የተሸፋፈነው እውነት ይገላለጥ አስቴር በዳኔ በ“ሀሌታ” ቃለመልልሷ ውስጥ ሶስት ዋና መልዕክቶችን ታቀርባለች። መጀመሪያ፣ “አሁን ትልልቅ ጦርነቶችን ያስነሳው ነገር…” በማለት የጦርነቱን እውነተኛ መነሻ ትደብቃለች። ሁለተኛ፣ “የሆነ ብሔረሰብና የሆነ ሃይማኖት የአገር ባለቤት ነኝ ብሎ ተቀምጧል” በማለት ተጠቂውን እንደ አጥቂ ታቀርባለች፣ እውነቱን ታዛባለች። ሶስተኛ፣ “ቶለሬት የማያደርግ ትውልድ…” በማለት ስለተጠቂዎቹ መከራ ኀላፊነቱን በሃሳቧ ለፈጠረችው ማኅበረሰብ ትሰጣለች፤ መንግሥትን ግን ነጸ ታደርገዋለች። እነዚህ መልዕክቶች በአንድ አቅጣጫ ያዘምማሉ፤ የጦርነቱን መነሻ፣ የተጎጂዎችን መከራ፣ የመንግሥትን ኃላፊነት — ይሸፋፍናሉ። የተዘጋጀው መጋረጃ አስቴር የተናገረችው እውነት አይደለም። በአማራዎች ላይ የተጀመረውን ጦርነት ለመሸፋፈን የተቀመጠ መጋረጃ ነው። እውነቱን አላቀረበችም፤ ቀበረችው እንጂ። ስለ ተጠቂዎቹ ጉዳት አልተነፈሰችም። የተጎጂዎቹንና የጎጂዎቹን ሥፍራ አቀያይራለች። ተጠያቂዎቹን አላጋለጠችም፤ ሸፋፈነቻቸው። ጦርነቱን ያወጀው መንግሥት ነው። መልዕክቷ ያን እውነት ተደብስብሶ እንዲያልፍ የታለመ ነው። ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖችን ባለመጠበቁ መንግሥትን እንዳይጠየቅም የሚሰውር ነው። እውነቱን በመደበቅ ብቻ አላቆመችም፤ ቅሬታን የሚያባብስ፣ የመበቃቀል አዙሪትን የሚጭር ሃሳብ ተክላለች። ይህንን የተሸፋፈነውን መልዕክቷን ገላልጦ ማየት —አደገኛነቱንም መመልከት ያስፈልጋል። አዎ — የተሸፋፈነው ይገላለጥ! እርሷም ስህተቷን ታርም — መንግሥትን ተጠያቂ ታድርግ! ---------------------------------------- የጸሀፊ ማስታወሻ በእህቴ አስቴር ላይ የግል ጥላቻ የለኝም። ይህ ጽሁፍ የሚመለከተው የእርሷን ፖለቲካዊ...