በወጉ አደራጅቶ ልመና አቅርቧል። መጀመሪያ ልመናውን በራሴ አገላለጽ በአጭሩ አኖረውና ከዚያ ወደ አስተያየቴ እገባለሁ፡፡   ልመና ፩፡   ለመንግሥት የቀረበ ብዙ ልጆች የወለደ አባት የሁሉን ልጆች ፍላጎት አስማምቶ ማርካት እንደሚቸግረው ሁሉ የሕዝቦች አባትና ጠበቃ የሆነው መንግሥትም የሁሉንም ሕዝቦች ፍላጎት መሙላት ሊያስቸግረው ይችላል። ዋናዎቹን በተመለከተ ግን ከእግዚአብሔርም ከሕዝብም የተሰጠው አደራ ስለሆነ ገሸሽ ሊያደርጋቸው አይገባም ይላል ፖስተር   ታምራት ኃይሌ  ሲጀምር። በመቀጠልም ዋናዎቹን እደራ ይዘረዝራል፦ አገርን ማልማትና የዜጎችን ሕይወት መቀየር   ዜጎች በአገራቸው በሰላም ሠርተው፣ ሐብት አፍርተውና ተጋብተው፣ ተዋልደው እንዲኖሩ የሰላምና የደኅንነት ዋስትና ማረጋገጥ   የአገርን ዳር ድንበር ከማናቸውም ወራሪ መጠበቅና አገርን...