አማትና ሥነ-ሥርዐት (ከMAY 2014 / REALSIMPLE.COM pp178-184) (በጽሑፉ የተመለከቱትን ጠበብት ማንነት ለማወቅ ለሚፈልግ በመጨረሻ ማስታወሻ ተሰጥቷል) በሚስቱና በእናቱ መኻል የሚኖረው ግንኙነት ብዙ ጊዜ ውጥረት የተሞላበት የሚሆነው ለምድነው? ስለዚህ የተወሳሰበ ግንኙነት አዲስ እይታና፣ ግንኙነቱን ለማሻሻል የሚረዳ ብልሃት አለ ወይ? የ”ሪይል ሲምፕል” መጽሔት አጠናቅሮ መልስ ይሰጣል። የሥነ ልቦና ባለሙያዋ ቴሪ አፕተር (2009) በአንድ ጥናታቸው ካካተቷቸው ሴቶች ከመቶዎቹ መኻል ስልሳዎቹ ምራት አማትን፣ አማትም ምራትን ‘ክፉ ነች’፣ ‘ቆሽቴን ታሳርረዋለች’ ፣ ‘አትመቸኝም’ በማለት የግንኙታቸውን ጎርባጣነት ገልጠዋል። ‘ሪል ሲምፕል’ መጽሔት አሰሳዊ ጥናትም ያሳየው ተመሳሳይ ነገር ነው። ስማቸውን ባልገለጡ 3700 ምራቶች እና 900 አማቶች ለ‘ሪይል ሲምፕል’ መጽሔት አዘጋጆች አማትና ምራት አንዳቸው ስለሌላቸው የሚሰማቸውን ገልጠው ነበር። የአሰሳ ጥናቱ በስድስት ጉዳዪች ዙሪያ ሲያጠነጥን ውጤቱ እንደሚከተለው ነበር። አርባ ስምንት ከመቶ ምራቶች ጥርሳቸውን ለማስነቀል የጥርስ ሐኪማቸውን መጎብኘት ከሚፈሩት ይልቅ አማታቸውን መጎብኘት እንደሚፈሩ ተናግረዋል። ምራት የምትበጠበጥበት ትልቅ ነገር አማቴ በጎ ዐሳቢ መስላ ትጎዳኛለች ማለቷ ነው።ሰላማዊና ደህና የሚመስለው የአማቷ ንግግር/ሥራ ያስቀይማታል። አማት የምትበጠበጥበት ትልቁ ችግር ምራት ከባሏ ወላጆች ይልቅ ከራሷ ወላጆች ጋር የበለጠ ጊዜ ታሳልፋለች እና ለእነርሱ ታዳላለች፣ እኔን ታገለኛለች ብላ ማሰቧ ነው። አፐርም ባደረጉት ጥናት ሁለት ሦስተኛ አማቶች ምራቴ ታ...