Skip to main content

ጦርነትም ጊዜ አለው?

 ጦርነትም ጊዜ አለው?

በእኔ ላይ የእናቴ ተጽዕኖ እጅግ ከባድ ነው። ከ”ነገሩ ጦም እደሩ” ትለኝ ነበር እንጂ ፤ እንደ አንዳንድ ወላጆች “ተደብድበህ እንዳትገባ” አትለኝም ነበር። ለዚህ ነው ወታደር መሆን በሚደነቅበትና መሆን  በተለመደበት ማኅበረሰብ ባድግም፣ ወታደር የመሆን ፍላጎት ኖሮኝ የማያውቀው።ሙሉ ሰው ከሆንኩም በኋላ ዐሳቤ በወንጌል አገልግሎት ላይ ስለነበርና ይኼም የሚደረገው ስደትን ተቋቁሞ እጅን በማንም ላይ በአለማንሳት ነው ብዬ አምን ስለነበር ከጦረኝነት ዐሳብ ርቄ የኖርኩ ነኝ። ዛሬ ላይ ግን የዐማራ ሕዝብና ዎገኖቹ

  • መንግሥት አልጠበቀኝም፣ እንዳውም በስቃዬ እየተሳለቀብኝ ነው፥ 
  • ከእንግዲህ ወዲያ ተዘቅዝቄ አልሰቀልም ፥
  • እንደ እንስሳ አልታረድም፥ ቆዳዬ  አይገፈፍም፥ የአካል ክፍሌ በአዋዜ እየተወራረደ አይበላም፥
  • እህቴም እናቴም አትደፈርም፥ ጡቷም አይቆረጥም፥ 
  • እርጉዝ  እህቴ በስለት ተቀዳ ጽንሷ አይጣልም፥ 
  • ህጻኗ  እህቴ “ወላሂ ዳግመኛ ዐማራ አልሆንም አትግደሉኝ” ብላ አትለምንም፥
  • አልገደልም፥ በውርደትም አልቀበርም፥
  • አልፈናቀልም፥ አልዘረፍም በማለት  በአልሞት ባይ ተጋዳይነት (በተከላካይነት) ጦር ቢመዝ የማከላክል አልሆንም። እንዳውም ይኸንን  ለማድረግ ወስኖ ደግፈኝ ቢለኝ (ጡረተኛ ብሆንም እንኳ) በምችለው ከመደገፍ ወደኋላ አልልም። የማወራው ስለ ድል አይደለም። ድሉ ለእግዚአብሔር የሚተው ነው። ነገር ግን ሕልውናንና ነጻነትን ማጣትን እምቢ ስለማለት ነው። ከማኅበራዊ መገናኛዎች እንደምከታተለው ደግሞ የዐማራ ሕዝብና ዎገኖቹ ዛሬ ይኸንኑ ለማድረግ  ፋኖ ሆኖ  ወጥቷል። አበጀህ፣ እግዚአብሔር ይርዳህ  ብዬአለሁ።
  • ግልጽ ላድርገው- መከላከሉን ነው- በእርሱ የደረሰበትን በሌሎች እንዲያደርግ አይደለም። አዎን ተሳስቼ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን አሁን ላይ ያለኝን ይኸንን ስሜቴን መደበቅ አልተቻለኝም። ታዲያ “አደባባይ ማውጣት  ምን ያስፈልግሃል?” የሚል ጓደኛዬ ይኖር/ትኖር ይሆናል።"የዎገኔ ህመም ተሰምቶኝ ቢፈነቅለኝ ነው! አትፍረድብኝ/አትፍረጂብኝ" ከማለት ሌላ መልስ የለኝም። 




Comments

Popular posts from this blog

Comparative Theology የነገረ መለኮት ንጽጽር (በኦርቶዶክስና በፕሮቴስታንት)/ በብፁዕ ወቅዱስ ፖፕ ሲኖዳ ሳልሳዊ

 የነገረ መለኮት ንጽጽር  (በኦርቶዶክስና በፕሮቴስታንት): የወደደ  ሁሉ በነጻ እንዲጠቀምበት ተፖስቷል። ይሁን እንጂ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ስለሆነ በየትኛውም መልኩ ለንግድ እንዲውል አልተፈቀድም። ልዩ ልዩ መግቢያ የሚለውን መጀመሪያ ካነበቡ በኋላ የተቀረውን በተመረጠው ቅደም ተከተል ማንበብ ይቻላል። ልዩ ልዩ መግቢያ   ጥምቀት   ትውፊት (ወግና ልማድ)   መካከለኝነት   ጾም የድንግል ማርያም ክብሯና ዘላለማዊ ድንግልናዋ መንፈሳዊ ስጦታዎችና በልሳኖች የመናገር ስጦታ   ሥርዐት ንስሐ

የድንግል ማርያም ክብሯና ዘላለማዊ ድንግልናዋ

የድንግል ማርያም ክብሯና ዘላለማዊ ድንግልናዋ (1)  ድንግል ማርያምን ስለማክበር (2) ለጥያቄዎች መልስ (ሀ) ድንግሊትን ‘የወይን ግንድ (ተክል)’ና የ ‘ሕይወት በር’ የሚል ማዕረግ  ለምን እንሰጣታለን? (ለ) ወደ ድንግል ማርያም መጸለይ ትክክል ነው ወይ? (3) የድንግል ማርያም ድንግልና ዘላለማዊነት (4) ለተቃራኒ አስተያየቶች መልስ (ሀ) “የመጀመሪያ ልጇን” የሚለው ሐረግ (ለ) “ሚስትህ” የሚለው ሐረግ (ሐ) “አብረው ከመሆናቸው በፊት ጸንሳ ተገኘች” (መ) “የመጀመሪያ ልጇን እስክትወልድ አላወቃትም” (ሠ)  “ወንድሞቹ” የሚለው ሐረግ   የቅድስት ድንግል ማርያም  ክብሯ (1) ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ድንግል እመቤታችንን አያከብሩም፤ ደግሞም እንድታማልድላቸውም (እንድትማልድላቸውም)  አይጠይቋትም።ከእነርሱ ወገኖች አንዳንዶቹ እንዲያውም ጫጩቱ ከተፈለፈለ በኋላ ዋጋ ከሌለው የዶሮ እንቁላል ቅርፊት ጋር እስከሚያመሳስሏት ይደርሳሉ።ይህ የተጋነነ ማቃለል የመጣው ምናልባት ሮሜዋውያን ካቶሊኮች የተጋነነ ማክበር ስለሚያከብሯት ለዛ ተቃርኖ ከማሳየት አዝማሚያ ሊሆን ይችላል። ስለዚህም ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን አንዱንም የእርሷን በዓል አያከብሩም።  (2) አንዳንዶቹ የፕሮቴስታንት ወገኖች ድንግል ማርያምን “እህታችን” ይሏታል። (3) በተጨማሪ አንዳንዶቹ ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ጌታ ኢየሱስን በድንግልና ከወለደች በኋላ ከዮሴፍ ጋር ጋብቻዋን ፈጽማለች፤ የ‘ኢየሱስ ወንድሞች’  ወይም የ’ጌታ ወንድሞች’ ተብለው የተጠሩ ልጆችን ወልዳለች ይላሉ።  (4) ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ቤተክርስቲያናችን ለድንግል እመቤታችን የሰጠቻቸውን አንዳንድ የማዕረግ ስሞችም ይቃወማሉ።  (5) ድንግልን ያለማክበራቸው አንዱ...

ከቄስ ( ዶ/ር ) ቶሎሳ ይልቅ

 አድማጭ ተመልካቾቼ አንደምን ከረማችሁ? የአብርሃም አምላክና አምላካችን የተመሰገነ ይሁንና እኔ ደህና ነኝ።"ከቄስ (ዶ/ር ) ቶሎሳ ይልቅ" በሚል ርዕስ ያዘጋጀሁትን  የሚከተለውን መልዕክቴን እንድትከታተሉልኝ በታላቅ አክብሮት እጠይቃችኋለሁ። ባንቱ ገብረማርያም ነኝ ከቄስ (ዶ/ር) ቶሎሳ ይልቅ           ቄስ (ፓስተር) ዶ/ር ቶሎሳ  ጉዲና የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን በአትላንታ/ጆርጂያ ፓስተር መሆናቸው በብዙዎች ዘንድ የሚታወቅ ይመስለኛል። በበኩሌ የማከብራቸውም ሰው ናቸው። በወንጌላውያን መኻል ለበርካታ ዐመታት ለኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት የተናገሩ፣ ያሳሰቡና የጸለዩ መሆናቸውን ሰምቼአለሁ።በነገዳቸው የተደራጁትን የወንዛቸው ልጆችን ወቀሳ ተቋቁመው ለመላው ኢትዮጵያዊ ሲጮኹ የኖሩ ናቸው።           ስለ እሬቻ የሰጡት ትምህርት እስከዛሬ እንደሞዴል የማየው ነው። እሬቻን እንዳይከተሉና እንዳያስፋፉ የአሁኖቹን የመንግሥት ዐላፊዎች የመከሩበትንም ጊዜ አስታውሳለሁ።           የወንጌላውያን ሽማግሌ ብቻ ሳይሆኑ በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ የአገር ሽማግሌ አድርጌ አያቸዋለሁ። ይህን መደላድል የማስቀምጠው ስለእርሳቸው ያለኝን አስተያየት ለማስታወቅና ይኸው ሐሳቤ የጸና መሆኑን ለማስጮህ ነው።አስተያየቴን አልጠየቁኝም፣ የሚጨምርላቸውም ሆነ የሚቀንስባቸው ነገር እንደማይኖርም ጠንቅቄ አውቃለሁ። መደላድሉን አስቀድሜ  ማስቀመጤ ወንድሞችንና እህቶችን “አይዟችሁ አትደንግጡ” ለማለት ያህል ነው። ...