Skip to main content

Posts

Showing posts from August, 2024

“የአቤል ደም” እና “አብረን ሰው እንሁን”

“የአቤል ደም” እና “አብረን ሰው እንሁን” መግቢያ    የ“አቤል ደም” ጸሐፊ አባ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ሲሆኑ ፤ የ”አብረን ሰው እንሁን” ጸሐፊ ደግሞ ሰለሞን ጥላሁን (ፓስተር) የኢትዮጵያ ወንጌል አማኝ ነው።     የ"አቤል ደም" በእጄ የገባው በመሸጪያ ድንኳኑ ፊት ለፊት ሰልፍ አይቼ ፣ “ምን ቢሆን ነው” በማለት ሰልፉን ተቀላቅዬ ነው (በአትላንታው በአሜሪካ የኢትዮጵያውያን እስፖርትና ባህል በዐል ላይ ማለት ነው)።“አብረን ሰው እንሁን”ን ያገኘሁት አንድ ወዳጄ ልኮልኝ ነው (በዚህ አጋጣሚ ፓስተር ሰለሞንን አንድ ቅጂ ደርሶኛል አመሰግናለሁ ማለት እወዳለሁ)።       የአቤል ድምጽ እጄ ከመግባቱ ከሁለት ሳምንት ቀደም ብዬ “አብረን ሰው እንሁን”ን አንብቤው ነበር። የጽሑፌ ርዕስ ይኸንኑ የንባቤን ቅደም ተከተል (ከፊት ወደ ኋላ) የሚያንጸባርቅ ነው።         የመጽሐፍ ሐያሲ አይደለሁም። የምጽፈው ለማሔስ አይደለም፣ የተጻፈው ሁሉ ገብቶኛል፣ ዘልቄዋለሁ ብዬም አይደለም።ለወገኑና ለአገሩ ችግር መፍትሔ ተገኘ ብሎ ሰፍ እንዳለ ሰው በ"ፈጣን ንባቤ" ከመጽሐፎቹ የጨበጥኩትን ያህልና የተሰማኝን ለማካፈል ነው። በሳትሁትና በተሳሳትሁት ለመታረምና ለመማር ዝግጁ ነኝ ከመጽሐፍቱ የተማርኩት      ሁለቱም መጽሐፎች በርካታ ገጾች በመያዛቸውና ዐሳቦቹም ለእኔ አዲስ በመሆናቸው በማነብበት ወቅት በማስመር፣ በማድመቅ፣ በማክበብና በጥያቄ ምልክት ሞልቼአቸዋለሁ።       ያለጥርጥር እጅግ ብዙ የተደከመባቸው ናቸው።በንባቤ እንደተረዳሁት ከሆነ ሁለቱም ጸሐፊዎች “እኛን ኢትዮጵያውያንን ሰው እንሁን” ...

ተመልከት ዐላማህን ፣ ተከተል አለቃህን

  ተ መልከት ዐላማህን፣ተከተል አለቃህን የኢትዮጵያን ፖለቲካ ወሬ መከታተል የጀመርሁት የፕሪዝደንት መንግሥቱ ኃይለማርያም መውደቂያቃቸው ከተቃረበበት ጊዜ አንስቶ ነው።እቤቴ ድረስ አንኳኩቶ መጥቶ ነበርና። በጊዜው የዐማራ ጉዳይ   እየተነሳ የሚጣልበት ጊዜ ስለነበር እኔም ዐማራ እንደመሆኔ መጠን ነገሩ እየከነከነኝ አዳምጥ ጀመርሁ። ምንም እንኳ ራሴ ፖለቲካ ሥራ ውስጥ ባልገባም የእኛን የዐማሮችን ሕልውና ስለማስጠበቅ ሁለት መንገዶች ሲሠራባቸው ተከታትያለሁ። አንዱ የዐማራው ሕልውና   የሚረጋገጠውም ሆነ ሌሎቹ ችግሮቹ   የሚፈቱት ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር ተቀላቅሎ “በኢትዮጵያዊነት” በመደራጀትና   በመሥራት ነው የሚለው ሲሆን ሌላው ደግሞ “ዐማራ ለብቻው ተደራጅቶ የራሱን ሕልውና ማስከበር አለበት” የሚለው ነው። ሁለቱም መስመሮች ለእኔ እስከገባኝ ድረስ የኢትዮጵያን መኖርና አንድነት እንዲሁም ከሌሎቹ ብሔር ብሔረሰቦች ጋር በእኩልነት አብሮ መኖርን የሚደግፉ ናቸው። በዚያ ልዩነት ያላቸው አይመስለኝም።በመጀመሪያው መስመር ለዐማራው የሠሩ በርካታ ግለሰቦች ነበሩ። ዛሬ በእርግጥ የእነርሱ መስመር እንደ “አስጠቂ   መስመር” በመታየቱ ስማቸውን ለማንሳት እንኳ እንደማይመች እረዳለሁ።      ዛሬ ላይ አሸንፎ የወጣው ዐሳብ   “ዐማራ ሌሎች ሳይገቡበት ለብቻው ተደራጅቶ” ለራሱ ሕልውና መሥራት አለበት የሚለው ነው ።የተደባልቆው መስመር   ዐማራውን በአጥጋቢ ሁኔታ ያላዳነው በመሆኑ   የቀረው አማራጭ ይኸው ሁለተኛው መስመር ሆኗል። ዕድሜ ለፋኖና ለፋኒት   እውነትም ታዲያ ዐማራው በዚህኛው መንገድ ቢያንስ ድምጹ ይሰማ ጀምሯል።      ...

እኔም ለሄቨን

  እኔም ለሄቨን በወገኖቻችን ሕጻናትና ሴቶቻችን ላይ የሚፈጸመው ወሲባዊ ወንጀል “ምነው ኖረ? እንዴትስ ይቆም ይሆን?” በማለት ለብቻዬ ሳወጣና ሳወርድ የኖርኩት ጉዳይ ነው። ባሕላችን ይኸንን ጉዳይ የሚጠየፍ አድርጌ ስለምቆጥር ፤ ወንጀሉን የሚፈጽሙት የአገሬ ልጆች “ይኸንን ባሕል እንዴት ጣሱት? እኩይ ጠባዩንስ ከየት አመጡት? ምን ነካቸው?” ስልም ቆይቼአለሁ።በሄቨን ላይ የሆነው ጉዳይ ግን ድርብርብ ወንጀል ሆኖ ተሰምቶኛል። ከማኅበራዊ መገናኛ እንደተከታተልኩትም ታላቅና ተገቢ ቁጣን ቀስቅሷል። በተለይ ለፍትሕ ያለው ጩኸት እጅግ በግልጽ ይሰማል። ለቤተሰቧም የሃዘኔታ መልዕክት ጎርፏል። በቀጥታ ሄቨንን የተመለከተ ጉዳይ  ደግሞ አንድ ዘፈን በቴዲ አፍሮ ተዘፍኖ ሰምቼአለሁ።ድምጻዊት ቬሮኒካም (ዘፈን ሠፈር ስለማልውል አላውቃትም ነበር) በሄቨን ላይ በተፈጸመው ግፍ ምክንያት አልበሟ የሚወጣበትን ግዜ አራዝማለች።እኔ ያልደረስኩበት ሌላም ነገር ተደርጎ ሊሆን ይችላል።ይህ ሁሉ ሄቨንን ለማስታወስ መልካም ጅማሬ ነው። ነገር ግን የአሁኑን የሕዝብ ቁጣ ወደ ገምቢ ኃይልነት መለወጥ ይገባል እላለሁ። "በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ወሲባዊ ወንጀል ለተፈጸመባቸው ሁለ ፈዋሽ የሆነና ለወደፊቱም ወሲባዊ ወንጀልን ለመከላከል የሚያስችል መንግሥታዊ ያልሆነ እንቅስቃሴ በስሟ ቢጀመር ስሟ ለዘላቂ በረከት ይሆናል። አሁን የታየው ቁጣም   ወደ ጠቃሚ ኃይልነት ይለወጣል። የእርሷ ጉዳይ የአንድ ሰሞን መጯጯህ ብቻ ሆኖም አይቀርም። እንዲህ ዐይነቱ ነገር በእነርሱ ቢዘጋጅ ይሰምራልና ተጽዕኖ ፈጣሬ የሆኑ ግለሰቦች እባካቸው ተባብረው ይኸንን ዐይነት መንግሥታዊ ያልሆነ እንቅስቅሴን ያፍጥኑ" እላለሁ። ይቅርታ! ብቻ ለአዋቂ አይነግሩም፣ ለአንበሳ አይመትሩም። 

መርጠው ያልቅሱበት

  መርጠው ያልቅሱበት መጀመሪያ መርጦ የማልቀስ ምሳሌዎች ናቸው ያልኳቸውን ልጻፍ፦ *ለወንጌላውያን የቀብር ቦታ አይከልከል፣ ለሁሉም ይፈቀድላቸው! *ስደት ይከልከልልን! *የሽርካ ኦርቶዶክሳውያንን መግደል ይቁም! *የኩሪፍቱ ቃለ ሕይወት ማዕከል አይወሰድ! *በዝቋላ መነኮሳት ግድያ መፈጸሙ አሰቃቂ ነው፣ ወንጀለኛው ይታወቅ፤ ይቀጣም! *በምዕራብ የአገራችን ክፍል የመሠረተ ክርስቶስ አባላትን የገደሉ ይያዙ፣ ይቀጡ! *በዚያው ዞን የመካነ ኢየሱስ ምዕመናንን ከጸሎት ሥፍራ ወስደው የገደሉ ይያዙ፣ይቀጡም! *ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ ኃላፊነታቸውን በሚገባ አልተወጡምና በኃላፊነት ይጠየቁ! *ለሰላማችን መጥፋት ምክንያት ነውና አሸባሪዎች ስለ አመጽ ሥራቸው ይወገዙ! *ታዬ ደንደአ መታሰሩና ቤተሰቡ ለችግር መዳረጉ ፍትሐዊ አይደለም! ይለቀቅ! *እውነትን ስለተናገሩ አቶ ታዲዎስ ታንቱን ማሰሩ ሕገወጥ ድርጊት ነው ይፈቱ! *በምሥራቁ የአገራችን ክፍል ታሪካዊው የመካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ሕንጻ አይወረስ! ወዘተርፈ መርጦ ማልቀስ የሚባለው እነዚህና እነዚህን የመሳሰሉትን ጥያቄዎች ችግሮቹ እንደተከሰቱ መጠየቅ መስሎኛል። ካልሆነ እታረማለሁ። ታዲያ እንዲህ ዐይነቱን ጥያቄ አትጠይቁ የሚሉ የተከበሩ ዎገኖችን በየዩትዩቡ ተመልክቼአለሁ። በደፈናው “የኢትዮጵያውያን ሰላም፣ እኩልነትና ነጻነት ይረጋገጥ በሉ! መርጣችሁ አትጠይቁ” ማለታቸው ሆኖ ተሰምቶኛል። እንዳውም ችግር እንደተከሰተ ስለዚያ የሚጠይቁትን ፣ በሽሙጥ “መርጦ አልቃሾች” የሚል ስም በመለጠፍ “ዐይነ አፋር” ሊያደርጓቸውም ይሞክራሉ።ይህን ሲያደርጉ “የሰው ሁሉ አፍቃሪ ፣ መልካም ሰዎች፣ አድልኦ እማያውቃቸው” እንደሆኑ ስለራሳቸው ሳይሰማቸው አይቀርም» መርጦ ድጋፍ መስጠትን “ከፉፉይ ዐሳብ” የሚያደርጉትም ይመ...