ከቴዲ አፍሮ ዘፈን ሳንወጣ!
በ “ዳስ ጣል” ዘፈኑ በአዎንታ ተደምሜአለሁ! በጥያቄዎችም ተሞልቼአለሁ።
·
ይህ ሁሉ
ሕዝብ ለምን አደመጠው?
§ ያደመጠውስ ቴዲን ነው?
§ ሙዚቃውን ነው?
§ መልዕክቱን ነው?
§ የራሱን ወይም የጎረቤቱን ህመም ነው?
§ ዘፈኑን የወደደውስ ሕዝብ ፣ቴዲ ያዘነበትን ነገር ለመለወጥ ምን ያደርግ ይሆን?
·
የተቃወሙትስ የተቃወሙት
ምኑን ነው?
§ ምን መልዕክት ደርሷቸው ነው የተቃወሙት?
§ ወይም ምን ሥጋት ገበቷቸው ነው?
§ ሥጋት ከሆነባቸውስ ከዚያ የሚወጡበት ገምቢ መንገድ የላቸውም?
ቴዲ ይኸንኑ ዘፈን በግፍ ለተገደሉና ለተፈናቀሉ መታሰቢያነት አበርክቶታልንም ሰማሁ። ይህን ስሰማ ለእነዚህ ቋሚ መታሰቢያ ሳፈላልግ የነበረውን ፍለጋዬን ተውኩት።
ባንቱ ገብረማርያም
ክ“አዎን ድምጽ”
Comments
Post a Comment