ደግሞ ባንዳ /ሆዳም በሉኝ አሉ! ማህበራዊ አንቂ አይደለሁም። ለዐማራ ሕዝብና ዎገኖቹ ግን ተቆርቋሪ ነኝ። እንዳውም ለዘለቄታው ይጠቀምበታል ያልኩትና እያስተዋወቅሁት ያለ የራሴ ዐሳብ አለኝ። በመቀጠል የምጽፈው ስለ ዐማራና ዎገኖቹ ነው። ዐማራ ነኝና። ስለ ሌሎች ነገዶችና ጎሳዎች የሚፈቀድልኝ ስላልመሰለኝ አልጽፍም። ታዲያ ባንጠቀምባቸው ወይም እጅግ በተመጠነ ልክ ብቻ ብንጠቀምባቸው የምላቸው ሁለት ቃላት (ከእነርሱ ተቀራራቢ የሆኑቱን ሁሉ ማለቴ ነው) አሉ። እነርሱም “ባንዳ” ና “ሆዳም“ የሚሉት ናቸው።የምጽፈው እነርሱን የታከከ ነገር ነው። ከጠላት ጋር በማበራቸው ምክንያት በታሪክ ባንዳ ተብለው የሚጠሩ መኖራቸውን አላጣሁትም። የወገኑን ነጻነት የማረጋገጥ ሥራን አሳንሶ፣ የአጭር ጊዜ የግል ጥቅም ማግኘትን አግዝፎ መያዝና ለተጋድሎው እንቅፋት መሆን ሆዳም ሊያሰኝ እንደሚችልም እረዳለሁ።ስንጠቀምባቸው ምናልባት በዚህ እሳቤ ቃኝተን እንደሆነም እገምታለሁ። ይሁን እንጂ አንድ ዎገን በዐሳብ ሊለይ ይችላል።ተቀባይነት ያለውን ዐሳቡን ተቀባይነት ወደ ሌለው ሊለውጥም ይችላል። ተቃራኒ የሆነ ዐሳቡን ትቶ የሚቃረነውን ዐሳብ ሊቀበል ይችላል። በርካታ ሰው “ዐማራ” ነኝ የሚለውን ማንነት ለማስታወስ ወይም ለመቀበል እንኳ ምን ያህል ጊዜ እንደፈጀበት ልብ ይሏል። ሁሉም የዐማራ ሕዝብና ዎገኖቹ በአንድ ጊዜ በአንድ መስመር ላይ ይገኛል ለማለት ትልቅ ድፍረትን ይጠይቃል። ስለዚህ የራስን ዎገን እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ አድርጎ ባንዳ/ሆዳም እያሉ ፈርጆ ስብዕናውን መግደል - ባንዳ በሚለውና በሚባለው መኻል ያለውን ልዩነት ያሳይ እንደሆነ እንጂ - ለዐማራው ምን ይጠቅመዋል? በተ...