እድማጭ
ተመልካቾቼ እንደምን አላችሁ? ቸርነቱ የማያልቅበት አምላክ ይመስገንና እኔ ደህና ነኝ።ዛሬ ፓስተር ታምራት ኃይሌ በቅርቡ ባሰማው “ልመና” ላይ ያለኝን አስተያየት አጋራለሁ። እንድትከታተሉልኝ በታላቅ ትህትና እጋብዛችኋለሁ።
ባንቱ
ገብረማርያም
ነኝ
ርእሱ፡ ፓስተር ታምራት ኃይሌ፡ አመሰግናለሁ! (ከታምራት ላይኔ ጋር አይምታታ)
መነሻዬ ሰሞኑን
ፓስተር በዩትዩብ ያቀረበው
መልዕክት ነው። ማዳመጥ ለሚፈልግ ሊንኩን እያይዤዋለሁ።
ፓስተር
ታምራት ለመንግሥት፣ መንግሥትን ለሚዋጉና እንዲሁም በዲያስፖራ ላለነው በወግ በወጉ አደራጅቶ ልመና አቅርቧል። መጀመሪያ ልመናውን በራሴ አገላለጽ በአጭሩ አኖረውና ከዚያ ወደ አስተያየቴ እገባለሁ፡፡
ልመና
፩፡ ለመንግሥት የቀረበ
ብዙ
ልጆች የወለደ አባት የሁሉን ልጆች ፍላጎት አስማምቶ ማርካት እንደሚቸግረው ሁሉ የሕዝቦች አባትና ጠበቃ የሆነው መንግሥትም የሁሉንም ሕዝቦች ፍላጎት መሙላት ሊያስቸግረው ይችላል። ዋናዎቹን በተመለከተ ግን ከእግዚአብሔርም ከሕዝብም የተሰጠው አደራ ስለሆነ ገሸሽ ሊያደርጋቸው አይገባም ይላል ፖስተር ታምራት ኃይሌ ሲጀምር። በመቀጠልም ዋናዎቹን እደራ ይዘረዝራል፦
- አገርን ማልማትና የዜጎችን ሕይወት መቀየር
- ዜጎች በአገራቸው በሰላም ሠርተው፣ ሐብት አፍርተውና ተጋብተው፣ ተዋልደው እንዲኖሩ የሰላምና የደኅንነት ዋስትና ማረጋገጥ
- የአገርን ዳር ድንበር ከማናቸውም ወራሪ መጠበቅና አገርን በሉዐላዊነት ማቆየት
- የሰላም ችግር ሲታይ ሳይውል ሳያድር ፈጥኖ ሰላምን መልሶ ማስፈን (ኢትዮጵያን ከዳር እሰከ ዳር የጥይት ድምጽ የማይሰማበት አገር ማድረግ) ናቸው።
ከዝርዝሩ
በኋላ፦
ከእግዚአብሔርም ከሕዝብም በተሰጠው በዚህ አደራ መሠረት የሕዝቦችን ጥያቄዎች አዳምጦ፣ የተፈለገውን መስዋእትነት ከፍሎም ቢሆን፣ ቢያስፈልግ “ወደ ኋላ አጎንብሶ” አሁን በአማራ ክልል፣ እንዲሁም ‘አነሱ-በዙ’፣ ‘ዳር ሆኑ-መኻል’ ሳይባል በሌሎችም ክልሎች ያለውን ጦርነት መንግሥት በአስቸኳይ እንዲቆም እንዲያደርግ ይለምናል። በልመናው ውስጥ የሕዝቦችን ሰላምና አንድነት መጠበቅን እንዲሁም የልማት አውታሮችንና የሕዝብ ንብረትን ከጥፋት መታደግ አስፈላጊነትን አስምሮባቸዋል።
ልመና
፪፡ መንግሥትን ለሚዋጉት፡
ተሞክሮችን ለማስረጃነት
ጠቅሶ - "ዛሬ ማሸነፍ እንዳለ ነገ መሸነፍ ስላለ ፣ ኃይል ዘላቂ መፍትሔ ያመጣ መስሏችሁ አትታለሉ፣ መነጋገሩን ብቻ አማራጭ አድርጉ። ምን ቢቸግራችሁ የኃይል አማራጭን አትጠቀሙ። እርግፍ እድርጋችሁ ተውት" ብሎ ይመክራቸዋል።
ልመና
፫: ለዲያስፖራው፡
ጦርነቱ
የሚጎዳው የራሳችሁን ወገን መሆኑን ተረድታችሁ እባካችሁ መከረኛውን ሕዝብ እንዲዋጋ አትቀስቀሱት በማለት ይማጸናቸዋል
ልመናዎቹ
እኔ እስከተረዳኋቸው ድረስ እነዚህ ናቸው። ያጎዳልኩት ካለ ይቅርታ እጠይቃለሁ።
አሁን
ወደ አስተያየቴ፡
ከልመናው
መንፈስ እንደምረዳው የኢትዮጵያ ሕዝብ ህመምና ስቃይ ፓስተር ታምራትን ያሳሳበው እንደሆነ ይነበባል። የመቃተት፣ የጩኸት ድምጽ ነው የጮኸው። ሕዝቡ እርፍ ብሎ እንዲኖርለት ይፈልጋል። ምናልባት ዘግይቷል ይባል እንደሆን እንጂ ለሥጋ ወገኖቹ ለኢትዮጵያውያን የተሰማውን የሃዘኔታና የርኅራሄ ስሜት በብልሃት ገልጧል እላለሁ። ከሕሊና ወቀሳም፣ ከታዛቢ ክስም ተርፏል ።
ለበርካታ
ፓስተሮችም ለሥጋ ወገኖቻቸው ለኢትዮጵያውያን የተቆርቋሪነት ስሜታቸውን በይፋ እንዲገልጡ መንገዱን ጠርጎላቸዋል ማለትም እችላለሁ። ልመናው የ"ወንጌላውያን ካውንስሉንም" ዐይን ይገልጣል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።
መንግሥትን
ለሚወጉትና
ለዲያስፓራው
የተናገረውን
ሐሳብ በተመለከተ ተመሳሳዩን ወይም ተቀራራቢውን ሐሳብ ከእኛ ሰፈር የተናገሩ ይገኛሉ ። ፓስተር ታምራት ግን በቅጡ አደራጅቶና አብራርቶ አቅርቦታል። ከዚህ የተነሳ እነዚያ መንግሥትን የሚዋጉትና “ጦርነት ቀስቃሽ” የሚላቸው ዲያስፖራዎችም ልመናውን ለመረዳት ይከብዳቸው አይመስለኝም።
መንግሥትን
በተመለከተ ኃላፊነቱን ማስታወሱና ሰበብ ሳያበዛ ይኸንኑ ኃላፊነት እንዲወጣ መለመኑ ሕሊናን የሚያድስ ነው። ምክንያቱም መንግሥትን የሚያንቆለጳጵሰው እንጂ መሠረታዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ የሚያሳስበው ድምጽ በይፋ እጅግም ከማይሰማበት ከእኛ ሰፈር የወጣ ነውና
ምን
አደከማችሁ፦ የትኞቹም ወገኖች ተግባራዊ እንዲያደርጉት የሚገደዱበትን መንገድ ባያውቅልንም (ያውቅ ከነበረም አልገለጠልንም) በበኩሌ ሐሳቡ እንደ ሐሳብ እፁብ ድንቅ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። በእርግጥ ሐሳቡን ሁሉም ላይገዛው፣ የለመናቸው ወገኖችም ላይሰሙት ይችላሉ የሚል ጥርጣሬ አለኝ ። እንደ ሐሳብ የወደድኩት መሆኔን ግን መሸሸግ አልተቻለኝም።
መደምደሚያ
ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ አገሬ ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ትልቅ ምስቅልቅል ውስጥ ትገኛለች። “ማመሰቃቀሉን
ማን ጀመረው?” ለሚል ጥያቄ፦ “ዶሮ ናት የቀደመችው ወይስ እንቁላል ነው የቀደመው?” የሚለውን ለመመለስ የሚከብደውን ያህል የሚከብድ አይመስምለኝም። ቢያንስ እየተዋጉት ካሉት ስለ"አንዳንዶቹ" በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል።
ወደ ጦርነት ከመግባታቸው በፊት ፖስተር በዘረዘረው አደራ መሠረት መንግሥት ሊመልስ ይገባቸው የነበሩ ጥያቄዎችን አቅርበው ስላልተመለሱላቸውና እንዳውም ጦርነት ስለተከፈተባቸው የመከላከል ጦርነት ውስጥ የገቡ ናቸው።
ማስተዳደር ቀላል እንዳልሆነ እገነዘባለሁ፡፡ነገር ግን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ
አሕመድ እንደ ነገሩን ሥልጣኑን የያዙት ለብዙ ጊዜ ተዘጋጅተውበት ነው። ብዙ ወንድና ሴት አማካሪዎችም አሏቸው።የትኛውም የቀደመ የኢትዮጵያ መሪ ያላገኘውን የሕዝብ ድጋፍ አግኝተው ነበር። አገሪቷ ሀብት የምታገኝበት ዘዴም ምንጩም በእጃቸው ነው ያለው። እልቆ መሳፍርት የሌለው የፕሮፓጋንዳ መስመር አላቸው።ማስተዳደር
ተስኖኛልም ሲሉ
አልሰማኋቸውም። ስለዚህ
አሁን በኢትዮጵያ የሚታየውን ምስቅልቅል ከመድረሱ በፊት ዘዴ ሊያበጁለት በቻሉ ነበር ለማለት ያስደፍረኛል።ሆኖም ሳያደርጉት
ቢቀሩ ይሆናል እነሆ እዚህ ምስቅልቅል ላይ ደርሰናል።
ብቻ ያለፈው አልፏል።ምናልባት (እንዳው ምናልባት) አሁን የፓስተር ታምራት ኃይሌ ልመናን ሰምተው፣ ቢያስፈልግ “ወደ ኋላ አጎንብሰው” (የፓስተር ቃልን ልዋስና) ስህተቶችን ለማረም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይነሳሉ ብዬ ተስፋ ላድርግ። ያን ጊዜ የሚዋጉትም ያቆማሉ። ዲያስፖራዎችም ጊዚያቸውንና ገንዘባቸውን ለጦርነት ከማዋጣት ይታቀባሉ። ሰበብም ሆነ ምክንያት አይቀርላቸውምና። በእርግጥ ልመናውን ሰምተው ፋኖዎቹም ሆኑ ሌሎች መንግሥትን የሚወጉ ኃይሎች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ጠመንጃቸውን ወደ ታች ለማዘቅዘቅ ሊመርጡ ይችላሉ። “ጦርነት ቀስቃሽ” የተባልነው እኛም ዲያስፖራዎች እንዲሁ
ምላሳችንን።ግና የማሸነፍ ዕድል አለኝ የሚል ይህን ያደርግ ይሆን? አይጠበቅም።
ለማንኛውም ፖሰተር ታምራትን ለዚህ ሥራው ላመሰግነው እወዳለሁ። አመሰግናለሁ ፓስተር ታምራት! እግዚአብሔር ይስጥህ
እናንተን
አድማጭ ተመልካቾቼንም ስለተከታተላችሁኝ አመሰግናችኋለሁ! እግዚአብሔር ይስጣችሁ።
ሁሉ ቀን መልካም ቀን ይሁንላችሁ።
የሰማና
የወደደ ላልሰማ ያሰማ!
ያየና
የወደደ ላላየ ያሳይ!
ያነበበና
የወደደ ላላነበበ ያስኑብብ
ሰብስክራይብ ፣ሼር፣ ላይክ ፣ ደወሏን ይጫኑ እንዲሉ
ባንቱ ገብረማርያም
ጠ/ሚሩን እግዚአብሄርን አሳዝኗል| ይህ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያዬ ነው ይላል ጌታ| ፓ/ር ታምራት ሕይሌ ለጠ/ሚሩ የተናገሩት ከባድ ትንቢት|
Comments
Post a Comment