ትውፊት (ወግና ልማድ) 1. ትውፊት (ወግና ልማድ) ከመጽሐፍ ቅዱስም ይልቅ በእድሜ የቀደመ ነው 2. መጽሐፍ ቅዱስ ሁሉን ነገር አይጠቅስም 3. የእግዚአብሔርን መንግሥት አስመልክቶ ጌታ ያስተማራቸው ነገሮች ምን ነበሩ? 4. ትውፊት ከሐዋርያቱ ትምህርት የተወሰደ ነው 5. ሐዋርያቱ ሥርዓትን ለቤተ ክርስቲያን መሥርተዋል 6. ሐዋርያው ጳውሎስ ትምህርቶችን ከጌታ ተቀበለ 7. ሐዋርያቱ በትውፊት የተቀበሉትን በመልዕክቶቻቸው መዘገቡ 8. የትውፊት ጥቅሙ (አግለግሎቱ) 9. ተቀባይነት ያለውና የሌለው ትውፊት 10. ድንጋጌን በማውጣትና በማስተማር የቤተ ክርስቲያን ሥልጣን 11. ትውፊት ጤናማ የሚባልበት ሁኔታ 12. ሐዋርያቱ ትውፊት እንዲጠበቅ አዘዋል ትውፊት (ወግና ልማድ) ትውፊት ማለት ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ሌላ ከሐዋርያቱና ከአባቶች ለእኛ በአደራ የደረሰን ማናቸውም ትምህርት ማለት ነው። ይህ ትምህርት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተካተቱ ርዕሶችን ይይዛል፣ ነገር ግን በምንም መንገድ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያፋልስ አይደለም። ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን በትውፊት አ ያምኑም ። በመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ይጸናሉ። በዚህ መንገድ ቤተ ክርስቲያን ከቀደመው ትውልድ የተቀበለችውን ቅርስ ገሸሽ ያደርጋሉ።ሐዋርያትና የቤተ ክርስቲያን አባቶች የጻፉትን ፣ የቅዱሳን ጉባኤ ውሳኔዎችን፣ የቤተ ክርስቲያን ቀኖናዎችና ደምቦችን፣ የቤተ ክርስቲያን አምልኮ ሥርዓትንና የቃል ትውፊትን አያካትቱም። ትውፊት ከመጽሐፍ ቅዱስም ይልቅ እድሜው የበለጠ ነው። ወደ አባታችን ወደ አዳም ዘመን ይዘልቃል። ለእኛ የደረሰን ከሁሉ የቀደመው የጽሑፍ ሕግ የተጻፈው በነቢዩ ሙሴ ነበር። ሙሴ የኖረበት ዘመን ደግሞ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ14ኛውና በ15ኛው ም...