Skip to main content

ፋኖ ያሸንፍ

ፋኖ ያሸንፍ!

ባለፈው ጊዜ “ፋኖ እንዲያሸንፍ ለምን እንደምመኝ /እንደምፈልግ ጊዜ ካገኘሁ እጽፍበታለሁ ፤ እስከዚያው ግን ምኞቴ እንዲደርስ መርቁኝ “ ብዬአችሁ ነበር። 

በአጭሩ፦ፋኖ እንዲያሸንፍ መመኘቴ “አንቺም ትሞቺብኝ ይሆን ወይ? (እንደ ተረቱ)” በሚባል አስተዳደር ላይ የተጠረቀመውን መዝጊያ ወለል  አድርጎ ይከፍታል” በሚል እሳቤ ነው። ("አንቺም ትሞችብኝ ይሆን ወይ" ማለት እንዲወድቅ የማይፈለግ ቅን መንግሥት ለማለት ነው። ተረቱን ለማወቅ የሚፈልግ በአስተያየት መስጪያ ላይ ይጠይቅ)

እንደሚታወቀው የዐማራ ሕዝብና ዎገኖቹ ከበዳዮቹና ከአስጨናቂዎቹ ይታደጉት ዘንድ በቅርቦቹ አሥርት ዐመታት በኢትዮጵያ ለተነሱት መንግሥታት አቤቱታውን ሲያሰማቸው ኖሯል። ሰላማዊ በተባለ መንገድ ጥያቄውን አቅርቦላቸዋል። ይሁን እንጂ ሊከላከልለት የፈቀደ የመንግሥት አካል ብቅ አላለም። በችግሩ አላዘኑለትም። ያም ቀርቶ መሳለቂያ ባላደረጉት  ምንኛ መልካም በሆነ ነበር።  እንዳውም አሁን በመጨረሻ  በብዙ ሥጋት ውስጥ እያለ መንግሥት ራሱ “ወርሰህ ታጠቅ” ያለውን ጠመንጃ አስረክብ ብሎ ተነሳበት። ሌሎቹ ሳይነኩ ልዩ ኅይሉንም አፈረሰበት።ጦርም አዘመተበት።የዐማራ ሕዝብ ምን ምርጫ ነበረው? ምን ቀረው? የመከላከል ጦርነት ውስጥ ገባ። ለተጋድሎው ፋኖ ዐይነተኛ መሪው ሆኖ ብቅ አለ።እግዚአብሔር የዐማራን ሕዝብና ዎገኖቹን  ሊያስበው መጀመሩ ነው መሰለኝ ሁኔታዎች ተገጣጠሙና ፋኖ የዐማራን ሕዝብና ዎገኖቹን የሚወጉትን ኃይላት የሚገዳደር ኅይል ሆኖ ወጣ።ታዲያ በዚህ እራስን  የማዳን ጦርነቱ ነው ፋኖ እንዲያሸንፍ የፈለግሁት/የተመኘሁት።የአብርሃም አምላክና አምላክህ ይርዳህ ! ድሉን ይስጥህ ብዬዋለሁ። 

ተሳስቼ ሊሆን ይችላል። ስለጦርነቱ ያለኝ አስተያየት  ይኸው ነው።ለመታረም ግን ዝግጁ ነኝ። (ዐማራን  የሚወጉት ኃይላት የሚሰጡትን ምክንያት ያልሰማሁ አይደለሁም)። 

ከዚህ ከተጋድሎው ፍትሐዊነቱ ባሻገር ፋኖ እንዲያሸንፍ የምሻበትን ሌሎች ምክንያቶች ከዚህ በታች  እዘረዝራለሁ።  

1. ጦርነቱ በፋኖ አሸናፊነት ከተደመደመ በዐማራ ሕዝብና ዎገኖቹ  ላይ የሚፈጸመው የግፍ ሥራ ያቆማል (ቀዳሚው ይህ ነው)።

2. የሁላችንም አባቶችና እናቶች የጋራ መሥዋዕትነት ከፍለውና በትጋት ሠርተው  ለጋራ ያወረሱንን አገር/መሬት ይኸኛው አካባቢ የእኔ ነው፣  ያኛው የአንተ አይደለም ሳይባባሉ ልጆቻችን በጋራና በእኩል መብትና ግዴታ ሊኖሩባት ፥ ሊባረኩባት የምትችል አገር የማግኘት ዕድል ይቀርብላቸዋል።

3.ወላጆች (ከተለያዩ  ነገዶች የሆኑ) በትዳር የወለዷቸው  ልጆችና የልጅ ልጆች ያለውዴታቸው የአባታቸውን ወይም የእናታቸውን ነገድ ከመምረጥ እንዲላቀቁና ከአንድ ዐይነት ነገድ ከተወለዱ ልጆች እኩል መብታቸውና ግዴታቸው እንዲከበር መንገድ ይጠርጋል።

4.የአንደኛውን ወይም የሁለቱንም ወላጆቻቸውን ነገድ የማያውቁ (ከተደፈሩ እናቶች ወይም  ከወሲብ ሠራተኞች በመወለዳቸው፥ ወይም  ነገዳቸውን ሳያውቁ ወላጆች ስለሞቱባቸው ወዘተርፈ) ከተቀሩት እኩል መብታቸውና ግዴታቸው እንዲከበር ዕድሎች ይገኛሉ

በቁጥር 2፣3፥4 መብት ሲባል ለምሳሌ፦

  •  በግልም፥ በማኅበርም ያለ ሥጋትና ያለአድልኦ ከቦታ ቦታ መዘዋወር፣ መሥራት ፣መኖርም መቻል        
  •  ሐብትና ንብረት ያለ ተገቢው ካሳ ወይም ተመጣጣኝ ምትክ  በጉልበት አለመቀማት 
  • የመንግሥት ሥራን ወይም አገልግሎትን ለማግኘት የዘር ወይም የሃይማኖት እድልኦ/ ልዩነት እለመደረግ። 
  • ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን በረከት ለመሆን ለሁሉም እኩል ዕድል ማግኘት 

ወዘተርፈ ለማለት ነው።

5 .አናሳ እየተባሉ የሚጠቀሱ ነገዶች በልዩ ልዩ ጫናና ደባ  ከመዋጥ /ከመሰልቀጥ ይተርፋሉ። 

6. የሃይማኖት ተቋማት የሌሎች አገልጋይ ከመሆን አደጋ ተርፈው በየፊናቸው የሚያመልኩትን አምላክ የሚያገለግሉ ይሆናሉ።

7. የልጅ ልጆቻችን በሞራል ስብራታችን ከመሳቀቅና ከማፈር ይተርፉልናል።እንደሚከተለው ከማለት ይሰወራሉ ለማለት ነው።

         << -ሰው እንደ እንስሳ ሲታረድ፣ቆዳው ሲገፈፍ፣የአካል ክፍል በአዋዜ እየተጠቀሰ ሲበላ

          -እናትና እህት ስትደፈር፣ 

          -ርጉዝ እህቱ ማኅጸኗ በስለት ተቀዶ ጽንሷ ሲጣል፣ 

          -ሕጻኗ ልጅ “ ወላሂ ዳግመኛ ዐማራ አልሆንም አትግደሉኝ ብላ እየለመነች ስትገደል

          -የወገኑ ቤት በላዩ ላይ ሲፈርስበትና በግፍ ሲፈናቀል  

መንግሥት እያየ መፍትሔ ሳይሰጥ ሲቀር፣ እንዳውም ተባባሪ ሲመስል ሕዝብ የት ሄዶ ነበር? 

እነዚህን ነገሮች እንዴት አልተጠየፈም? 

በተቃውሞስ እንዴት ምድርን አላንቀጠቀጠም?

እንደዚያ ኅላፊነት የጎደለው መንግሥት ሥልጣን ላይ እንዲቆይስ እንዴት ፈቀደ?

ትከሻውስ ጭቆናን እንዴት ቢለምደው ነው >> ብለው አይሳቀቁብንም፥ አያፍሩብንም ፥አይታዘቡንም ለማለት ነው።

8.የዐማራን ሕዝብ የሚወጉት  ቢያሸንፉ “ፍጻሜው ዘዴውን ያቆነጀዋል” በሚል ፈሊጥ  ( the end justifies the means ለማለት ነው) ያደረጉት ግፍ ሁሉ ትክክል እንደነበረ ተደርጎ ይተረካል። ፋኖ ቢያሸንፍ ግን እንደዚያ አይተረክም (ከተሳሳተ ትርክት አንድዬ ይጠብቀን)። 

አዎ ፋኖ ቢያሸንፍ “አንቺም ትሞቺብኝ ይሆን ወይ?” ለሚባል አስተዳደር ተጠርቅሞ የነበረው መዝጊያ ወለል ብሎ ይከፈታል። ስለዚህ የአብርሃም አምላክና አምላኩ እንዲያሸንፍ ይርዳው።  እናንተም እንጂ! አሜን!

ማስታወሻ፡፡

ከልጅነት እስከ ዕውቀት ዕድሜዬ ጦሱን ስላየሁና ስለሰማሁ ጦርነትን አልደግፍም። እዚህ ሳይደረስ በፊት  የዐማራ ሰቆቃ መፍትሔ አግኝቶ ቢሆንና ጦርነቱ ባይጀመር ኖሮ እጅግ መልካም በሆነ ነበር። አሁንም ቢሆን የዐማራ ሕዝብና ዎገኖቹ ጥያቄ መልስ አግኝቶ ጦርነቱ ቢቆም እወዳለሁ።



Comments

Popular posts from this blog

Comparative Theology የነገረ መለኮት ንጽጽር (በኦርቶዶክስና በፕሮቴስታንት)/ በብፁዕ ወቅዱስ ፖፕ ሲኖዳ ሳልሳዊ

 የነገረ መለኮት ንጽጽር  (በኦርቶዶክስና በፕሮቴስታንት): የወደደ  ሁሉ በነጻ እንዲጠቀምበት ተፖስቷል። ይሁን እንጂ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ስለሆነ በየትኛውም መልኩ ለንግድ እንዲውል አልተፈቀድም። ልዩ ልዩ መግቢያ የሚለውን መጀመሪያ ካነበቡ በኋላ የተቀረውን በተመረጠው ቅደም ተከተል ማንበብ ይቻላል። ልዩ ልዩ መግቢያ   ጥምቀት   ትውፊት (ወግና ልማድ)   መካከለኝነት   ጾም የድንግል ማርያም ክብሯና ዘላለማዊ ድንግልናዋ መንፈሳዊ ስጦታዎችና በልሳኖች የመናገር ስጦታ   ሥርዐት ንስሐ

የድንግል ማርያም ክብሯና ዘላለማዊ ድንግልናዋ

የድንግል ማርያም ክብሯና ዘላለማዊ ድንግልናዋ (1)  ድንግል ማርያምን ስለማክበር (2) ለጥያቄዎች መልስ (ሀ) ድንግሊትን ‘የወይን ግንድ (ተክል)’ና የ ‘ሕይወት በር’ የሚል ማዕረግ  ለምን እንሰጣታለን? (ለ) ወደ ድንግል ማርያም መጸለይ ትክክል ነው ወይ? (3) የድንግል ማርያም ድንግልና ዘላለማዊነት (4) ለተቃራኒ አስተያየቶች መልስ (ሀ) “የመጀመሪያ ልጇን” የሚለው ሐረግ (ለ) “ሚስትህ” የሚለው ሐረግ (ሐ) “አብረው ከመሆናቸው በፊት ጸንሳ ተገኘች” (መ) “የመጀመሪያ ልጇን እስክትወልድ አላወቃትም” (ሠ)  “ወንድሞቹ” የሚለው ሐረግ   የቅድስት ድንግል ማርያም  ክብሯ (1) ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ድንግል እመቤታችንን አያከብሩም፤ ደግሞም እንድታማልድላቸውም (እንድትማልድላቸውም)  አይጠይቋትም።ከእነርሱ ወገኖች አንዳንዶቹ እንዲያውም ጫጩቱ ከተፈለፈለ በኋላ ዋጋ ከሌለው የዶሮ እንቁላል ቅርፊት ጋር እስከሚያመሳስሏት ይደርሳሉ።ይህ የተጋነነ ማቃለል የመጣው ምናልባት ሮሜዋውያን ካቶሊኮች የተጋነነ ማክበር ስለሚያከብሯት ለዛ ተቃርኖ ከማሳየት አዝማሚያ ሊሆን ይችላል። ስለዚህም ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን አንዱንም የእርሷን በዓል አያከብሩም።  (2) አንዳንዶቹ የፕሮቴስታንት ወገኖች ድንግል ማርያምን “እህታችን” ይሏታል። (3) በተጨማሪ አንዳንዶቹ ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ጌታ ኢየሱስን በድንግልና ከወለደች በኋላ ከዮሴፍ ጋር ጋብቻዋን ፈጽማለች፤ የ‘ኢየሱስ ወንድሞች’  ወይም የ’ጌታ ወንድሞች’ ተብለው የተጠሩ ልጆችን ወልዳለች ይላሉ።  (4) ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ቤተክርስቲያናችን ለድንግል እመቤታችን የሰጠቻቸውን አንዳንድ የማዕረግ ስሞችም ይቃወማሉ።  (5) ድንግልን ያለማክበራቸው አንዱ...

ስለ "አስታዋሽ ጾምና በዐሉ" ጥያቄና መልስ

 ስለ "አስታዋሽ ጾምና በዐሉ" ጥያቄና መልስ  ለዐማራ ሕዝብና ዎገኖቹ፦ ሕልውናችንን-ነጻነትችንን የማረጋገጥና የማስቀጠል አንድነታችንን የመጠበቅና የማጠንከር  በእሴቶቻችን የመደሰት፣ እነርሱን የመንከባከብና የማስተዋወቅ  በረከታችንን የማብዛትና የማካፈል  ኃላፊነቶቻችንን በማኅበር ፣ በማስተዋልና በትጋት እንድንወጣ “ጾሙና በዐሉ" አስታዋሽ ባሕላዊ ምልክታችን ይሁንልን   ጥያቄ 1 ፡ አድማጭ ተመልካቾቻችን እንኳን ደህና መጣችሁ።የከበረ ሰላምታችን ይድረሳችሁ። ዛሬ የምንወያየው ከአቶ ባንቱ ገብረማርያም ጋር ይሆናል። አቶ ባንቱ በሙያው ፋርማሲት ነው። እንደነገረኝ በእምነቱ ደግሞ ባፕቲስት ነው።ለዐማራ ሕዝብና ዎገኖቹ ባሕላዊ ምልክት የሚሆን “ጾምና በዐልን” በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል። የምንወያየውም ስለዚሁ "ጾሙና በዐሉ" ምልክትነት ይሆናል።  አቶ ባንቱ ለመወያየት  ወደ እኛ በመምጣትህ አመሰግንሃለሁ። እንኳን ደህና መጣህ። አንተ እያልኩ ልቀጥል ወይስ አንቱ? መልስ 1፡ ዎገኔ፡   እንኳን ደህና ቆየኸኝ። ለአድማጭ ተመልካቾቻችሁም ሰላምታዬ ይድረስልኝ። አንተ በለኝ። የሚያውቀኝ ሁሉ አንተ ነው የሚለኝ።  ጥያቄ 2 ፡ እሺ  አንተ እያልኩ እቀጥላለሁ። አቶ ባንቱ፣ ምናልባትም ብዙ ሰው ስለማያውቅህ  እስቲ ስለራስህ በአጭሩ ንገረን። ወዲያውም መክፈቻ ይሆነናል መልስ 2 ዎገኔ ፦ አስቀድሜ ይኸን ዕድል ስለሰጠኸኝ ላመሰግንህ እወዳለሁ። አድማጭ ተመልካቾችህንም ጊዜ ወስደው  ውይይቱን  ስለሚከታተሉ ላመሰግናቸው እወዳለሁ።አዎን፣ ባንቱ ገብረማርያም እባላለሁ።እንደነገሩኝ የተወለድኩት ሽርካ በዛሬ አጠራሩ በአርሲ ዞን ነው።ነፍስ ያወቅሁትና ትምህርት ...