የተሸፋፈነው እውነት ይገላለጥ
አስቴር በዳኔ በ“ሀሌታ” ቃለመልልሷ ውስጥ ሶስት ዋና መልዕክቶችን ታቀርባለች።
መጀመሪያ፣ “አሁን ትልልቅ ጦርነቶችን ያስነሳው ነገር…” በማለት የጦርነቱን እውነተኛ መነሻ ትደብቃለች።
ሁለተኛ፣ “የሆነ ብሔረሰብና የሆነ ሃይማኖት የአገር ባለቤት ነኝ ብሎ ተቀምጧል” በማለት ተጠቂውን እንደ አጥቂ ታቀርባለች፣ እውነቱን ታዛባለች።
ሶስተኛ፣ “ቶለሬት የማያደርግ ትውልድ…” በማለት ስለተጠቂዎቹ መከራ ኀላፊነቱን በሃሳቧ ለፈጠረችው ማኅበረሰብ ትሰጣለች፤ መንግሥትን ግን ነጸ ታደርገዋለች።
እነዚህ መልዕክቶች በአንድ አቅጣጫ ያዘምማሉ፤ የጦርነቱን መነሻ፣ የተጎጂዎችን መከራ፣ የመንግሥትን ኃላፊነት — ይሸፋፍናሉ።
የተዘጋጀው መጋረጃ
አስቴር የተናገረችው እውነት አይደለም። በአማራዎች ላይ የተጀመረውን ጦርነት ለመሸፋፈን የተቀመጠ መጋረጃ ነው።
እውነቱን አላቀረበችም፤ ቀበረችው እንጂ። ስለ ተጠቂዎቹ ጉዳት አልተነፈሰችም። የተጎጂዎቹንና የጎጂዎቹን ሥፍራ አቀያይራለች። ተጠያቂዎቹን አላጋለጠችም፤ ሸፋፈነቻቸው።
ጦርነቱን ያወጀው መንግሥት ነው። መልዕክቷ ያን እውነት ተደብስብሶ እንዲያልፍ የታለመ ነው። ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖችን ባለመጠበቁ መንግሥትን እንዳይጠየቅም የሚሰውር ነው።
እውነቱን በመደበቅ ብቻ አላቆመችም፤ ቅሬታን የሚያባብስ፣ የመበቃቀል አዙሪትን የሚጭር ሃሳብ ተክላለች።
ይህንን የተሸፋፈነውን መልዕክቷን ገላልጦ ማየት —አደገኛነቱንም መመልከት ያስፈልጋል። አዎ — የተሸፋፈነው ይገላለጥ!
እርሷም ስህተቷን ታርም — መንግሥትን ተጠያቂ ታድርግ!
----------------------------------------
የጸሀፊ ማስታወሻ
በእህቴ አስቴር ላይ የግል ጥላቻ የለኝም። ይህ ጽሁፍ የሚመለከተው የእርሷን ፖለቲካዊ ምልከታዋንና የንግግር ምርጫዋን ነው፤ የግል ስብዕናዋን አይነካም።
See Through the Smoke
Aster’s words are not truth — they are a shield placed to cover the government that launched the war on Amharas. She did not present the truth; she buried it. She did not acknowledge the victims; she inverted them. She did not expose power; she concealed it.
The government is the one that declared the war. Her message is crafted to hide that fact behind a cloud of misdirection. It also shields the government from accountability for failing to protect Orthodox Christians.
She didn’t just mask the truth — she introduced a rhetoric that fuels grievance and a cycle of revenge. She didn’t present the political reality; she blurred the cause in a way that feeds the very cycle her framing ignites.
See through the smoke.
May she correct her error — and hold the government accountable.
----------------------------------------
Author’s Note
I hold no personal animosity toward sister Aster. My critique addresses the political framing and rhetorical choices in her message, not her dignity as an individual.
- Get link
- X
- Other Apps
- Get link
- X
- Other Apps

Comments
Post a Comment