Skip to main content

Posts

ለፓስተር ግርማ ቤካ

ለፓስተር ግርማ ቤካ ይህ የመጀመሪያው ጽሑፌ በዩ ትዩብ ለማቅረብ እንዲስማማ የተደረገ ነው። አድማጭ ተመልካቾቼ እንደምን ሰነበታችሁ? እኔ ቸርነቱ የበዛ አምላክ ይመስገንና ደህና ነኝ። የዛሬ ዝግጅቴ አንድ ፓስተር ወንድሜ ለተናገረው ምላሸ የሚሰጥ ነው።      የአርሲ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች የደረሰባቸውን ግፍ ከኦርቶዶክሳውያኑ ጎን በመሆን ያወገዙ የወንጌል አማኞች ነበሩ። ይኸንን የወንጌል አማኞች ድርጊት “አታሽቃብጡ” በማለት ይኸው ወንድማችን ተቃውሞታል።የተቃወባቸውን ስምንት ምክንያቶች ነጥብ በነጥብ እያነሳሁ የራሴን አጭር ምላሽ የምሰጥባቸው ይሆናል። ከአጭር ምላሹ በኋላም ማብራሪያን አስከትላለሁ። በመጨረሻም ሐሳቤን አጠቃልላለሁ።በስፋት ከተደመጠ ቀና ውይይት ይከፍታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።      በዚህ አጋጣሚ ቤተሰብ የተገደለባቸውን እግዚአብሔር አምላክ ያጽናናችሁ ለማለት እወዳለሁ። ያፈሩትን ሐብትና ንብረት በትነው፣ ለዘመናት ከኖሩበት ቀዬ እንዲሰደዱ ለተገደዱት ወገኖችም ስቃያችሁን እግዚአብሔር “ሕይወትን ለማዳን” ያድርግላችሁ እላቸዋለሁ። አሁን ወደ ምላሹ፡      የተወደድክ ፓስተር ወንድሜ: ለጤናህ እንደምን አለህ? እኔ ቸርነቱ የማያልቅበት እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን ደህና ነኝ።      በአርሲ ግፍ ለተቀበሉት ኦርቶዶክሳውያን ድምጽ ላሰሙቱ የወንጌል አማኞች “አታሽቃብጡ" በሚል ሐሳብ ዙሪያ የተናገርከውን በአንክሮ አዳምጬ ከጨረስኩ በኋላ ግልጽነትህንና ስሜትህን ለመግለጥ መድፈርህን አድንቄአለሁ።ይኸው ድፍረትህ እኔንም እንድናገር አነቃቅቶኛል። ወንጌላዊ አማኝ ብሆንም በአርሲ ኦርቶዶክሳውያን የደረሰውን ግፍ ካወገዙት ጋር ...

እግዚአብሔር የጠላቶቼ ጠላት አይደለም!

 እግዚአብሔር የጠላቶቼ ጠላት አይደለም! በባንቱ ገብረማርያም አድማጭ ተመልካቾቼ ፡ እንደምን ሰነበታችሁ? እኔ እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ። እንደገና ብቅ ብያለሁ። ዛሬ የምናገረው መምህር  በጋሻው ሰሞኑን የተናገሩት መነሻ ሆኖኝ ነው። ርዕሱም "እግዚአብሔር የጠላቶቼ ጠካት አይደለም" የሚል ይሆናል። እንደ ተለመደው በጽሞና እንድትከታተሉኝ ላስቸግራችሁ እወዳለሁ። አሁን ወደ አስተያየቴ፦ ከዚህ ቀደም በኦርቶዶክሳውያን ስለሚደርሰው መከራ የደረስኩበትን ግንዛቤ “መከራው እስካለ” በሚል ርዕስ ጽፌ ነበር። ማንበብ ለሚፈልግ ሊንኩ ይኸው።  You searched for መከራው እስካለ - Hintset  ። መምህር  በጋሻው ሰሞኑን በተናገሩት መነሻ የጻፍሁት ይኸኛው  ጽሑፍ ከዚያ የተከተለ አድርጎ መውሰድ ይቻላል። “እግዚአብሔር የጠላቶቼ ጠላት አይደለም” የሚለው ሐረግ የተነገረው በማርቲን ኒሞለር (Martin Niemöller") የሉተራዊ ነገረ መለኮት አዋቂ በነበረው ጀርመናዊ ነበር። ማርቲን መጀመሪያ የሂትለር ደጋፊ ቢሆንም በኋላ ላይ  አጥብቀው ከሚቃወሙት አንዱ ሆኗል። “የእግዚአብሔር ፍቅርና ምህረት በወገን/ በቡድን የሚታጠር አይደለም። ጠላት ለሚባሉትም እንኳ የተዘረጋ ነው ። የእዚአብሔር ፍቅር የግል ቂም በቀልን ትክክለኛነት ለማጽደቅ ወይም የበቀል መሣሪያ ሆኖ  ሊያገለግል አይገባውም” ብሎ የሚሞግት ሰው ነበር። ናይጄራዊቷ  ጸሐፊና ተናጋሪ ቺማማንዳ ንጎዚ አዲሼ (Chimamanda Ngozi Adichie) ይኸንን አተያየት በሕይወት ጉዞዋ ደርሳበታለች። ነገር ግን ጊዜ እንደወሰደባት በተለያዩ አጋጣሚዎች ስትናገር ተደምጣለች። የካቶሊክ አማኝ የሆነችዋ ይኽች ሰው አንድ ጊዜ ራሷንና የእርሷ የሆኑትን የ...

ፓስተር ታምራት ኃይሌ፡ አመሰግናለሁ!

  እድማጭ ተመልካቾቼ እንደምን አላችሁ ? ቸርነቱ የማያልቅበት አምላክ ይመስገንና እኔ ደህና ነኝ።ዛሬ ፓስተር ታምራት ኃይሌ በቅርቡ ባሰማው “ ልመና ” ላይ ያለኝን አስተያየት አጋራለሁ። እንድትከታተሉልኝ በታላቅ ትህትና እጋብዛችኋለሁ። ባንቱ ገብረማርያም ነኝ ርእሱ ፡ ፓስተር ታምራት ኃይሌ ፡  አመሰግናለሁ ! (ከታምራት ላይኔ ጋር አይምታታ)   መነሻዬ ሰሞኑን ፓስተር በዩትዩብ ያቀረበው መልዕክት ነው። ማዳመጥ ለሚፈልግ ሊንኩን እያይዤዋለሁ። ፓስተር ታምራት ለመንግሥት፣ መንግሥትን ለሚዋጉና   እንዲሁም በዲያስፖራ ላለነው በወግ በወጉ አደራጅቶ ልመና አቅርቧል። መጀመሪያ ልመናውን በራሴ አገላለጽ በአጭሩ አኖረውና ከዚያ ወደ አስተያየቴ እገባለሁ፡፡   ልመና ፩፡   ለመንግሥት የቀረበ ብዙ ልጆች የወለደ አባት የሁሉን ልጆች ፍላጎት አስማምቶ ማርካት እንደሚቸግረው ሁሉ የሕዝቦች አባትና ጠበቃ የሆነው መንግሥትም የሁሉንም ሕዝቦች ፍላጎት መሙላት ሊያስቸግረው ይችላል። ዋናዎቹን በተመለከተ ግን ከእግዚአብሔርም ከሕዝብም የተሰጠው አደራ ስለሆነ ገሸሽ ሊያደርጋቸው አይገባም ይላል ፖስተር   ታምራት ኃይሌ  ሲጀምር። በመቀጠልም ዋናዎቹን እደራ ይዘረዝራል፦ አገርን ማልማትና የዜጎችን ሕይወት መቀየር   ዜጎች በአገራቸው በሰላም ሠርተው፣ ሐብት አፍርተውና ተጋብተው፣ ተዋልደው እንዲኖሩ የሰላምና የደኅንነት ዋስትና ማረጋገጥ   የአገርን ዳር ድንበር ከማናቸውም ወራሪ መጠበቅና አገርን...

Venerating Blessed Mary: ብፅዕት ማርያምን የማክበር ጉዳይ ማወኩ!

  ብፅዕት ማርያምን  የማክበር ጉዳይ ማወኩ? በባንቱ ገብረማርያም አድማጭ ተመልካቾቼ፡ እንደምን አላችሁ ? ክብሩ ይስፋ የመድኃኒዓለም ! እኔ ደህና ነኝ ሰሞኑን የማርያም ሥዕል መቀደዱን ከማህበራዊ መገናኛ ተመለከትኩ። ስለዚያ ያለኝን አስተየየት እንደሚከተለው አቀርባለሁ። እንድትከታተሉት በታላቅ ትህትና እጋብዛችኋለሁ።        በመጀመሪያ ስለ ማርያም ሥዕል ያለኝን ትውስታ ልንገራችሁ። በጎባ / ባሌ የአዝማች ደግልሃን ት / ቤት   ተማሪ ነበርኩ ( ስሙ ተቀይሯል ) ። ይህ ታሪክ የሆነ ጊዜ የስንተኛ ክፍል ተማሪ እንደነበርኩ አሁን ተዘንግቶኛል። የዘጠነኛ   ወይም የአሥረኛ   ክፍል   ተማሪየነበርኩ ይመስለኛል። በዚያን ዐመት በትምህርት ቤቱ የተማሪ ክበቦች ተቋቁመው ነበር።ታዲያ እኔም ከተቋቋሙት አንዱ ከነበረው ከመጽሐፍ ቅዱስ ክበብ   ገባሁኝ። የክበቡ መሪ ከቀዳማዊ ኃይለሥላሤ ዩኒቨርስቲ ( ስሙ ተቀይሯል ) በብሔራዊ አገልግሎት የመጣ የኬሚስትሪ   አስተማሪ ነበር። አንዱን ቀን መጽሐፍ ቅዱስን ሊያስተምረን አባላቱን   ሚካኤል ጋራ ላይ ይዞን ወጣ ( አካባቢውን ለማታውቁት ሚካኤል ጋራ ከትምህርት ቤቱ ጀርባ የተቆለለ ጋራ ነው ) ። እዚያ ስብሰባ ላይ ነበር የማርያምን ሥዕል   ያደለን።የሥዕሉ   ትልቅነቱ   የኪስ ቦርሳ ውስጥ ለማስገባት የሚያስቸግር ያህል ነበር።እጅግም ትልቅ አልነበረም ለማለት ነው። ት / ቤት   ለዕረፍት በተዘጋበት ጊዜ   ...