Skip to main content

Posts

ፋኖ ፡ በኢትዮጵያ የሃያ አንደኛው ምዕተ ዐመት ልዩ ክስተት

  ፋኖ ፡ በኢትዮጵያ የሃያ አንደኛው ምዕተ ዐመት ልዩ ክስተት  የኢትዮጵያን ሁኔታ ከዜና አቅራቢዎች  እንደሚከታተል ሰው በዚችው ጥቂት ዕድሜዬ በርካታ ፓለቲከኞች ተነስተው አይቼአለሁ። አስተዋጽኦዋቸውን በጓዳዬ ያደነቅኋቸው ብዙ ናቸው። ከእነዚህ መኻል ባስቀመጥኳቸው ሥፍራ ያላገኘኋቸው  አሉ።ድርጅቶቻቸውም  እንደዚያው የሆኑባቸው። ያዘንኩላቸውም ያዘንኩባቸው ይኖራሉ። ችግራቸውንና  ፈተናቸውን እነርሱ ያውቃሉ። እኔ በሩቅ ሆኜ የምከታተል ስለሆንኩ እሳቱ ምን ያህል እንደፈጃቸው ልረዳላቸው አልታደልኩም።  አሁን ላይ ከእነዚህ መኻል  የዐማራ ሕዝብና ዎገኖቹን ለማዳን ኃላፊነቱን በሚገባ እየተወጣ ያለውን ፋኖ፣ ለመለወጥ ወይም ለማደናቀፍ ወይም ጠልፎ ለመጣል የሚሠሩትን  ግን  ተቀይሜአቸዋለሁ። የዐማራ ስቃይን ለዘለቄታው  ማስወገድ እስከቻለ ድረስ ማንስ ፋኖን ቢመራው ምን ቸግሯቸዋል?  ቀጥታ በተጋድሎው ሥፍራ  ላይ ያሉት የፋኖ መሪዎች ያጎደሉት ምን ኖሮ ነው? እንደ እኔ ዐሳብ ይህን ትተው በመተባበሩ ላይ ቢያተኩሩ ለሁላችንም ድንቅ ይሆናል እላለሁ። ደግሞ ይኸንን ያጡታል ብዬ አላስብም። መተባበሩን ይመርጣሉም ብዬ አምናለሁ። ለማንኛውም በስፋት ሲዘገብ እንዳገኘሁት ፋኖዎች  ሞትን ሳይፈሩ፥ ደፍረው ፥ በነፍሳቸው ቆርጠው ጉልበታቸውን በደሊላዎች ሳያደክሙ  ገንዘብንም ሎሌያቸው እንጂ ገዥያቸው ሳያደርጉ  በቅርብም በሩቅም ባሉ ወንድሞቻቸው የሸፍጥና  የኅይል ሥራ ሳይርዱ የዐማራ ሕዝብና ዎገኖቹ እንዳይጐዳ እየተጠነቀቁለትና እርሱም እየደገፋቸው አብዛኞቹ መሪዎቹ ለዐማራ ሕዝብ በረከት ሲሉ  የግል ኢጎአቸውን በመዋጥ  ወደ መተ...

ካውንስሉ ካስገደደው የሚስተካከል የጸሎት ጥያቄ ባይሆንም፦

  ካውንስሉ ካስገደደው የሚስተካከል የጸሎት ጥያቄ ባይሆንም፦ እነዚያ ሁሉ አባቶች ፣ የቤተክርስቲያን መሬዎችና፣ አዋቂዎች መክረው (ግራና ቀኙን አይተው) በካውንስሉ በኩል ካቀረቡት አስገዳጅ የጸሎት ጥያቄ የተሻለ አቅርቤአለሁ አልልም። ይሁን እንጂ የአደባባዩ ቢቀር የተሰማችሁ በየግላችሁ ብትጸልዩበት ይሆናል።በተባለው የሰላም መልዕክትና ጸሎት ጊዜም ልታስቡት ትችላላችሁ። “በአዲስ አበባ ያላችሁ ወንጌላውያን ተረጋጉ” በሚለው ጽሑፌ ያቀረብኩት የጸሎት ጥያቄ ነበር። ፋኖዎች የሃይማኖት እኩልነትን  የማክበር አቋማቸውን በተግባር ማሳየት እንዲችሉ እግዚአብሔር  አምላክ እንዲረዳቸው ለፋኖ  መነሳት ምክንያት የሆነው የዐማራ ሕዝብና ዎገኖቹ መጨፍጨፍና መፈናቀል ስለሆነ እግዚአብሔር ዐማራውንና ዎገኖቹን  እንዲታደግ ፥ ሊከፋፍሉትና ሊያጠፋት ሌት ተቀን የሚያደቡትን ምክራቸውን እንዲያፈርስ ፥ ኅይላቸውንም እንዲበትን ከኦርቶዶክሳውያን ጋር በበጎ ዐይን ለመተያየት እንዲያበቃንና ወንጌልን በመተባበር ወደ መዝራቱ በተለይ ዕዳሪ መሬት ወደ ማውጣቱ  ልቦቻችንን እንዲያዘነብል የብልጽግና የበላይነት ለረዠም ጊዜ ከቀጠለ ኢትዮጵያ ወደ አረማዊ አገርነት የመገስገስ  አደጋ ስለሚገጥማት ከዚያ እንዲታደጋት። እኛም ከኦርቶዶክሳውያኑ ጋር ሆነን ኢትዮጵያን ከዚያ  ለማትረፍ  በመሥራቱ እንዲያተጋን  እንጸልይ

ልቡን ለሕዝብ የሚያዘነብል መሪ ፍለጋ

  ልቡን  ለሕዝብ የሚያዘነብል መሪ ፍለጋ ለዚህ ሐተታዬ መነሻ የሆኑኝ የብጹእ አቡነ ኤርምያስ፣ የብጹእ አቡነ ሉቃስ እና የብጹእ  አቡነ አብርሃም  ንግግሮች ናቸው። እንደ ራሴ ግንዛቤ ከንግግሮቹ  ባገኘኋቸው ሦስት የዐማራ ሕዝብና ዎገኖቹ እይታዎች (እሴቶች) ላይ አትታለሁ።  መጀመሪያ ስለ ብጹኣን ጳጳሳቱ የተሰማኝን ልጻፍ፦ ሦስቱም ብጹአን አባቶች በንግግራቸው የብሔር ማንነታቸውን ሲገልጡ አልሰማሁም። ምናልባት መነኩሴ ማለት ለዚህ ዐለም ነገር የሞተ ማለት ሆኖባቸው ምድራዊውን የነገድ ነገር ስለማያስቡት ሊሆን ይችላል። ወይም ራሳቸውን ለኦርቶዶክሳውያንና እድል ፈንታው ከኦርቶዶክሳውያኑ ጋር ለሚወሰን ሕዝብ ሁሉ አባት አድርገው ስለሚያዩ ሊሆን ይችላል (የዐሳባቸውን መድረሻ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ማድረጋቸው  ለዚህኛው ምክንያት ክብደት ይሰጣል)። ሦስቱም ብጹአን አባቶች ለኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንና  ምዕመናኑ የሚገዳቸው ናቸው። በአቡነ ኤርምያስ በኩል የላሊበላ አብያተክርስቲያናት ጉዳት እንዳይደርስባቸው ብልሃት ያሉትን መምከራቸውና በሰበካቸው ስለሚገኘው ምእመናቸው  ችግር መጨነቃቸው ማሳያ ነው። አቡነ ሉቃስ ደግሞ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት ስለመቃጠላቸው፣ ገደማውያንና መነኮሳቱ ስለመገደላቸውና ፣ በአጠቃላይ ስለ ኦርቶዶክሳውያኑ መጨፍጨፉ ያሰሙት የቁጭት ቃል ይመሰክራል። አቡነ አብርሃም ከሕግ ውጭ የታሠሩ ኦርቶዶክሳውያን እንዲፈቱ ፣በሕግ አግባብ የታሠሩ ካሉም ፍትሕን  እንዲያገኙ መጠየቃቸው (ይፋ ባልሆነ መንገድ) ይኽንኑ ያሳያል።  በቀኖናዋ መሠረት እንጂ በሌላ ወገን ተጽዕኖ  ቤተክርስቲያን እንደማትሠራ ማረጋገጫ መስጠታቸውም ለቤተክርስቲያን የመቆማቸው የመጨረሻው መገለጪያ ነው።...

ፋኖ ያሸንፍ

ፋኖ ያሸንፍ! ባለፈው ጊዜ “ፋኖ እንዲያሸንፍ ለምን እንደምመኝ /እንደምፈልግ ጊዜ ካገኘሁ እጽፍበታለሁ ፤ እስከዚያው ግን ምኞቴ እንዲደርስ መርቁኝ “ ብዬአችሁ ነበር።  በአጭሩ፦ፋኖ እንዲያሸንፍ መመኘቴ “አንቺም ትሞቺብኝ ይሆን ወይ? (እንደ ተረቱ)” በሚባል አስተዳደር ላይ የተጠረቀመውን መዝጊያ ወለል  አድርጎ ይከፍታል” በሚል እሳቤ ነው። ("አንቺም ትሞችብኝ ይሆን ወይ" ማለት እንዲወድቅ የማይፈለግ ቅን መንግሥት ለማለት ነው። ተረቱን ለማወቅ የሚፈልግ በአስተያየት መስጪያ ላይ ይጠይቅ) እንደሚታወቀው የዐማራ ሕዝብና ዎገኖቹ ከበዳዮቹና ከአስጨናቂዎቹ ይታደጉት ዘንድ በቅርቦቹ አሥርት ዐመታት በኢትዮጵያ ለተነሱት መንግሥታት አቤቱታውን ሲያሰማቸው ኖሯል። ሰላማዊ በተባለ መንገድ ጥያቄውን አቅርቦላቸዋል። ይሁን እንጂ ሊከላከልለት የፈቀደ የመንግሥት አካል ብቅ አላለም። በችግሩ አላዘኑለትም። ያም ቀርቶ መሳለቂያ ባላደረጉት  ምንኛ መልካም በሆነ ነበር።  እንዳውም አሁን በመጨረሻ  በብዙ ሥጋት ውስጥ እያለ መንግሥት ራሱ “ወርሰህ ታጠቅ” ያለውን ጠመንጃ አስረክብ ብሎ ተነሳበት። ሌሎቹ ሳይነኩ ልዩ ኅይሉንም አፈረሰበት።ጦርም አዘመተበት።የዐማራ ሕዝብ ምን ምርጫ ነበረው? ምን ቀረው? የመከላከል ጦርነት ውስጥ ገባ። ለተጋድሎው ፋኖ ዐይነተኛ መሪው ሆኖ ብቅ አለ።እግዚአብሔር የዐማራን ሕዝብና ዎገኖቹን  ሊያስበው መጀመሩ ነው መሰለኝ ሁኔታዎች ተገጣጠሙና ፋኖ የዐማራን ሕዝብና ዎገኖቹን የሚወጉትን ኃይላት የሚገዳደር ኅይል ሆኖ ወጣ።ታዲያ በዚህ እራስን  የማዳን ጦርነቱ ነው ፋኖ እንዲያሸንፍ የፈለግሁት/የተመኘሁት።የአብርሃም አምላክና አምላክህ ይርዳህ ! ድሉን ይስጥህ ብዬዋለሁ።  ተሳስቼ ሊሆን ይችላል። ስ...

"የሚቀጠቅጥ በእኛ ላይ ወጥቶአል"

"የሚቀጠቅጥ በእኛ ላይ ወጥቶአል" የቀን እንቅልፍ ለምዶብኛል።እንደ ወትሮዬ ምሣዬን ከበላሁ በኋላ ድንክ አልጋዬ ላይ ጋደም አልኩ። ወዲያው እንቅልፍ አሸለበኝ።እንደ ሌላው ጊዜ አጭርና ጣፋጭ ሆኖ አልተሰማኝም። ህልም አይሉት፣ ቅዠት- ብቻ ቆየሁበት። አንድ ሰው ጎራዴውን ታጥቆ በግራጫ ፈረስ ላይ ጉብ ብሏል። ጀርባውን ለእኔ ሰጥቶ ስለነበር ፊቱ አልታየኝም።ማን እንደሆነ አልለየሁትም። ለምን እንደሆነ አላውቅም፤ ገና ሳየው “ፈረሱስ፣ ጎራዴውስ የራሱ ይሆን?” ብዬ ጠየቅሁ። ትንሽ ጊዜ ትክ ብዬ እንዳየሁት፦ «በዕቅዳችን መሠረት ኢምፓየራችንን ለመመሥረት እንፍጠን። ብዙ ሕዝብ ሊያልቅ ይችላል፣ ምንም ማድረግ አንችልም። ለመመሥረቱ ግን መፍጠን አለብን» ሲል ሰማሁት። ቀጥሎም፦ «ኢምፓየሮቻችንን ለመገንባት እንቅፋቶችን የምናስወግድበት ዘዴ አግኝቼአለሁ!»አለ ጮክ ባለ ድምጽ። እኔም:-«መጀመሪያ ኢምፓየር ሲል የሰማሁት መስሎኝ ነበር። አሁን ደግሞ ኢምፓየሮች ይላል።ምን ማለቱ ነው? አልዘባረቀም? ለመሆኑ የሚናገረው ለማንነው?» አልኩ። ወደ ቀኝ፣ ከቀኝ ወደ ግራ፣ ከዚያ ወደፊት አማትሬ ተመለከትሁ።ጥቋቁር ፈረሶቻቸውን ሽምጥ ለመጋለብ አቆብቁበው ያሉ ሦስት ሰዎችን ከፊት ለፊቱ አየሁ።ለካንስ የሚናገረው በተጠንቀቅ ለሚጠብቁት ለእነዚያ ሰዎች ኖሯል። አለቃቸው መሆኑ ይሆን? ለመጀመሪያው ሰው ተናገረ፦ «ወደ ጥንታዊቷ ኢትዮጵያ ውጣ ! ነገዶቿንና ጎሳዎቿን ሁሉ በጎጥ ፣ በቀበሌ ከፋፍላቸው፣ ክተፋቸው።እርስ በእርሳቸው እንዳይዳረሱ አድርጋቸው። ለመሰልቀጥና እንደፈለግን ለመጥረብ የሚመቸን እንደዚያ ሲሆኑ ነው። የሚቋቋሙበት አቅም ያጣሉ። ዳግመኛ የሚሰባሰቡበት 'ቡረሌ' እንዳያገኙም ነቅንቃቸው ። ፍጠንና ይኸንኑ አድርግ»ሲል ሰማሁት።የመጀመሪያው ሰውዬም ይኸንኑ ለማ...

አማትና ሥነ-ሥርዐት

  አማትና ሥነ-ሥርዐት   (ከMAY 2014 / REALSIMPLE.COM pp178-184) (በጽሑፉ  የተመለከቱትን ጠበብት ማንነት ለማወቅ ለሚፈልግ በመጨረሻ ማስታወሻ ተሰጥቷል)     በሚስቱና በእናቱ መኻል የሚኖረው ግንኙነት ብዙ ጊዜ ውጥረት የተሞላበት የሚሆነው ለምድነው? ስለዚህ የተወሳሰበ ግንኙነት አዲስ እይታና፣ ግንኙነቱን ለማሻሻል የሚረዳ ብልሃት አለ ወይ? የ”ሪይል ሲምፕል” መጽሔት አጠናቅሮ መልስ ይሰጣል።     የሥነ ልቦና ባለሙያዋ  ቴሪ አፕተር (2009)  በአንድ ጥናታቸው ካካተቷቸው ሴቶች ከመቶዎቹ መኻል ስልሳዎቹ ምራት አማትን፣ አማትም ምራትን ‘ክፉ ነች’፣ ‘ቆሽቴን ታሳርረዋለች’ ፣ ‘አትመቸኝም’ በማለት የግንኙታቸውን ጎርባጣነት ገልጠዋል።     ‘ሪል ሲምፕል’ መጽሔት አሰሳዊ ጥናትም ያሳየው ተመሳሳይ ነገር ነው። ስማቸውን ባልገለጡ 3700 ምራቶች እና 900 አማቶች ለ‘ሪይል ሲምፕል’ መጽሔት አዘጋጆች አማትና ምራት አንዳቸው ስለሌላቸው የሚሰማቸውን ገልጠው ነበር። የአሰሳ ጥናቱ በስድስት ጉዳዪች ዙሪያ ሲያጠነጥን ውጤቱ እንደሚከተለው ነበር። አርባ ስምንት ከመቶ ምራቶች ጥርሳቸውን ለማስነቀል የጥርስ ሐኪማቸውን መጎብኘት ከሚፈሩት ይልቅ አማታቸውን መጎብኘት እንደሚፈሩ ተናግረዋል። ምራት የምትበጠበጥበት ትልቅ ነገር አማቴ በጎ ዐሳቢ መስላ ትጎዳኛለች ማለቷ ነው።ሰላማዊና ደህና የሚመስለው የአማቷ ንግግር/ሥራ ያስቀይማታል። አማት የምትበጠበጥበት ትልቁ ችግር ምራት ከባሏ ወላጆች ይልቅ ከራሷ ወላጆች ጋር የበለጠ ጊዜ ታሳልፋለች እና ለእነርሱ ታዳላለች፣ እኔን ታገለኛለች ብላ ማሰቧ ነው። አፐርም ባደረጉት ጥናት ሁለት ሦስተኛ አማቶች ምራቴ ታ...

ነገረ አማት ወምራት

ነገረ አማት ወምራት ትርጉም፦ የባል እናትና አባት ለሚስት ዐማቶች ናቸው። አንዱን ከሌላው ለመለየት የወንድ አማቷ ወይም የሴት አማቷ ይባላሉ። የሚስት አባትና እናትም ለባል ዐማቶቹ ይባላሉ። የወንድ አማቱ ወይም የሴት አማቱ ተብለው ይለያሉ። በዚህ ጽሑፍ አማት ሲባል የባል እናትን ፥ ምራት ሲባል ደግሞ የልጁ ሚስትን ማለት ነው። አዋጅ፦ ጊዜ ወስጄ ያጠናቀርሁት ነው።ዐላማዬም በጉዳዩ በቤተክርስትያን ውይይት ለማነቃቃትና ለዚሁ መነሻ ዐሳብ ለማቅረብ ነው። ይህ ለመግቢያ ይሁን።  በ አማትና ሥነ-ሥርዐት (awondimts.com)  ይቀጥላል። (ዋቢ መጨረሻ ተዘርዝሯል) ነገረ አማት ወምራት      ልጆች ማንነታቸውን የሚመሠርቱበት፣ የወገንነት ስሜት የሚያገኙበት፣ ለራሳቸውም ሆነ ለወገኖቻቸው የሚኖራቸውን ኅላፊነት የሚማሩበት ማኅጸን ቤተሰብ ይባላል። ደህንነት፣ ከለላ ፣ ድጋፍና ፍቅር አግኝተው የሚያድጉትም በዚያ ነው። ቤተሰብ የሚሰፋውና ቀጣይ የሚሆነው ደግሞ በጋብቻ /በትዳር ነው። ትዳር ማለት በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መኻል አዲስን ቤተሰብ ለመመሥረት የሚገባ ቃልኪዳን ነው። ከዚህ የተለየ ትርጉም የሚሰጡት ማኅበረሰቦች መኖራቸው የሚታወቅ ሲሆን ይህ ጽሑፍ በዚሁ ክርስትያናዊ ትርጉም የተወሰነ ነው።      ትዳር በወላጅ ወይም በተጋቢዎቹ በራሳቸው ምርጫ ሊመሠረት ይችላል። በወላጅ ምርጫ የሚፈጸሙ በሃይማኖትና በማኅበራዊ አቋም በሚኳኋኑ መኻል ይገደባል ። ወላጆች ሲሆኑ ጥሩ የቤተሰብ ዳራ ፣ በቂ መተዳደሪያ እንዲሁም በተመሳሳይ ሃይማኖት ወይም ዘር መሆናቸውን አረጋግጠው ይድራሉ።የሚመራረጡት ወላጆች ነበሩ። በተጋቢዎቹ በራሳቸው ምርጫ ትዳር ሲመሠረት ግን ወላጆች በምርጫው ላይ የሚያሳድሩት ተጽእኖ ...