Skip to main content

Posts

Showing posts from December, 2023

ፋኖ ያሸንፍ

ፋኖ ያሸንፍ! ባለፈው ጊዜ “ፋኖ እንዲያሸንፍ ለምን እንደምመኝ /እንደምፈልግ ጊዜ ካገኘሁ እጽፍበታለሁ ፤ እስከዚያው ግን ምኞቴ እንዲደርስ መርቁኝ “ ብዬአችሁ ነበር።  በአጭሩ፦ፋኖ እንዲያሸንፍ መመኘቴ “አንቺም ትሞቺብኝ ይሆን ወይ? (እንደ ተረቱ)” በሚባል አስተዳደር ላይ የተጠረቀመውን መዝጊያ ወለል  አድርጎ ይከፍታል” በሚል እሳቤ ነው። ("አንቺም ትሞችብኝ ይሆን ወይ" ማለት እንዲወድቅ የማይፈለግ ቅን መንግሥት ለማለት ነው። ተረቱን ለማወቅ የሚፈልግ በአስተያየት መስጪያ ላይ ይጠይቅ) እንደሚታወቀው የዐማራ ሕዝብና ዎገኖቹ ከበዳዮቹና ከአስጨናቂዎቹ ይታደጉት ዘንድ በቅርቦቹ አሥርት ዐመታት በኢትዮጵያ ለተነሱት መንግሥታት አቤቱታውን ሲያሰማቸው ኖሯል። ሰላማዊ በተባለ መንገድ ጥያቄውን አቅርቦላቸዋል። ይሁን እንጂ ሊከላከልለት የፈቀደ የመንግሥት አካል ብቅ አላለም። በችግሩ አላዘኑለትም። ያም ቀርቶ መሳለቂያ ባላደረጉት  ምንኛ መልካም በሆነ ነበር።  እንዳውም አሁን በመጨረሻ  በብዙ ሥጋት ውስጥ እያለ መንግሥት ራሱ “ወርሰህ ታጠቅ” ያለውን ጠመንጃ አስረክብ ብሎ ተነሳበት። ሌሎቹ ሳይነኩ ልዩ ኅይሉንም አፈረሰበት።ጦርም አዘመተበት።የዐማራ ሕዝብ ምን ምርጫ ነበረው? ምን ቀረው? የመከላከል ጦርነት ውስጥ ገባ። ለተጋድሎው ፋኖ ዐይነተኛ መሪው ሆኖ ብቅ አለ።እግዚአብሔር የዐማራን ሕዝብና ዎገኖቹን  ሊያስበው መጀመሩ ነው መሰለኝ ሁኔታዎች ተገጣጠሙና ፋኖ የዐማራን ሕዝብና ዎገኖቹን የሚወጉትን ኃይላት የሚገዳደር ኅይል ሆኖ ወጣ።ታዲያ በዚህ እራስን  የማዳን ጦርነቱ ነው ፋኖ እንዲያሸንፍ የፈለግሁት/የተመኘሁት።የአብርሃም አምላክና አምላክህ ይርዳህ ! ድሉን ይስጥህ ብዬዋለሁ።  ተሳስቼ ሊሆን ይችላል። ስ...

"የሚቀጠቅጥ በእኛ ላይ ወጥቶአል"

"የሚቀጠቅጥ በእኛ ላይ ወጥቶአል" የቀን እንቅልፍ ለምዶብኛል።እንደ ወትሮዬ ምሣዬን ከበላሁ በኋላ ድንክ አልጋዬ ላይ ጋደም አልኩ። ወዲያው እንቅልፍ አሸለበኝ።እንደ ሌላው ጊዜ አጭርና ጣፋጭ ሆኖ አልተሰማኝም። ህልም አይሉት፣ ቅዠት- ብቻ ቆየሁበት። አንድ ሰው ጎራዴውን ታጥቆ በግራጫ ፈረስ ላይ ጉብ ብሏል። ጀርባውን ለእኔ ሰጥቶ ስለነበር ፊቱ አልታየኝም።ማን እንደሆነ አልለየሁትም። ለምን እንደሆነ አላውቅም፤ ገና ሳየው “ፈረሱስ፣ ጎራዴውስ የራሱ ይሆን?” ብዬ ጠየቅሁ። ትንሽ ጊዜ ትክ ብዬ እንዳየሁት፦ «በዕቅዳችን መሠረት ኢምፓየራችንን ለመመሥረት እንፍጠን። ብዙ ሕዝብ ሊያልቅ ይችላል፣ ምንም ማድረግ አንችልም። ለመመሥረቱ ግን መፍጠን አለብን» ሲል ሰማሁት። ቀጥሎም፦ «ኢምፓየሮቻችንን ለመገንባት እንቅፋቶችን የምናስወግድበት ዘዴ አግኝቼአለሁ!»አለ ጮክ ባለ ድምጽ። እኔም:-«መጀመሪያ ኢምፓየር ሲል የሰማሁት መስሎኝ ነበር። አሁን ደግሞ ኢምፓየሮች ይላል።ምን ማለቱ ነው? አልዘባረቀም? ለመሆኑ የሚናገረው ለማንነው?» አልኩ። ወደ ቀኝ፣ ከቀኝ ወደ ግራ፣ ከዚያ ወደፊት አማትሬ ተመለከትሁ።ጥቋቁር ፈረሶቻቸውን ሽምጥ ለመጋለብ አቆብቁበው ያሉ ሦስት ሰዎችን ከፊት ለፊቱ አየሁ።ለካንስ የሚናገረው በተጠንቀቅ ለሚጠብቁት ለእነዚያ ሰዎች ኖሯል። አለቃቸው መሆኑ ይሆን? ለመጀመሪያው ሰው ተናገረ፦ «ወደ ጥንታዊቷ ኢትዮጵያ ውጣ ! ነገዶቿንና ጎሳዎቿን ሁሉ በጎጥ ፣ በቀበሌ ከፋፍላቸው፣ ክተፋቸው።እርስ በእርሳቸው እንዳይዳረሱ አድርጋቸው። ለመሰልቀጥና እንደፈለግን ለመጥረብ የሚመቸን እንደዚያ ሲሆኑ ነው። የሚቋቋሙበት አቅም ያጣሉ። ዳግመኛ የሚሰባሰቡበት 'ቡረሌ' እንዳያገኙም ነቅንቃቸው ። ፍጠንና ይኸንኑ አድርግ»ሲል ሰማሁት።የመጀመሪያው ሰውዬም ይኸንኑ ለማ...