Skip to main content

Posts

Showing posts from November, 2025

ለፓስተር ግርማ ቤካ

ለፓስተር ግርማ ቤካ አድማጭ ተመልካቾቼ እንደምን አላችሁ ? እኔ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁንና ደህና ነኝ። ይህ   የአርሲ ኦርቶዶሳውያንን መገደል በተመለከተ   ለፓስተር ግርማ ቤካ የሚተላለፍ መልእክቴ ነው።   ከታች ልናገርባቸው ያሉትን ጉዳዮች በዩትዩብ ሲናገር የሰማሁት እርሱን ነውና። ይሁን እንጂ ከግርማ ቤካ ሐሳቦች ብዙውን የሚጋሩ ፓስተሮች እንዳሉ እገምታለሁ።ስለዚህ መልዕክቴ ለአንድ ሰው የተላለፈ ቢሆንም፣ ተመሳሳይ ሐሳብ ላላቸውም የሚዛመት ነው። በሌላ በኩል ግን ሐሳቡን ጨርሶ የማይጋሩት   የወንጌል አማኝ ፓስተሮች   እንዳሉም ከግርማ ቤካ ንግግር መረዳት ይቻላል።   የአርሲ ኦርቶዶክሳውያን ጭፍጨፋ አሳሳቢ ነው። ጉዳዩን የሰብዐዊ መብት ተሟጋቾች እንዲይዙትና ክትትል እንዲያደርጉበት ተስፋ አደርጋለሁ። በዚህ አጋጣሚ   ቤተሰብ   የተገደለባቸውን እግዚአብሔር አምላክ ያጽናናችሁ፣ የአርሲ  ሕዝብንም አይዟችሁ ፥ የአብርሃም አምላክ ያያችኋል  ለማለት እወዳለሁ።    ይህን ካልኩ በኋላ የፓስተር ግርማ ቤካን  ሐሳብ ነጥብ በነጥብ   እያነሳሁ    ፣ በየነጥቡ ሥር   የራሴን አጭር መልስ እሰጣለሁ፤ ማብራሪያዬንም አስከትላለሁ። አቀራረቡ እስከመጨረሻው እንደዚህ ይቀጥላል። በስፋት ከተደመጠ ቀና  ውይይት ይከፍታል ብዬም አምናለሁ። የተወደድክ ወንድሜ ፓስተር ግርማ ቤካ፡ - ለጤናህ እንደምን አለህ ? እኔ ቸርነቱ የማያልቅበት እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን ደህ...