Skip to main content

ተመልከት ዐላማህን ፣ ተከተል አለቃህን

 

መልከት ዐላማህን፣ተከተል አለቃህን

የኢትዮጵያን ፖለቲካ ወሬ መከታተል የጀመርሁት የፕሪዝደንት መንግሥቱ ኃይለማርያም መውደቂያቃቸው ከተቃረበበት ጊዜ አንስቶ ነው።እቤቴ ድረስ አንኳኩቶ መጥቶ ነበርና። በጊዜው የዐማራ ጉዳይ  እየተነሳ የሚጣልበት ጊዜ ስለነበር እኔም ዐማራ እንደመሆኔ መጠን ነገሩ እየከነከነኝ አዳምጥ ጀመርሁ። ምንም እንኳ ራሴ ፖለቲካ ሥራ ውስጥ ባልገባም የእኛን የዐማሮችን ሕልውና ስለማስጠበቅ ሁለት መንገዶች ሲሠራባቸው ተከታትያለሁ። አንዱ የዐማራው ሕልውና  የሚረጋገጠውም ሆነ ሌሎቹ ችግሮቹ  የሚፈቱት ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር ተቀላቅሎ “በኢትዮጵያዊነት” በመደራጀትና  በመሥራት ነው የሚለው ሲሆን ሌላው ደግሞ “ዐማራ ለብቻው ተደራጅቶ የራሱን ሕልውና ማስከበር አለበት” የሚለው ነው። ሁለቱም መስመሮች ለእኔ እስከገባኝ ድረስ የኢትዮጵያን መኖርና አንድነት እንዲሁም ከሌሎቹ ብሔር ብሔረሰቦች ጋር በእኩልነት አብሮ መኖርን የሚደግፉ ናቸው። በዚያ ልዩነት ያላቸው አይመስለኝም።በመጀመሪያው መስመር ለዐማራው የሠሩ በርካታ ግለሰቦች ነበሩ። ዛሬ በእርግጥ የእነርሱ መስመር እንደ “አስጠቂ  መስመር” በመታየቱ ስማቸውን ለማንሳት እንኳ እንደማይመች እረዳለሁ።

    ዛሬ ላይ አሸንፎ የወጣው ዐሳብ  “ዐማራ ሌሎች ሳይገቡበት ለብቻው ተደራጅቶ” ለራሱ ሕልውና መሥራት አለበት የሚለው ነው።የተደባልቆው መስመር  ዐማራውን በአጥጋቢ ሁኔታ ያላዳነው በመሆኑ  የቀረው አማራጭ ይኸው ሁለተኛው መስመር ሆኗል። ዕድሜ ለፋኖና ለፋኒት  እውነትም ታዲያ ዐማራው በዚህኛው መንገድ ቢያንስ ድምጹ ይሰማ ጀምሯል።  

    (በዚህ አጋጣሚ ለፋኖዎችና  ለፋኒቶች አድናቆቴን  ልገልጥ እወዳለሁ። በነፍሳቸው፣ በቤተሰባቸውና በኑሮአቸው ላይ ቆርጠው ፤ በቁጭት፣ በራሳቸው ተነሳሽነት ፣ ያለ ምንም ረብ ፍለጋ ለዐማራ ሕዝብ ሕልውናና ለትውልዱ ቀጣይነት ሲሉ ጫካ ለገቡትና ለሚገቡት ሁሉ ልባዊ አድናቆት አለኝ። አዎ በዚህ ዘመን በእርስ በእርስ ጦርነት መጠመድ ባልተገባም ነበር። ጉዳቱ “የገደለው ባልሽ የሞተው ወንድምሽ” እንዲሉ እንደሆነ ይሰማኛል።ነገር ግን  እስካሁን በዚህ መጠን ያልተሞከረው ብቸኛ  የዐማራ ሕዝብ መውጪያ  በር ይኸው ሆኖ ይታያል።ምናልባትም “የአብርሃም አምላክና አምላካችን የሚታደገን በዚኸኛው መንገድ ይሆንን?” ብያለሁ። አድማ ብተና ፣ ሚሊሺያ ፣ ፖሊስ የተባሉት የራሴ ወገኖች ከፋኖ/ከፋኒት ጋር ተቀላቅለው ቢያግዙ መስዋዕትነቱን ያሳንሰዋል፣ ያሳጥረዋልም እላለሁ። ወደ ፋኖዎቹ ማድላቴ! በብልጽግና ወገን ያሉቱ ለዐማራው ሕልውና መቆማቸውን የሚያሳይ ሥራ ሲሠሩ አለማየቴ ነው(ዕውር ግን አይደለሁም)።

    ታዲያ ወደ ተነሳሁበት ነጥቤ ልመለስና፦ የፋኖዎችን ጫካ መግባት ተከትሎ በየአካባቢው በርካታ የዐማራ ፋኖ መሬዎች ተወልዳችኋል። ከባዱን  የመምራት ኅላፊነት ተቀበላችሁ የፋኖ ኃይልን  በአስገራሚ ብቃት እየመራችሁ በመሆኑ በየእርከኑ ያላችሁትን የፋኖ መሪዎች በማመስገን ጽሑፌን እንድቀጥል ይፈቀድልኝ።

    አስተያየቴ በፖለቲካ ውስጥ ያለውን የሥልጣን ጉጉት፣ ፉክክር ፣ ሴራ፣  ውጥንቅጥ  ወዘተርፈ ባለመረዳቴ ሊሆን ይችላል። የምሰጠው አስተያየት በሞቀ ቤቴ ተቀምጪም ስለሆነ እንደ ድፍረት እንዳትቆጥሩብኝ ልመናዬን አስቀድሜ አቀርባለሁ። አንዳንዶች የፋኖ መሪዎች አንዳንዶችን  መሪዎች ስለሚቃወሙት ጉዳአስተያየት አለኝ። እንደ ተራ ደጋፊ ወይም እንደ ተራ ተከታይ የማስበው  ነው።

    የምከተላችሁ ከዐማራ ዐላማ ጋር በሚስማማው ሥራችሁና አቋማችሁ እንጂ ስለምትቃወሙት መሪ ወይም ግለሰብ አይደለም። ሌላው ቀርቶ  የምደግፋችሁ ወይም የምከተላችሁ ዶ/ር ዐብይን በመቃወማችሁ ምክንያት አይደለም።ይኼ ጨርሶ ከእኔ ይራቅ። የምደግፋችሁ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ለዐማራው የማይሠሩ (እንዳውም ዐማራውን የሚያምቁ አድርጌ እጠረጥራቸው ጀምሬአለሁ) መሪ ሆነው ስለታዩኝና እናንተ የፋኖ መriዎች ግን ለዐማራው ታዋጡታላችሁ በማለት ነው። ለዚህ ዐላማ እስከሠራችሁ ድረስ ማናችሁም የዐማራ ፋኖ መሪዎች መሪዎቼ ናችሁ። በቃ ይኸው ነው።

    ታዲያ  እኔ ይህን ልበል እንጂ አንዳንድ የፋኖ መሪዎች  አንዳንዶቹን የፋኖ መሪዎች ተቃውማችኋል ሲባል እሰማለሁ።ይኸንን  ለእኔ ማሰማታችሁ ምን ይረባኛል? ለዐማራው ጥያቄ መልስ ለማስገኘትስ ምን ይፈይድለታል? ለተቀሩት  ኢትዮጵያውያንስ ምን  ተስፋ ይዞላቸው ይመጣል? ልዩነት ካላችሁ እናንተው  በመኻከላችሁ ብትጨርሱት አይሻልም ኖሯል? እንደ እኔ ዐይነቱ ተራ  ደጋፊ/ተከታይ እንዲሰማው ማድረግ ምን ያስፈልጋል? የመሪነት ብስለትስ ይህን አለማድረግ አይደለምን? ከሆነም ደግሞ “ተቃውሟችሁን በተናገረ አንደበታችሁ ለይተው የሚደግፏችሁን፡- “እርግጥ ነው በመኻከላችን ልዩነት አለ፣  ነገር ግን ለመፍታትም እየሠራን ነው። ደግሞም እንፈተዋለን” ብሎ ማረጋጋት ማንን ገደለ? ይህን ማድረግ የደካማነት ምልክት ይሆናልን?

    “አንተን እስከመፈጠርህም አናውቅህም፣ ለአንተ ማን ተናገረ” እንደምትሉ እርግጠኛ ነኝ።  የተናገራችሁት ነገር በፈቃዳችሁ በዩትዩብ ከተላለፈና ማስተባባያችሁ ካልተሰማ  ምን ማለታችሁ ሊሆን ይችላል? ያው ለሕዝብ መናገራችሁ አይደለም? እኔ ደግሞ ከሕዝብ መኻል እገኛለሁ። ተራው ደጋፊ/ተከታይ “የጋራ መሪን” ለመምረጥ ድምጽ እንዲሰጥ የሚፈለግ ሲሆን፤ ያኔ “ያንን መሪ”  ለመሆን የሚፈልግ ከሌላው የምሻል እኔ ነኝ ብሎ ቢቀሰቅስ መላ አለው። አሁን ግን  መሪን ስለመምረጥ የተራ ደጋፊ/ተከታይ ድምጽ በማይፈለግበት/በማይሰጥበት ሁኔታ በአደባባይ “እኔ እሻል ፤ እኔ” ማለቱ ጥቅሙ ምንድነው?

    የፖለቲካ ልምድ ያላቸውና ለዐማራው በመድከማቸው ከሚታወቁ  መኻል አንዳንዶቹ ከእኔ የተለየ ዐሳብ እንዳላቸው በዩ ትዩብ ተከታትዬአለሁ። ዐሳባቸውን  የሚገዙላቸውን ለማብዛትም በብዙ ሲተጉ አያለሁ።መቼም የእኔ ዐሳብ ከእነርሱ ይሻላል ማለት አጉል መንጠራራት ይሆንብኛል።

    ስሜቴን መግለጤ ግን ክፋት ስለሌለው እነሆኝ አሰማሁ። ደግሞም በተቃውሞ የተነሱት መሪዎች የሚሠሩት የማይወደድ ቢሆን እንኳ ፤ ይኸንኑን በሐቅና በሚገባ ማስረጃ አጣርቶ (በፈጠራ፣ በሸፍጥ ወይም በስሜት አይደለም) ጎጂ መሆኑን ማስረዳት እንጂ፣ የግለሰቦቹን ስብእና ማጉደፍና ሞታቸውን መመኘትስ  ለምን ይታሰባል? ይህ አካሄድ ልምድ ያካበቱትንና መታመንን ያተረፉትን መሬዎቼን ተራ በተራ የሚያሳጣኝ እንጂ መሪን አንጥሮ ለማውጣት የሚበጅ ነው ብዬ አላስብም። ድምዳሜው “ሁሉንም አጥቶ ባዶ እጅን አጨብጭቦ መቅረት” ይሆናል።ይህንን የማላስተውል አይደለሁም። ባዶ እጃችንን መቅረታችንን  የሚፈልጉ ደግሞ አይታጡም። ብቻ ከእኔ ይልቅ እሳቱ ላይ ያላችሁትን እናንተን የበለጠ ስለሚያማችሁና ስለሚያሳስባችሁ መላ ታበጁለታላችሁ ብዬ እተማመናለሁ። ጊዜያዊ መንገጫገጭ ስለሚመስለኝ እጽናናለሁ።

ተመልከት ዐላማህን ተክተል አለቃህን። ወይም “ተመልከት ዐላማህን ተከተል አለቆችህን”።

ቸር እንሰንብት!

Comments

Popular posts from this blog

Comparative Theology የነገረ መለኮት ንጽጽር (በኦርቶዶክስና በፕሮቴስታንት)/ በብፁዕ ወቅዱስ ፖፕ ሲኖዳ ሳልሳዊ

 የነገረ መለኮት ንጽጽር  (በኦርቶዶክስና በፕሮቴስታንት): የወደደ  ሁሉ በነጻ እንዲጠቀምበት ተፖስቷል። ይሁን እንጂ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ስለሆነ በየትኛውም መልኩ ለንግድ እንዲውል አልተፈቀድም። ልዩ ልዩ መግቢያ የሚለውን መጀመሪያ ካነበቡ በኋላ የተቀረውን በተመረጠው ቅደም ተከተል ማንበብ ይቻላል። ልዩ ልዩ መግቢያ   ጥምቀት   ትውፊት (ወግና ልማድ)   መካከለኝነት   ጾም የድንግል ማርያም ክብሯና ዘላለማዊ ድንግልናዋ መንፈሳዊ ስጦታዎችና በልሳኖች የመናገር ስጦታ   ሥርዐት ንስሐ

የድንግል ማርያም ክብሯና ዘላለማዊ ድንግልናዋ

የድንግል ማርያም ክብሯና ዘላለማዊ ድንግልናዋ (1)  ድንግል ማርያምን ስለማክበር (2) ለጥያቄዎች መልስ (ሀ) ድንግሊትን ‘የወይን ግንድ (ተክል)’ና የ ‘ሕይወት በር’ የሚል ማዕረግ  ለምን እንሰጣታለን? (ለ) ወደ ድንግል ማርያም መጸለይ ትክክል ነው ወይ? (3) የድንግል ማርያም ድንግልና ዘላለማዊነት (4) ለተቃራኒ አስተያየቶች መልስ (ሀ) “የመጀመሪያ ልጇን” የሚለው ሐረግ (ለ) “ሚስትህ” የሚለው ሐረግ (ሐ) “አብረው ከመሆናቸው በፊት ጸንሳ ተገኘች” (መ) “የመጀመሪያ ልጇን እስክትወልድ አላወቃትም” (ሠ)  “ወንድሞቹ” የሚለው ሐረግ   የቅድስት ድንግል ማርያም  ክብሯ (1) ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ድንግል እመቤታችንን አያከብሩም፤ ደግሞም እንድታማልድላቸውም (እንድትማልድላቸውም)  አይጠይቋትም።ከእነርሱ ወገኖች አንዳንዶቹ እንዲያውም ጫጩቱ ከተፈለፈለ በኋላ ዋጋ ከሌለው የዶሮ እንቁላል ቅርፊት ጋር እስከሚያመሳስሏት ይደርሳሉ።ይህ የተጋነነ ማቃለል የመጣው ምናልባት ሮሜዋውያን ካቶሊኮች የተጋነነ ማክበር ስለሚያከብሯት ለዛ ተቃርኖ ከማሳየት አዝማሚያ ሊሆን ይችላል። ስለዚህም ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን አንዱንም የእርሷን በዓል አያከብሩም።  (2) አንዳንዶቹ የፕሮቴስታንት ወገኖች ድንግል ማርያምን “እህታችን” ይሏታል። (3) በተጨማሪ አንዳንዶቹ ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ጌታ ኢየሱስን በድንግልና ከወለደች በኋላ ከዮሴፍ ጋር ጋብቻዋን ፈጽማለች፤ የ‘ኢየሱስ ወንድሞች’  ወይም የ’ጌታ ወንድሞች’ ተብለው የተጠሩ ልጆችን ወልዳለች ይላሉ።  (4) ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን ቤተክርስቲያናችን ለድንግል እመቤታችን የሰጠቻቸውን አንዳንድ የማዕረግ ስሞችም ይቃወማሉ።  (5) ድንግልን ያለማክበራቸው አንዱ...

ስለ "አስታዋሽ ጾምና በዐሉ" ጥያቄና መልስ

 ስለ "አስታዋሽ ጾምና በዐሉ" ጥያቄና መልስ  ለዐማራ ሕዝብና ዎገኖቹ፦ ሕልውናችንን-ነጻነትችንን የማረጋገጥና የማስቀጠል አንድነታችንን የመጠበቅና የማጠንከር  በእሴቶቻችን የመደሰት፣ እነርሱን የመንከባከብና የማስተዋወቅ  በረከታችንን የማብዛትና የማካፈል  ኃላፊነቶቻችንን በማኅበር ፣ በማስተዋልና በትጋት እንድንወጣ “ጾሙና በዐሉ" አስታዋሽ ባሕላዊ ምልክታችን ይሁንልን   ጥያቄ 1 ፡ አድማጭ ተመልካቾቻችን እንኳን ደህና መጣችሁ።የከበረ ሰላምታችን ይድረሳችሁ። ዛሬ የምንወያየው ከአቶ ባንቱ ገብረማርያም ጋር ይሆናል። አቶ ባንቱ በሙያው ፋርማሲት ነው። እንደነገረኝ በእምነቱ ደግሞ ባፕቲስት ነው።ለዐማራ ሕዝብና ዎገኖቹ ባሕላዊ ምልክት የሚሆን “ጾምና በዐልን” በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል። የምንወያየውም ስለዚሁ "ጾሙና በዐሉ" ምልክትነት ይሆናል።  አቶ ባንቱ ለመወያየት  ወደ እኛ በመምጣትህ አመሰግንሃለሁ። እንኳን ደህና መጣህ። አንተ እያልኩ ልቀጥል ወይስ አንቱ? መልስ 1፡ ዎገኔ፡   እንኳን ደህና ቆየኸኝ። ለአድማጭ ተመልካቾቻችሁም ሰላምታዬ ይድረስልኝ። አንተ በለኝ። የሚያውቀኝ ሁሉ አንተ ነው የሚለኝ።  ጥያቄ 2 ፡ እሺ  አንተ እያልኩ እቀጥላለሁ። አቶ ባንቱ፣ ምናልባትም ብዙ ሰው ስለማያውቅህ  እስቲ ስለራስህ በአጭሩ ንገረን። ወዲያውም መክፈቻ ይሆነናል መልስ 2 ዎገኔ ፦ አስቀድሜ ይኸን ዕድል ስለሰጠኸኝ ላመሰግንህ እወዳለሁ። አድማጭ ተመልካቾችህንም ጊዜ ወስደው  ውይይቱን  ስለሚከታተሉ ላመሰግናቸው እወዳለሁ።አዎን፣ ባንቱ ገብረማርያም እባላለሁ።እንደነገሩኝ የተወለድኩት ሽርካ በዛሬ አጠራሩ በአርሲ ዞን ነው።ነፍስ ያወቅሁትና ትምህርት ...