Skip to main content

መርጠው ያልቅሱበት

 መርጠው ያልቅሱበት

መጀመሪያ መርጦ የማልቀስ ምሳሌዎች ናቸው ያልኳቸውን ልጻፍ፦
*ለወንጌላውያን የቀብር ቦታ አይከልከል፣ ለሁሉም ይፈቀድላቸው!
*ስደት ይከልከልልን!
*የሽርካ ኦርቶዶክሳውያንን መግደል ይቁም!
*የኩሪፍቱ ቃለ ሕይወት ማዕከል አይወሰድ!
*በዝቋላ መነኮሳት ግድያ መፈጸሙ አሰቃቂ ነው፣ ወንጀለኛው ይታወቅ፤ ይቀጣም!
*በምዕራብ የአገራችን ክፍል የመሠረተ ክርስቶስ አባላትን የገደሉ ይያዙ፣ ይቀጡ!
*በዚያው ዞን የመካነ ኢየሱስ ምዕመናንን ከጸሎት ሥፍራ ወስደው የገደሉ ይያዙ፣ይቀጡም!
*ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ ኃላፊነታቸውን በሚገባ አልተወጡምና በኃላፊነት ይጠየቁ!
*ለሰላማችን መጥፋት ምክንያት ነውና አሸባሪዎች ስለ አመጽ ሥራቸው ይወገዙ!
*ታዬ ደንደአ መታሰሩና ቤተሰቡ ለችግር መዳረጉ ፍትሐዊ አይደለም! ይለቀቅ!
*እውነትን ስለተናገሩ አቶ ታዲዎስ ታንቱን ማሰሩ ሕገወጥ ድርጊት ነው ይፈቱ!
*በምሥራቁ የአገራችን ክፍል ታሪካዊው የመካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ሕንጻ አይወረስ! ወዘተርፈ
መርጦ ማልቀስ የሚባለው እነዚህና እነዚህን የመሳሰሉትን ጥያቄዎች ችግሮቹ እንደተከሰቱ መጠየቅ መስሎኛል። ካልሆነ እታረማለሁ። ታዲያ እንዲህ ዐይነቱን ጥያቄ አትጠይቁ የሚሉ የተከበሩ ዎገኖችን በየዩትዩቡ ተመልክቼአለሁ።
በደፈናው “የኢትዮጵያውያን ሰላም፣ እኩልነትና ነጻነት ይረጋገጥ በሉ! መርጣችሁ አትጠይቁ” ማለታቸው ሆኖ ተሰምቶኛል። እንዳውም ችግር እንደተከሰተ ስለዚያ የሚጠይቁትን ፣ በሽሙጥ “መርጦ አልቃሾች” የሚል ስም በመለጠፍ “ዐይነ አፋር” ሊያደርጓቸውም ይሞክራሉ።ይህን ሲያደርጉ “የሰው ሁሉ አፍቃሪ ፣ መልካም ሰዎች፣ አድልኦ እማያውቃቸው” እንደሆኑ ስለራሳቸው ሳይሰማቸው አይቀርም» መርጦ ድጋፍ መስጠትን “ከፉፉይ ዐሳብ” የሚያደርጉትም ይመስላል።
ለእኔ ግን “መርጣችሁ አታልቅሱ” ማለት “ለማንም አታልቅሱ!” የማለት ያህል ኃላፊነት የመሸሽ ብልሃታዊ አነጋገር ሆኖ ይሰማኛል። “መርጦ አጥቂና መርጦ አበልጻጊ” እስካለ ምን ማድረግ ይቻላል? በቃ መርጠው ያልቅሱበት፣ እንተዋቸው። “ለሁሉም ነው የምንቆረቆረው” የሚሉም ይሻላል እስካሉ ድረስ “አድበስብሰው” ያልቅሱ።ሆኖም አድበስባሾቹን መጠርጠር አይቻልም ትላላችሁ? ለውጥ እንዲመጣ የማይፈልጉ እንዳይሆኑ?

Comments

Popular posts from this blog

Comparative Theology የነገረ መለኮት ንጽጽር (በኦርቶዶክስና በፕሮቴስታንት)/ በብፁዕ ወቅዱስ ፖፕ ሲኖዳ ሳልሳዊ

 የነገረ መለኮት ንጽጽር  (በኦርቶዶክስና በፕሮቴስታንት): የወደደ  ሁሉ በነጻ እንዲጠቀምበት ተፖስቷል። ይሁን እንጂ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ስለሆነ በየትኛውም መልኩ ለንግድ እንዲውል አልተፈቀድም። ልዩ ልዩ መግቢያ የሚለውን መጀመሪያ ካነበቡ በኋላ የተቀረውን በተመረጠው ቅደም ተከተል ማንበብ ይቻላል። ልዩ ልዩ መግቢያ   ጥምቀት   ትውፊት (ወግና ልማድ)   መካከለኝነት   ጾም የድንግል ማርያም ክብሯና ዘላለማዊ ድንግልናዋ መንፈሳዊ ስጦታዎችና በልሳኖች የመናገር ስጦታ   ሥርዐት ንስሐ

የድንግል ማርያም ክብሯና ዘላለማዊ ድንግልናዋ

የድንግል ማርያም ክብሯና ዘላለማዊ ድንግልናዋ (1)  ድንግል ማርያምን ስለማክበር (2) ለጥያቄዎች መልስ (ሀ) ድንግሊትን ‘የወይን ግንድ (ተክል)’ና የ ‘ሕይወት በር’ የሚል ማዕረግ  ለምን እንሰጣታለን? (ለ) ወደ ድንግል ማርያም መጸለይ ትክክል ነው ወይ? (3) የድንግል ማርያም ድንግልና ዘላለማዊነት (4) ለተቃራኒ አስተያየቶች መልስ (ሀ) “የመጀመሪያ ልጇን” የሚለው ሐረግ (ለ) “ሚስትህ” የሚለው ሐረግ (ሐ) “አብረው ከመሆናቸው በፊት ጸንሳ ተገኘች” (መ) “የመጀመሪያ ልጇን እስክትወልድ አላወቃትም” (ሠ)  “ወንድሞቹ” የሚለው ሐረግ   የቅድስት ድንግል ማርያም  ክብሯ (1) ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ድንግል እመቤታችንን አያከብሩም፤ ደግሞም እንድታማልድላቸውም (እንድትማልድላቸውም)  አይጠይቋትም።ከእነርሱ ወገኖች አንዳንዶቹ እንዲያውም ጫጩቱ ከተፈለፈለ በኋላ ዋጋ ከሌለው የዶሮ እንቁላል ቅርፊት ጋር እስከሚያመሳስሏት ይደርሳሉ።ይህ የተጋነነ ማቃለል የመጣው ምናልባት ሮሜዋውያን ካቶሊኮች የተጋነነ ማክበር ስለሚያከብሯት ለዛ ተቃርኖ ከማሳየት አዝማሚያ ሊሆን ይችላል። ስለዚህም ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን አንዱንም የእርሷን በዓል አያከብሩም።  (2) አንዳንዶቹ የፕሮቴስታንት ወገኖች ድንግል ማርያምን “እህታችን” ይሏታል። (3) በተጨማሪ አንዳንዶቹ ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ጌታ ኢየሱስን በድንግልና ከወለደች በኋላ ከዮሴፍ ጋር ጋብቻዋን ፈጽማለች፤ የ‘ኢየሱስ ወንድሞች’  ወይም የ’ጌታ ወንድሞች’ ተብለው የተጠሩ ልጆችን ወልዳለች ይላሉ።  (4) ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ቤተክርስቲያናችን ለድንግል እመቤታችን የሰጠቻቸውን አንዳንድ የማዕረግ ስሞችም ይቃወማሉ።  (5) ድንግልን ያለማክበራቸው አንዱ...

ከቄስ ( ዶ/ር ) ቶሎሳ ይልቅ

 አድማጭ ተመልካቾቼ አንደምን ከረማችሁ? የአብርሃም አምላክና አምላካችን የተመሰገነ ይሁንና እኔ ደህና ነኝ።"ከቄስ (ዶ/ር ) ቶሎሳ ይልቅ" በሚል ርዕስ ያዘጋጀሁትን  የሚከተለውን መልዕክቴን እንድትከታተሉልኝ በታላቅ አክብሮት እጠይቃችኋለሁ። ባንቱ ገብረማርያም ነኝ ከቄስ (ዶ/ር) ቶሎሳ ይልቅ           ቄስ (ፓስተር) ዶ/ር ቶሎሳ  ጉዲና የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን በአትላንታ/ጆርጂያ ፓስተር መሆናቸው በብዙዎች ዘንድ የሚታወቅ ይመስለኛል። በበኩሌ የማከብራቸውም ሰው ናቸው። በወንጌላውያን መኻል ለበርካታ ዐመታት ለኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት የተናገሩ፣ ያሳሰቡና የጸለዩ መሆናቸውን ሰምቼአለሁ።በነገዳቸው የተደራጁትን የወንዛቸው ልጆችን ወቀሳ ተቋቁመው ለመላው ኢትዮጵያዊ ሲጮኹ የኖሩ ናቸው።           ስለ እሬቻ የሰጡት ትምህርት እስከዛሬ እንደሞዴል የማየው ነው። እሬቻን እንዳይከተሉና እንዳያስፋፉ የአሁኖቹን የመንግሥት ዐላፊዎች የመከሩበትንም ጊዜ አስታውሳለሁ።           የወንጌላውያን ሽማግሌ ብቻ ሳይሆኑ በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ የአገር ሽማግሌ አድርጌ አያቸዋለሁ። ይህን መደላድል የማስቀምጠው ስለእርሳቸው ያለኝን አስተያየት ለማስታወቅና ይኸው ሐሳቤ የጸና መሆኑን ለማስጮህ ነው።አስተያየቴን አልጠየቁኝም፣ የሚጨምርላቸውም ሆነ የሚቀንስባቸው ነገር እንደማይኖርም ጠንቅቄ አውቃለሁ። መደላድሉን አስቀድሜ  ማስቀመጤ ወንድሞችንና እህቶችን “አይዟችሁ አትደንግጡ” ለማለት ያህል ነው። ...